Agew's አፍሌን Voice

Agew's አፍሌን Voice Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Agew's አፍሌን Voice, Addis Ababa.

28/01/2025

እንኳን ለ85ኛ ዓመት የአገው ፈረሰኞች በዓል አደረሳችሁ!
-----
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አገው ጥናት ኢንሲቲትዩት በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሲምፖዚየም ተዘጋጅቷል።

ስለሆነም ጥር 22/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በአዊ ባህል አዳራሽ በመገኘት እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

28/01/2025

85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል 5 ቀን ቀድሞ ተጀምሯል።በትናንትናው ዕለት የአድማስ ዩኒየን የሰራተኞች የቁንጅናና የፈረሰኞች አለባበስ ውድድር መጀመሩን እናስታውሳለን፣

❤ ዛሬ ጥር 20/2017 በአገውኛ ቋንቋ የተሰራውና 'አንታጉ' ፊልም በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግርና የኢንተርኔት መቋረጥ በአግባቡ ለህዝብ ስለሚለቀቅበት መንገድ ይመከራል
❤በ21/05/17 በእንጅባራ ከተማ አቅራቢያ ባሉ የማሪያም አብያተ ክርስቲያናት ኃይማኖታዊና ባህላዊ የንግስ አከባበር እንታደማለን(አስተርእዮ ማሪያም)
❤ በ22/05/2017 ጠዋት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት ከሰዓት የባህላዊና ዘመናዊ የጃኖ ፋሽንና የወይዘሪት አገው አዊ የቁንጅና ውድድር ይካሄዳል
❤ ጥር 23/2017 በግዙፉና አንጋፋው በአገው ፈረሰኞች ልዩ ልዩ ትዕይንቶች በእንጅባራ ስቴዲየም ይካሄዳል።
እርስዎም የአገው መገለጫ የሆነው ጃኖ በመልበስ ጥር 23 ይገኙ።

12/05/2024

ማስታወቂያ!

አገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል

በእንጅባራ (በኮሶበር) ከተማ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ስፔሻሊስት ሀኪሞችና ዘመኑ ባፈራቸው የህክምና መሳሪያዎች ተደራጅቶ ስራ በጀመረ ባጭር ጊዜ ውስጥ ሺዎች ተፈዉሰዋል።

ሆስፒታላችን !!
👉ፉሊ አዉቶሜትድ በሆኑ ማሽኖች የተደራጀ ላቦራቶሪ
👉ባላ 5ፕሮቭ ሳምሰንግ HS40 እና ሌሎች ዶፕላር አልትራ ሳዉንዶች👉ሲቲ ስካን
👉 ዲጅታል ራጅ ,ECGና በመሳሰሉ ማሽኖች በመታገዝ

1. ጠቅላላ የዉስጥ ደዌ ህክምና
2. ከፍተኛና ዉስብስብ ቀዶ ህክምና
3. የአጥንትና መገጣጠሚያ ምርመራናቀዶ ህክምና
4. የነፍሰጡር ክትትልና የማዋለድ አገልግሎት በኦፕራሲዮንና ያለ ኦፕራሲዮን
5. የመካንነት (Histro sulfingograpgy)ምርመራ
6. ጠቅላላ የህፃናት ምርመራና ህክምና
7. የመነፅር ምርመራን ጨምሮ በAScan እና በB scan የዓይን አልትራ ሳዉንድ የታገዘ ጠቅላላ የዓይን ህክምና
8. ሰዉ ሰራሽ ጥርስ መስራትን ጨምሮ ጠቅላላ የጥርስ ህክምና
9. በሜካኒካል ቬንትሌተር የታገዘ የአዋቂዎየችናጨቅላ ህፃናት ፅኑ ህሙማን ህክምና
10. የቆዳና አባላዘር በሽታዎች ህክምና
11. የአምቡላንስ አገልገሎት
12. በ ባለሙያና በአቅርቦት እጅግ የተደራጀ መድኃኒት ቤት
13. ለተኝቶ ታካሚዎች VIp እና ኢኮኖሚ ክፍሎች ዝግጁ ናቸው ፡ ፡
14. ለድርጅቶች ዱቤ ህክምና እንሰጣለን

👉ልብ ይበሉ
ሁሉም ህክምናዎች በስፔሻሊስት ሀኪሞች ብቻ ይሰጣሉ

አድራሻ ፡ በደጋዋ ገነት እንጅባራ ከአደባባይ ወደ ቻግኒ መዉጫ 50 ሜትር ገባ ብለዉ ያገኙናል

 # አገውነት ይለያል..........❤️❤❤
02/05/2024

# አገውነት ይለያል..........❤️❤❤

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥Today's Best photo🥰🥰🥰🥰Agew's Voice ❤❤❤
20/04/2024

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
Today's Best photo🥰🥰🥰🥰
Agew's Voice ❤❤❤
















🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥Today's Best photo🥰🥰🥰🥰
20/04/2024

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
Today's Best photo🥰🥰🥰🥰
















ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣትአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል...
21/07/2023

ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ባስመረቀበት ወቅት ነው ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት የሰጠው፡፡

የክብር ዶክትሬቱን በወላጅ እናቷ በወ/ሮ ተናኜ አማካኝነት ተቀብላለች።

በመርሐ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር)÷አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሀገሯን ሙዚቃና ባህል እንዲሁም የተወለደችበትን የአገው ህዝብ ባህልና ቋንቋ ለዓለም ህዝብ በማስተዋወቋ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስቷ የክብር ዶክትሬት ሲሰጣት ታላቅ ክብር ይሰማዋል ብለዋል፡፡

ጂጂን ማክበር ጥበብን ማክበር ነው ያሉት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር)÷ጂጂን ማክበር የኢትዮጵያን ታሪክና ጀግኖችን እንዲሁም ፍቅርንና አንድነትን ማክበር ነውም ብለዋል፡፡

ተቋሙ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲውን በታሪክ ሊያስታውስ የሚችል የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለድንቋ ድምጻዊትና ለጥበብ ንግስት ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) በሚሰጥበት እለት መሆኑ መርሐ ግብሩን ለየት ያደርገዋልም ብለዋል፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agew's አፍሌን Voice posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share