Mizan tappi city

Mizan tappi city Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mizan tappi city, Grocers, mizan tapi, Addis Ababa.

07/08/2024
✍️በሸካ ዞን ሰሞኑን ከትላንት ወድያ የተመረቀው 27ኪሎሜትር መንገድ  በ30ሚሊዮን ብር✍️ቤንች ሸኮ ዞን ዛሬ የተመረቀው ድልድይ በ47ሚሊዮን ብር ✍️ ቆይ ግን ንቀት ነው ወይስ የሸክበዶ መ...
05/08/2024

✍️በሸካ ዞን ሰሞኑን ከትላንት ወድያ የተመረቀው 27ኪሎሜትር መንገድ በ30ሚሊዮን ብር
✍️ቤንች ሸኮ ዞን ዛሬ የተመረቀው ድልድይ በ47ሚሊዮን ብር

✍️ ቆይ ግን ንቀት ነው ወይስ የሸክበዶ መንገድ አንድም ድልድይ በሌለበት እና ጠጠር ራሱ ሳያለብሱ መንገድ አስመረቅን የምሉት
✍️ለሸካ ዞን ሁላችንም ድምፅ እንሁን ከፖለቲካ ወተን እስቲ ሸካ እንወዳለን የምትሉት ሀሳባችሁን ስጡ ።🙏🙏🙏🙏

ቤንች ሸኮ
05/08/2024

ቤንች ሸኮ

" #ሾንጋም" የድምፃዊ ፍቃዱ ዛሀ/ ዜዋ/የቤንችኛ ባህላዊ የሙዚቃ ስራ ተመረቀ‼==============================ሚዛን አማን ሃምሌ 27/2016 ዓ/ም የድምጻዊ ፍቃዱ ዛሀ/ዜዋ/...
03/08/2024

" #ሾንጋም" የድምፃዊ ፍቃዱ ዛሀ/ ዜዋ/የቤንችኛ ባህላዊ የሙዚቃ ስራ ተመረቀ‼
==============================
ሚዛን አማን ሃምሌ 27/2016 ዓ/ም የድምጻዊ ፍቃዱ ዛሀ/ዜዋ/ "ሾንጋም" እና "ጭላጭቴ" የሙዚቃ ቪዲዮ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞን፣ የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የአርቲስቱ አድናቂዎች በተገኙበት በድምቀት ተመረቀ።

የምረቃ ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም እንደገለጹት የፍቃዱ የሙዚቃ ስራዎች ሌሎች የሌላቸውን የእኛ ያለንን ድንቅ ባህል ለሌሎች የሚያስተዋውቅ የሙዚቀኛው የተሰጥኦ ውጤት ነው ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም አካባቢን ለማስተዋወቅ ኪነ ጥበብ ድርሻው ከፍተኛ በመሆኑ ድምፃዊው በኪነጥበብ አካባቢውን እንዲያስተዋውቅ ከተማ አስተዳደሩ መስራቱን ተናግረዋል።ድምፃዊ ፍቃዱ ዛሃ (ዜዋ) ውስጡ ያሉትን እምቅ የኪነ ጥበብ እውቀት ለመጠቀም መደገፍ ከሁሉም እንደሚጠበቅ አቶ ግሩም ገልፀዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪ ተወካይና የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኮይካ በበኩላቸው ድምፃዊው ባህላዊና ዘመናዊን አዋህዶ በመስራት በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል ።

ኪነ ጥበብ ሰዎችን በማስተሳሰር ፣በማቀራረብ፣ በማስተዋወቅ ድርሻው ከፍተኛ በመሆኑ ድምፃዊው በቤንቸኛ ባህል ፣ታሪክ ላይ እየሰራው ያለው ስራ መሆኑን አቶ ጌታቸው ጠቁመዋል።ለሚሰራ እውቅና መስጠት ከስር ለሚወጡት የሚያበረታታ መሆኑን አቶ ጌታቸው ጠቁመዋል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መልካሙ ተክሌ በበኩላቸው ባህል የአንድ ማህበረሰብ የማንነት መገለጫ በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ ከአርቲስት ፈቃዱ ዛሃ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ከ350 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ ፈቃዱ የሙዚቃ ስራውን ለህዝብ እንዲያደርስ በትኩረት ሲሰራ እንደነበር አቶ መልካሙ አክለው ገልጸዋል።

''ሾንጋም'' የቤንችን ብሔር ባህልና ወግ ለአለም የሚያስተዋውቅና ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶ የተሰራ የሙዚቀኛውና የሌሎች አንጋፋ ባለሙያዎች ብቃት የታከለበት ተወዳጅ ሙዚቃ ሲሆን ከሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የተስራ መሆኑ ተጠቁሟል።

ድምፃዊው ከዚህ ቀደም በርካታ ሥራዎችን ለአድማጭ ያደረሰ የአካባቢው ባህል በማስተዋወቅ ፈር ቀዳጅ መሆኑ ይታወቃል።

ድምፃዊ ፍቃዱ ዛሃ (ዜዋ) በበኩሉ የሚዚቃ ሥራው ብዙ ባለሙያዎች ተጠበውበት ለአድማጭ የበቃ መሆኑን ገልጿል።

በሙዚቃው ምረቃ ላይ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ ተረፈ ታደሰ (ካናንስ)፣ የሚዛን አማን ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም ፣የክልል ፣የዞንና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።

ሸገር አዲስ አበባ በሰላም እደሪ
02/08/2024

ሸገር አዲስ አበባ በሰላም እደሪ

11ኛው የሜርቴት ጉሽ ሻሽ  የንግስና ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል ።(ቤ.ሸ.መ.ኮ) ሐምሌ 26/2016 ከቤንች ነገዶች አንዱ የሆነው የሜርቴት የንግስና ስርዓት ባህላዊ የንግስና ስርዓቱን በጠ...
02/08/2024

11ኛው የሜርቴት ጉሽ ሻሽ የንግስና ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል ።

(ቤ.ሸ.መ.ኮ) ሐምሌ 26/2016 ከቤንች ነገዶች አንዱ የሆነው የሜርቴት የንግስና ስርዓት ባህላዊ የንግስና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል።

የንግስና ስርዓቱ በቅርቡ በ119 ዓመታቸው በሞት የተለዩት 10ኛው የሜርቴት ጃሹ ባፌንስን ለመተካት የሚከናወን ሲሆን ሜርቴት ጉሽ ሻሽ 11ኛው ንጉስ በመሆን ይተኳቸዋል ተብሏል።

በንግስና መርሐግብሩ ላይ ታላላቅ የቤንች አባቶች ፣ የክልል ፣ የዞንና የሰሜን ቤንች ወረዳ አስተዳደር እና የካቢኔ አባለት ፣ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ቀሪ የንግስና ባህላዊ ስርዓቶቸ በቅርቡ የሚጠናቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

👉 #ሾንጋም የቤንችኛ ባህላዊ የሙዚቃ አልበም ከሐምሌ 27-28/2016 ዓ/ም በታላቅ ድምቀት ይመረቃል :: ፕሮግራሞቹም :>>ቅዳሜ ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበ...
01/08/2024

👉 #ሾንጋም የቤንችኛ ባህላዊ የሙዚቃ አልበም ከሐምሌ 27-28/2016 ዓ/ም በታላቅ ድምቀት ይመረቃል ::
ፕሮግራሞቹም :>>ቅዳሜ ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አልበሙ በይፋ ይመረቃል::
>>እሁድ ቀኑን ሙሉ የባህላዊ ዜማው ኮንሰርት ለአድናቂያንና ለታዳሚያን በሙሉ ይቀርባል ::
ድምፃዊ ፍቃዱ ዘሃ(ዜዋ) በቤንችኛ በማቀንቀን ብሔሩ በሰፊው እንዲተዋወቅ በማድረግ ሰፊ ስራ በመስራት በታሪክ ሊፃፍ የሚችል ታላቅ አሻራ እያኖረ ያለ ተወዳጅ የቤንች ብሔር ድምፃዊ ነው::
መላው የቤንች ሸኮ ዞን ማህበረሰብና በአጎራባች ዞኖች የምትገኙ #የፍቄ አድናቂዎች #ሾንጋም በተሰኘው በአይነቱና በአቀራረቡ ለየት ባለ የባህላዊ ዜማ የአልበም ምረቃ ላይ እንድትገኙ በክብር ተጋብዘዋል‼
coming soon....💝

የተፈጥሮ ሀፈት
25/07/2024

የተፈጥሮ ሀፈት

ከጅማ ወደ ሚዛን የሚወስደው መንገድ በለጠ ጫካ ከባድ ጥንቃቄ ይፈልጋል ሼር አድርጉ ።Godina Jimmaa Aanaa Shabee Sombootti Daandiin Haala Suuraa Irratti...
24/07/2024

ከጅማ ወደ ሚዛን የሚወስደው መንገድ በለጠ ጫካ ከባድ ጥንቃቄ ይፈልጋል ሼር አድርጉ ።
Godina Jimmaa Aanaa Shabee Sombootti Daandiin Haala Suuraa Irratti Argaa Jirtaaniin Caccabee Waan Jiruuf of eeggannoo gochuun darbuu qabdu.
Waliif share godha.

ከጅማ ወደ ሚዛን የሚወስደው መንገድ በለጠ ጫካ ከባድ ጥንቃቄ ይፈልጋል ሼር አድርጉ
አደጋ እንዳይደርስ

Address

Mizan Tapi
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mizan tappi city posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category