ማኅቶት ዘተዋህዶ Mahitot z tewahedo

  • Home
  • ማኅቶት ዘተዋህዶ Mahitot z tewahedo

ማኅቶት ዘተዋህዶ Mahitot z tewahedo Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ማኅቶት ዘተዋህዶ Mahitot z tewahedo, Grocers, .

20/05/2024

እኔና ተሻገር
ሃብታሙ ተካልኝ
ግንቦት 9-2016 ደሴ
ሃሳቦች ሁሉ ወደ ተሻገር ናቸው.. ይልቅ ከመንፈስ ቅዱስ ተዋልደናን የቤተክስቲያን ልጅነታችን አስተሳስሮናል የሚሉ ወንድሞችና እህቶች ለአፍታ እንኳ ስለእርሱ ከመጨነቅ ቦዝነው አያውቁም... በሃያዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወጣት የዪንቨርስቲ ተማሪ ነው ተሸገር ..በተለይ ከፍሬሽ ማን ጀምሮ የሚውቁት ወዳጆቹ ከቤተሰቦቹ ጋር የነበረው ቆይታ ምንያህል በስነ ምግባር ታንጾ ያደገ እንደሆነ ለመገመት አልከበዳቸውም …ምክንያቱም መንፈሳዊነቱ፤ ታታሪነቱ፤ ሰው አክባሪነቱ.. ምን አለፋችሁ ተሻገር ማለት ኦርቶዶክሳዊና ሰዋዊ ቃናው ዘወትር የመንገድ አላፊውን ሁሉ ቀልብ እንደገዛው ነው….አሁን ይህ ታሪክ ከተከወነ ሁለት ዓመታት አልፈዋል በማያረጅና በውዕደቱ መሃል ወዘናው በማይወይብ የግዜ ሃዲድ እየገሰገሰ ያለው ተሻግር መሳፈሪያውን ግዜን በማንነት መሆን ያቃተው ይመስላል ….ለዚህም ነው በቅርብ የሚያውቁት ወዳጆቹ አብዝተው እሰለርሱ መጨነቃቸው….ዛሬ ያ ፍሬሽ ማን እና የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ እያለ ያሳሳ የነበረ መንፈሳዊነቱ ኮሳሷል፤ ታዛዥነቱ፤ ሰው አክባሪነቱና ትህትናው የተሰራባቸው መሰረቱ እንዳልሆኑ አሁን አሁን እንደ መስከረም ወፍ የሚናፈቁ ምግባራቱም ከሆኑ ሰነባብተዋል ….የመንፈስ ፍሬያትም ታጭደውበት በቃርሚያ ከቀረ ቆየ…..ለዚህ ነው ተሻገር ምን ነካው የሚሉ አንደበቶች የበረከቱት …. አልፎ አልፎ ከፋ ሲልበትም ሱስ ቤቶችም ይታያል … ኦ ተሻገር….

….እኔም ስለ ተሼ ከሚጨነቁ ወንድምና እህቶች መሃል እራሴን አገኘውት ….አንድ ቀን ግቢ ጉባኤያችን ከሚገለገልበት ቤተክርስቲያን ቅጥር አጸድ ስር ቁጭ ብዬ ስለ ተሼ ማሰላሰል ጀመርኩ ….ዓይነ ህሊናዬን ከጠፋው ወንድማችን ላይ ተክዬ በጥያቄ አፋጥጠው ጀመር ….ግን ምን ነካህ?…አሁን ባለህበት ህይዎት ሰላም ይሰማሃል? ….የቱ ሃይል ነው ከከፍታህ ያወረደህ? ….ከኪዳኑና ከቅዳሴው ስርዓት ተገኝቶ ከህጣኑ መዓዛ ከመካፈል ይልቅ ዓለም የአዳምን ዘር የምታጠምድበት የመጠጡና የጫቱ የከረፋ ሽታ እንዴት አድርጎ ቀልብህን ገዛው? …..እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ሰነዘርኩበት …….መልስ የለም …..እንባዬ ድንገት ተወርዉሮ መሬት ጠብ ሲል ከሃሳቤ ነቃው ….ሰዓቱን ሳየው 2፤00 ይላል የትምህርት መግቢያ ሰዓታችን ስለደረሰ ወድያው ከተቀመጥኩበት የዛፍ ግንዳፊና የትካዜ ዙፋን ብድግ ብዬ አቡነ ዘበሰማያት ልደግም ተሰናዳው …….ወዴት ወዴት አለኝ አዕምሮዬ ….ደነገጥ …እውነት ተሻገር ነህ አንተ የሚለቀስለት? አለኝ አዕምሮዬ ….እንዴት? አልኩ ሙግት መግጠም ሳልፈልግ አዕምሮዬን ገጠምኩት …..ስንት ለሰው የማይታይ የፈረሰ ጎን አለህ?…..ስንትስ ግዜ በስንፍና: በቸልተኝነት የሚወድህ አምላክህን ልቡን አቁስለኸዋል? ….ቀጠለ … ….ስለተሼ እንቅልፍ ያጣችሁ ወንድምና እህቶቼ ስለኔም ጭራችሁ አንቡ››…………ድጋሚ ከሃሳቤ ብንን ብዬ አቡነ ዘበሰማያቴን አድርሼ ወደ ዩንቨርሲቲያችን አመራሁ….

22/02/2024

ልብ ሰባሪ ዜና 💔💔💔

የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 መነኮሳት በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

ከገዳሙ በስልክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የካቲት 12/2016 ዓ.ም የታጠቁ ሰዎች ወደ ገዳሙ በመግባት ሁለት መነኮሳት መውሰዳቸውን እነሱ ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቁ በማግስቱ የካቲት 13/2016 ዓ.ም ታጣቂዎቹ ድጋሚ መጥተው ለውይይት እንፈልጋችኋለን በማለት 3 መነኮሳትን ወደ "ጂዳ ተክለ ሃይማኖት" ወስደዋል ብለዋል።

መነኮሳቱ "ለውይይት" ሲባሉም "ችግር የለውም እናንተ አባቶች እዚህ ቆዩ እኛ አነጋግረናቸው እንመጣለን፤ ተረጋጉ" ብለው ታጣቂዎቹን ተከትለው ከገዳሙ ሂደዋል።

ቀኑን ሙሉ ስልካቸው ክፍት እንደነበረ አመሻሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ተጨንቀው የአካባቢውን ምእመናን ሲያጠያይቁ 4ቱ መገደላቸውን እንደነገሯቸው አንደኛው አባት ግን ተለቀዋል ቢባልም እስካሁን ያሉበት እንዳልታወቀ አባቶቹ ለጣቢያችን በእንባ ተናግረዋል።

በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች

፩ አባ ተክለ ማርያም አሥራት (የገዳሙ መጋቤ)
፪ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን (የገዳሙ ዋና ጸሐፊ)
፫ አባ ገብረ ማርያም አበበ (ቀዳሽ ካህን፣የመጽሐፍ መምህርና የገዳሙ አስተዳደር አባል)
፬ ባህታዊ ኃ/ማርያም ስሜ (የገዳሙ የአስተዳደር አባል) ሲሆኑ
እስካሁን ያሉበት ያልታወቀው ደግሞ አባ ኪዳነ ማርያም ገ/ሰንበት ናቸው።

(ዜናው የማኅበረ ቅዱሳን ነው)

🤲​21🤲📚📚📚📚📚📚📚ወዳጄ ሆይ! እናታችን ቅድስት ድንግልማርያም ከልጇ ከወዳጅዋ ጋር ሰርግ ተጠርታወደ ቃና ዘገሊላ ሄደች። ታድያ በዚያን ጊዜእንግዳችን በማስተናገድ ላይ እያለ ዶኪማስየወይን ጠ...
30/12/2021

🤲​21🤲

📚📚📚📚📚📚📚
ወዳጄ ሆይ! እናታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ከልጇ ከወዳጅዋ ጋር ሰርግ ተጠርታ
ወደ ቃና ዘገሊላ ሄደች። ታድያ በዚያን ጊዜ
እንግዳችን በማስተናገድ ላይ እያለ ዶኪማስ
የወይን ጠጅ አለቀበት። የሰው ልጅን ጭንቅ
ገና ሳይነግርዋት የምትረዳ፣ ቅድስት ድንግል
ማርያም ለውርደት የተቃረበ ዶኪማስን
በፍቅር ዓይን ተመለከተችውና ተነሥታ
“የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም” በማለት ለልጇ
ለወዳጇ ለኢየሱስ ክርስቶስ አሳሰበች። ዮሐ.
2፥3። ክቡር አንባቢ! እዚህ ላይ ዶኪማስ
የወይን ጠጅ አልቆብኛልና እባክሽ
እንዳልዋረድ ለችግሬ መፍትሔ ስጪኝ ብሎ
አልጠየቃትም። የፍቅር እናት ከቶ
አታሳፍርምና እርሱ ባይጠይቃትም ችግሩን
አውቃ አላሳፈረችውም።
ታሪኩ ስንቀጥለው ደግሞ “የእናት
ልመና ፊት አያሰመልስ አንገት አያስቀልስ”
እንደሚባለው ሁሉ ልጇ ወዳጇ ጥያቄዋን
ተቀበላት እና “አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን
አለኝ?” ብሎ ጋኖቹን ሁሉ በውኃ እንዲሞሉ
አዘዘ። ዮሐ. 2፥4። በእመቤታችን ምልጃ
ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ ቀየረላቸው።
የሚገርመው ደግሞ የተቀየረው ወይን ጠጅ
ከመጀመሪያው ይልቅ የሚያነጋግር ጣፋጭ
ወይን ሆነ። ወዳጄ ልብ በል! ዶኪማስም
በእንግዶቹ መኃል ያላፈረው በሰርጉ
እመቤታችንን ከነልጇ ስለጋበዘ ነው።
“የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች” ዮሐ 2፥1።
ዛሬም እኛም ብንሆን በስእሏ ፊት በመቆም
ውዳሴዋን እየደገምን ብንለምናትና
በምናደርገው ጉዳይ ብንጋብዛት ለዶኪማስ
ያደረገችውን ድንቅ ተአምር በእኛም ላይ
መድገሙ አይከብዳትም።
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

 (ክፍል አንድ)ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባ...
30/12/2021


(ክፍል አንድ)

ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው:: ይህ አባት መስከረም አራት ቀን በዚች ዕለት እንደተወለደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡

ዮሐንስ የሚለው ስም ዮሐናን ከሚለው ቃል የተገኘ ሲኾንትርጓሜውም “ከያሕዌ (ከእግዚአብሔር) የተሰጠ” ማለትእንደኾነ ብዙ ሊቃውንት ይስማማሉ፡፡ ትርጓሜ ወንጌል ግን“ዮሐንስ ማለት ፍስሐ ወሐሴት ማለት ነው” ይላል፡፡ ቅዱስዮሐንስ ብዙ ቅጽል ስሞች አሉት፡፡ ከእነዚኽም መካከል፡-

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በመግለጡናለጌታችን ባለው ቅንዓት ባሳየውም የኃይል ሥራ “ቦኤኔርጌስ-ወልደ ነጐድጓድ” /ማር.፫፡፲፯/፣

የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት ስለሚናገር “ታዖሎጐስ-ነባቤ መለኰት”፣

ኃላፍያትንና መጻእያትን ስለሚናገር “አቡቀለምሲስ-ረአየኅቡአት- ባለ ራዕይ”፣

እንዲሁም የጌታን ጸዋትወ መከራ አይቶ ፊቱ በኃዘን ተቋጥሮይኖር ስለ ነበር “ቁጹረ ገጽ- ፊቱ በሐዘን የተቋጠረ” ይባላል፡፡

ጌታችን ግርማ-መንግሥቱን ሲገልጥ /ማቴ.፲፯፡፩/፣ የኢያኢሮስንልጅ ሲያነሣ /ማር.፭፡፴፯/፣ በጌቴሴማኒ የአታክልት ቦታ ሲጸልይ/ማቴ.፳፮፡፴፯/፣ ስለ ኢየሩሳሌም መጥፋት ትንቢት ሲናገር/ማር.13፡3/ ዮሐንስ አብሮ ስለ ነበር “የምሥጢር ልጅ”ምይባላል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ አዕማደ ቤተ ክርስቲያን ብሎ ከሚጠራቸው ሐዋርያት አንዱ ዮሐንስ ነው /ገላ.፪፡፱/፡፡

ከሌሎቹ ደቀ መዛሙርት በተለየ አኳኋንም ጌታን ይወደው ስለነበር ሁሌ ከእቅፍ አይለይም ነበር፡፡ በዚህም “የጌታ ወዳጅ-ፍቁረ እግዚእ” ተብሏል /ዮሐ.፲፫፡፳፫/፡፡

ከነዚህ በተጨማሪ ወንጌላዊው፣ ሐዋርያው፣ ድንግል፣ ዘንሥር፣ዘረፈቀ ውስተ ህፅኑ ለኢየሱስ፣ ካልእ ረድእ፣ ባሕረ ጥበባት፣አበ ልሳናት… እየተባለም ይጠራል፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ አባቱ ዘብዴዎስ የሚባል የሲዶና ሀገር ገሊላዊ ሲሆን ዓሣ አጥማጅ ነበር፡፡ እናቱም ማርያም ባውፍልያ እንደምትባልና ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ መኾኗን የቤተ ክርስቲያናችንትውፊት ያስረዳል /ማቴ.፳፰፡፩/፡፡

🙏ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በወንጌላዊዊ ዮሐንስ ፀሎት ይማረን🙏

(ክፍል ሁለት ይቀጥላል..

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማኅቶት ዘተዋህዶ Mahitot z tewahedo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Grocery Store?

Share