09/09/2025
የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ተመስገን ጥላሁን (ኢንጂነር) ያስተላለፉት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት፦
የአንድነታችን አርማ የኢትዮጵያዊያን ተጨማሪ የወል እውነት የሕዳሴ ግድብ ምረቃ በዓል እንኳን አደረሰን!
መላው ኢትዮጵያውያን በቁጭት ተነስተው ካላቸው ሳይሆን ከሌላቸው አጉድለው በባለቤትነት የገነቡት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያዊያን ከብርሃንም በላይ ነው።
በአምስት አመት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ተወጥነው የተጀመረው ግድባችን ግንባታው እንዳይሳካ በውጭ የኢትዮጵያ ታርካዊ ጠላቶች በውስጥ ሀገርን የሚሸጡ ባንዳዎች ተናበው ያደርጉ የነበረው አሰናካይ አካሄድ ምክንያት ተደናቅፎ ከነበረበት በመሪያችን ቁርጠኝነትና የድፕሎማሲ ጥበብ ዳግም አንሰራርተው በሚደነቅ መልኩ እነሆ እውን ሆኗል።
ብልጽግና ፓርቲ በ2018 ዓ/ም ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን ለመድረስ ያስቀመጠውን ግብ እውን ማድረጉን ያረጋገጠበት የሕዳሴ ግድብ ከብርሃንነት ባሻገር ለኢትዮጵያዊያን ተጨማሪ እድሎችን የሚያመጣ እንዲሆን ተደርጎ ተገንብቶ ተጠናቋል።
ቃልን በተግባር ከማሳየት ቦዝኖ የማያውቀው ብልጽግና ፓርቲ ከሁለት ዓመት በፊት "ኢትዮጵያ በእዳ ከመጨፍገግ ወደ በምንዳ መንበሽበሽ" ማለቱ የሚተወስ ስሆን እነሆ ቃሉን ለመፈጸም የብርሃን ጮራ መፈንጠቅ ጀምሯል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ታፍራና ተከብራ ትኑር!
እንኳን ደስ አለን አላችላሁ!
ተመስገን ጥላሁን (ኢንጂነር)
የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
ጳጉሜ 04/2017 ዓ/ም