09/01/2025
እጅግ ቀላል አረዳድ ስለገንዘብ
ሁሉም ሰው ብዙ ገንዘብ ሲያገኝ ሀብታም እንደሚሆን አምኗል:: ደምድሟል:: በልጅነታችን በንጹሕ አዕምሮ ደግሞ የገንዘብ ኖት የሚያትመው ሰውዬ እንቀናበታለን:: ብዙ ብር አትሞ ያሻውን መግዛትና ሀብታም መሆን እንደሚችል ስናስበው በጣም እንጓጓለን::
ወደ ዕውነታው ስንመጣ
አንደኛ:- ብዙ ብር ማተም ደሃ ያደርጋል:: ኑሮን ያመሰቃቅላል:: ስለዚህ ገንዘቡ ገንዘብ አይደለም ማለት ነው:: ብዙ ቢታተም ሀብታም ካላደረገና ኑሮን ካንበጫበጨ ገንዘብ ነው ብለን ቋሚ ፍርዶችን ልንፈርድበት አንችልም:: 1952 ላይ ሰውን የገደለ 40,000 ብር ከነበረ 2012 ላይ 40,000 ብር የበሬ ዋጋ ነው የሆነው:: ወርቅ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ግን ሚዛኑን እንደጠበቀ ይሄድ ነበር:: ስለዚህ የእኛ ብር ከላዩ ሌላ ብር (ዶላር) ስላለበት የእኛ ገንዘብ, ገንዘብ አይደለም::
ሁለተኛ:- ገንዘብ የሚያትመው የመጨረሻው "ሰውዬ" አሜሪካ ነው ያሉት:: 12 ናቸው:: እነርሱ በዶላር ያሻቸውን ነገር ቀርቶ አሕጉር ይገዛሉ:: ስለዚህ ሀብታም ናቸው:: ስለዚህ የልጅነታችን የጅል ጥያቄ ትክክል ነው ማለት ነው:: ሆኖም ግን የዓለም ሁሉ ሕዝብ ወደዚህኛው ሲስተም ስለገባ የባርነት ኑሮ ይኖራል:: ፕሮፌሰር ዶክተር ኢንጂነር ቢሆን እንኳ ደሃ ነው:: ምክንያቱም ሲስተሙ ፌክ ነው:: ጀንዊን ሰው ፊኩ ሲስተም ላይ መኖር አይችልም:: ወይ ሰውየው ወይ ሲስተሙ ይሰበራሉ::
በነገራችን ላይ አንድ መሥሪያ ቤት ሄዳችሁ ማናጀሩ ከሌለ ሥራ አይቆምም:: አካውንታንት ከሥሬ ቢቀር ሌላው ክፍል ይቀጥላል:: ሲስተም ከሌለ ግን ሙሉ ሠራተኛ ቢገባ እንኳ ሲስተም ከገገመ ወይም ከተበላሸ ሁሉም ነገር ይበላሻል::
ስለገንዘብ ስብሰባ ከማሰባችሁ በፊት ሲስተሙን አስቡት:: እንዴት ነው የሚሠራው? እንዴትስ ነው የማይሠራው? የሚለው ተቀዳሚ ጥያቄ ነው:: Naturally በንጹሕ አዕምሮ የምትጠይቁት ጥያቄ ትክክል ነው:: እርሱኛውን ከመለሳችሁ ቁልፉን አግኝታችሁታል::
source hassen enjamo