Wansisa Wana /Siso/

  • Home
  • Wansisa Wana /Siso/
Permanently closed.
02/04/2026
በዚህ ጉዳይ ከሰሞኑን በሚዲያና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በተመለከትነዉ ልክ እዉነታዉ ይህ ይሆናል ብለን ፈጽሞ አልጠበቅንም አልገመትንም ነበር። (ከስር የተለጠፉትን እያንዳንዱን ፎቶዎች ከፍ...
02/04/2026

በዚህ ጉዳይ ከሰሞኑን በሚዲያና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በተመለከትነዉ ልክ እዉነታዉ ይህ ይሆናል ብለን ፈጽሞ አልጠበቅንም አልገመትንም ነበር።

(ከስር የተለጠፉትን እያንዳንዱን ፎቶዎች ከፍተዉ ይመልከቱ! የቪዲዮ ሊንክም ከስር አስቀምጠናል!)

የክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተች ከጥቂት ጊዜ በኋላ ማስፋፊያ በማስፈለጉ በ2013 ከአከራዮች ጋር የሶስት ዓመት ኮንትራት ዉል በመግባት ተጨማሪ የአዳራሽና ሌሎች ግንባታዎችን ለማድረግ በስምምነት ኦና የነበረዉንና ከአገዳ በማይሻል ነገር የተሰሩ ቀድሞ የነበሩ የፈራረሱ ዝናብና ፀሐይ የሚያፈስባቸዉ ቤቶች እነሱን የሚፈርሰዉን በማፍረስ የሚታደሰዉን በማደስ ከ10 ሚሊየን በላይ በሆነ ወጭ አድሰዉ ሲያጠናቅቁ አከራዮች ነን ያሉት በመምጣት አመድ የመሰለ ጊቢዉ ዉሎ አድሮ ተዉቦና ደምቆ ሲመለከቱ ከ2 እጥፍ በላይ ጭማሪ አድርጉ ካልሆነ አንዳች ንብረታችሁን ሳትይዙ ለቃችሁ ዉጡ!” በማለት ፍ/ቤት ክስ መስርተዉ ላም እሳት ወለደች.. አይነት ነገር ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ወጪ አዉጥታ ያረገችዉን ግንባታ ለቀዉ እንዳይወጡ ከፍተኛ ገንዘብ፤ የምዕመኑ ጉልበትና ጊዜ የፈሰሰበት መሆኑ፤ እንዳይቀጥሉ ቀድሞ ከተደረገዉ ስምምነት ዉጪ ሁለት እጥፍ ጭማሪ ክፍያ በመጠየቅ ለሰሚም ለተመልካችም ጆሮን ጭዉ የሚያደርግ የክህደት ጥግ በማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንድትፈናቀል አድርገዋት ሳያበቁ በሚዲያ ላይ እኛም እናንተም ሲጮህ የነበረዉ ጩኸት ሌላ ሆኖ ከራረመ። በቲክቶክ ያሉ ጎሮምሶችንና የኃይማኖቱ ተከታይ ባልሆኑ ሰዎች ጭምር ክርስትናን በሚያስነቅፍ መልኩ የቤተ ክርስቲያኒቷን ባለራዕይ ዶክተሩን ጭምር ሲሰድቡ ሲያብጠለጥሉ ወንጀለኛ አርገዉ ሲፈርጁ ሲያጠለሹ በሁሉ እምነት ሲያሳጡት መሰንበትን ስራዬ ብለዉ ተያይዘዉ ሰነበቱ። በዚህም ሳይበቃ ቤቱን የኪራይ ጊዜዉ ሳይደርስ ከነግንባታዉ ወስደዉ፤ ለግንባታ ያወጣቸዉን ሚሊየን ብሮች እንኳ መክፈል ይቅር ጭራሽ በሀሰት የዓመታት እዳ አለበት ብለዉ እንዲፈጽም ተብሎ ሰማን። የእዉር ድንብር የሆነ ፍርድ!

በተራ የመንደር ቲከቶከርና ፌስቡከር እያስጮሁ በዚህ ልክ የዜጎችን የአልጋዮችን መብት መግፋት ምን ማለት ነዉ? ያዉም የቤተ እምነታችንን ወንጌል የሚሰራበትን!

አልፎ ተርፎ ካስረከብናችሁ ውጪ ባነርና ስቲከሮችን ከመለጣጠፍ ባለፈ ምንም ግንባታ አላከናወናችሁም የሚል የፍርድ ቤት ክስ በማምጣት ክርክሩን የመሬት ልቀቅ አልለቅም። ግብግብ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ የራሷን ንብረት ይዛ ልትወጣ የጠየቀችበት ጥያቄ ነበር። ሆኖም ጉዳዩ በሚዲያዎች ጩኸት ተጣመመ፤ እውነት ተደበቀ፤ ስም ለማጠልሸት የተሰሩ ትርኢቶች ተቀናበሩ ዋና መጋቢውም በቀጥታ ኢላማ ተደረጉ።

እዉነት ለመናገር በዚህ ልክ እኛም እናንተም ሌላዉም ዜጋ በጉዳዩ ላይ የዚህን ዓይነት እዉነት ይኖረዋል ብሎ የገመተ አይኖርም። እኛም አልነበረንም። ነገር ግን ጉዱ ሌላ የተነገረዉ ሌላ መሆኑ በጉዳዩ ላይ ምርመራችንን እንደናሰፋ አድርጎን እዉነታዉን ከዉጭም ከራሳቸዉ ከከሳሽ ወገን በኩል በተለያየ ሁኔታ በሚገባ ማረጋገጥ እንድንችል ሆነናል።

በአጠቃላይ በየክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ላይ ለአመታት በተለያዩ የሚዲያ አዉታሮች በግለሰቦች ሲነገር የነበረዉ ነገር እንዲህ ባለ መልኩ የተፈጸመ በእዉነት ያልተገባ የማጭበርበር ተግባር ጭምር ነዉ። እስቲ ለመረዳት ከታች ያሉትን አስረጂ ፎቶዎች ቀድሞ ገና ሲከራዩና ከክራይ በኋላ የነበረዉን የጊቢዉን ገጽታ የግንባታዎች ሁኔታ እያንዳንዱን ተመልከቱ!

እነዚህ ሰዎች ለሕግ ይቅረቡ !!!!!

ሊንኮቹንም ይመልከቱ👇
https://youtu.be/I0k74f96JVs?si=ERHHTGD2QTp8iIyE

https://youtu.be/1vPA79xyi8Q?si=t51lEP_bk_sgdpBd

በክፍል 2 እንመጣለን

Address

Bole Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wansisa Wana /Siso/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wansisa Wana /Siso/:

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed Grocery Store?

Share