04/12/2023
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ም/ቤት በአሶሳ ከተማ እና አጎራባች ወረዳዎች ጸጥታ ዙሪያ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
**********************************************
(ህዳር 24/16ዓም አሶሳ)
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ም/ቤት በአሶሳ ከተማ እና አጎራባች ወረዳዎች ጸጥታ ዙሪያ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
የጸጥታ ም/ቤት ስብሰባውን የመሩት ክቡር ከንቲባ አቶ አብደልከሪም አብደረሂም፤ የአሶሳ ዞን መስ/ር ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዑስማን መሐመድ፤የቤ/ጉ/ክ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አምሳሉ አሪና እና የቤ/ጉ/ሚ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኦሳም የሱፍ ጋር በጋራ በመሆን ሲሆን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር እና አጎራባች ወረዳዎችን ጸጥታ ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ በመወያየት
የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፈዋል፡-
**********
1ኛ/ማንኛውም ሰሌዳ የሌላቸው ባጃጆች፣የሞተር ብስክሌትና መኪና በማንኛውም ሠዐት እንዳይንቀሳቀ፤
2ኛ/በአሶሳ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ ከ2፡00 እስከ ንጋቱ 12:00 ባጃጅና የሞተር ብስክሌት ከተፈቀደላቸውና ወደ ህክምና ከሚያጓጉዙ ውጪ የእንቅስቃሴ ገደብ የተጣለ መሆኑ.፤
3ኛ/ በአሶሳ ከተማ የሚገኙ የጭፈራና መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ እንዲዘጉ የሠዐት ገደብ የተጣለ መሆኑ
4ኛ/ የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን መረጃ ለቀበሌያቸው እንዲያሳውቁ፤በማያሳውቁ አከራዮች ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን፤
5ኛ/የሆቴል አልጋ አከራዮች ህጋዊ የታደሠ መታወቂያ ያላቸውን ደንበኞች ብቻ እንዲያከራዩ፤አጠራጣሪ መረጃዎችን ሲያገኙ ወዲያውኑ ለቅርብ የጸጥታ አካላት እንዲያሳውቁ ፤
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር፣የአሶሳ ዞን፣የቤ/ጉ/ክ/ፖሊስ ኮሚሽንና የቤ/ጉ/ሚሊሻ ጽ/ቤት ጥምር ጸጥታ ም/ቤት ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ለተፈጻሚነት ይህ ውሳኔ ከተወሰነበት ከ25/03/16ዓም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚፈጸም፤ ሁኔታዎች እየተገመገሙ ማሻሻያ የሚደረግ ሆኖ በየደረጃው እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው የጸጥታ መዋቅርና ዘወትር ለጸጥታ ተባባሪ የሆነው የአሶሳ ከተማአስተዳደርና አጎራባች ወረዳዎች የበኩላቸውን እንዲያስፈጽሙ ተወስኗል፡፡