02/05/2025
የሴቶች አደረጃጀት ተቋም በማጠናከር ለጠንካራ ፓርቲ መመስረት ተግቶ መስራት ይገባል!!!
አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም
በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሴቶች ክንፍ የ3ተኛ ሩብ ዓመት ኮንፈረንስ በደመቀ መልኩ አከናወነ።
የሴቶች አደረጃጀት ተቋም በማጠናከር ለጠንካራ ፓርቲ መመስረት ተግቶ በመስራት የሴቷ የውሳኔ ሰጪነት ሚና የበለጠ ማረጋገጥ ላይ ተግቶ መስራት እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊና የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም ገልጿል።
ሴቶች የሀገር ግንባታ ሚና ግንባር ቀደም ሚና እንዳላቸው የገለፁት አቶ ተወዳጅ ይህ የበለጠ ከፍ ለማድረግ በሁሉም ዘርፎች የሴቶች ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ አመላክቷል።
ሴቶች ለሀገር እድገትና ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው የገለፁት የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊና በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሴቶች ክንፍ የስራ አስፈፃሚ ኮሙቴ አባል ወ/ሮ ለምለም ንጉሴ የሴቶች ክንፍ የፓርቲ ተልዕኮዎችን ከግብ በማሳካት በግንባር ቀደምትነት በመወጣት ጠንካራ ፓርቲ እንዲፈጠር የሴቶች ተሳትፎ አይተኬ ሚና እንደነበረ አስገንዝቧል።
ሴቶች በውሳኔ ሰጪነትና በአመራር ተሳትፎ ላይ ከወረዳ ጀምሮ ያለው ውጤታማነት እጅግ አበረታች መሆኑና ይህ ጠንካራ ተቋም ከግብ እንዲሳካ ማድረግ እንደሚገባ ወ/ሮ ለምለም ተናግሯል።
ባሳለፍነው ሶስት የሩብ ዓመት የበጀት አመት በሴቶች ክንፍ በርካታ መደበኛና ወቅታዊ የንቅናቄ ስራዎች መሠራታቸው የገለፁት በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ባይሳ ፓርቲያችን በሰው ሀይል በፋይናንስ ለማጠናከርና ለመደገፍ የተሰራበት አግባብ እጅግ አመርቂ እንደነበር አስገንዝቧል።
በመጨረሻም የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀሙ ላይ ውይይት በማድረግና የስራ አስፈፃሚ ኮሙቴዎች በማፅደቅ አቅጣጫ በማስቀመጥ ኮንፈረንሱ ተጠናቋል።