Santu seera

Santu seera Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Santu seera, Grocers, Adama.

23/04/2025

ለፈገግታ
አንዱ ጥሬ ስጋ በጣም ነው የሚወደው።
እናም አምሮቱን ሊወጣ አንድ ስጋ ቤት ገባና ...
"ወንድሜ ከዚህ ላይ ትቆርጥልኝ?"
"ምንችግር አለ ይቆረጥልሀል!"

"እሺ አንድ ኪሎ ስንት ብር ነው?"
"1000 ብር!"
"እንዴ? አንድ ኪሎ?🤔
ምነው አልበዛም እንዴ በሬውኮ የኛን ሰፈር ሳር በልቶ ነው ያደገው። ከጃፓን ወይንም ከኮሪያ አልመጣ!😳"
"ወንድሜ የምትበላ ከሆነ ብላ አለበለዚያ ሙድ አትስረቅ ውጣ!"😳
"እሺ በቃ ግማሽ ቁረጥልኝ!" ብሎ ቁጭ አለ ተቆርጦ ሲመጣለት በንዴት ብው ብሎ ...

"አሁን ይሄ ግማሽ ይሞላል?😳 ምነው በዛ! እኔ በኪሴ ሚዛን ይዤ መዞር አለብኝ? አረ ተዉ ግፍ ነው! ያሳዝናል🙄" እያለ ያቺን ስጋ ትም ትም እያደረገ ሳለ ድንገት መብራት ጠፋ።

ይሄኔ ቢላውን ይዞ ወንበር እያጋጨ በጭለማ እየተደናበረ ከተሰቀለው ስጋ ላይ ላጥ አደረገና ቁጭ ብሎ እየበላ
"ወይጉድ! መብራት በቦታው ሲጠፋ ለካ ይጠቅማል ጎበዝ!🙄" እያለ ጨረሰ። አሁን ንጭንጭ የለ።
ስሞታ የለ። በላዩ ላይ አምቦ ውሀውን ከልበስ አደረገና ሆዱን እያሻሸ አስተናጋጁን በጭብጨባ ጠርቶ "ሂሳብ አምጣ!" አለው።

ብሩ ተሰርቶ ሲመጣለት እያየው ቆየና
"ምንድነው ይሄ?😳" አንድኪሎ 1000 ብር ከሆነ ግማሹ 500 ነው መሆን ያለበት። 50 ብር የተጨመረው ለምንድነው?😳 እኔ እንጀራ ወይንም ዳቦ አላስጨመርኩ!" ብሎ ሲያፈጥበት ..

አስተናጋጁ :-"በጭለማ ሳምባ በልተሀል!🙄"

ምንጭ ኮሜድያን አሰፋ ተገኝ

Address

Adama

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Santu seera posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category