ADWA MIDYA አድዋ ሚዲያ

ADWA MIDYA አድዋ ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ADWA MIDYA አድዋ ሚዲያ, Grocers, አዲስ አበባ ኢትዮጵያ, Addis Ababa.

ይመልሱ ! ይሳተፉ ! በ5 ሄክታር ላይ የተንጣለለው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ስንት መግቢያ በሮች አሉት? መግቢያ በሮቹ ስያሜያቸው ምን ይባላል?  ይመልሱ ! ይሳተፉ !
23/02/2026

ይመልሱ ! ይሳተፉ !

በ5 ሄክታር ላይ የተንጣለለው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ስንት መግቢያ በሮች አሉት? መግቢያ በሮቹ ስያሜያቸው ምን ይባላል? ይመልሱ ! ይሳተፉ !

21/11/2025

የዕጩ ምዝገባን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ

ቦርዱ ኅዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባስተላለፈው ጥሪ፤ ፖለቲካ ፓርቲዎች “ቦርዱ ያበለጸገውን ሲስተም” ተጠቅመው ዕጩዎቻቸውን ለመመዝገብ እንዲችሉ “በቅድሚያ” ከጥሪው ጋር የተያያዙትን ቅጾች በመጠቀም የተጠየቁትን መረጃዎች አሟልተው ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።

የዕጩ ምዝገባ የሚከናወንበት አግባብ እና የቅጾች አጠቃቀም

1. የፖለቲካ ፓርቲ ቦርዱ ያበለጸገውን የዕጩ መመዝገቢያ ሲስተም ተጠቅሞ ዕጩ ለመመዝገብ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና የዕጩ ምዝገባ መመሪያ መሠረት በቅድሚያ የዕጩ ዝርዝር ማቅረቢያ ቅጽ አምስትን በመጠቀም የዕጩዎችን ዝርዝር መረጃ፤ የፓርቲውን ሊቀ-መንበር ሦስት የፊርማ ናሙና እና የመወዳደሪያ ምልክቱን ለቦርዱ አስቀድሞ ባሳወቀው ወኪል አማካኝነት ከኅዳር 8 እስከ ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ለቦርዱ በአካል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

2. ቅጽ አራትን በመጠቀም የፖለቲካ ፓርቲው ከፍ ብሎ በተራ ቁጥር አንድ ላይ የተመለከቱት ሠነዶች በሙሉ የተሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ እና መጠይቁ ላይ ምልክት በማድረግ ለቦርዱ አስቀድሞ ባሳወቀው ወኪል አማካኝነት ከኅዳር 8 እስከ ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ለቦርዱ በአካል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

3. የፖለቲካ ፓርቲው የዕጩ የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ ወጥነት እንዲኖረው ቦርዱ ያዘጋጀውን ቅጽ ሦስትን በመጠቀም መረጃ በማሰባሰብ በዕጩ መመዝገቢያ ሲስተም ላይ የሚጫን ሲሆን፤ ይኽም የሚከናወነው በምርጫው የጊዜ ሠሌዳው መሠረት ቦርዱ ወደፊት በሚያሳውቀው የዕጩዎች የምዝገባ ጊዜ፤ ፓርቲው በወከለው ባለሙያ አማካኝነትና በፖለቲካ ፓርቲው ጽ/ቤት ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ኅዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም.

21/11/2025
21/11/2025
09/11/2025

በአንድ ስልክ ቁጥር ከአንድ በላይ ሰው ቢመዘገብና ፣ የፋይዳ ልዩ ቁጥር ባይደርስ ምን ማድረግ ይቻላል?

በ*9779 # ደውሎ "1"ን በመጫን በስልክ ቁጥርዎ ላይ የተደረጉ ሁሉም ምዝገባዎች የፋይዳ ቁጥር ይደርስዎታል::

በዚህ መንገድ ካልደረስዎ ደግሞ በ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ በመግባት "መግቢያውን እለፍ" የሚለውን በመቀጠልም "የፋይዳ ቁጥር ያስልኩ" የሚለውን በመንካት የምዝገባ ቁጥርዎን በመጠቀም የፋይዳ ቁጥርዎን ማስላክ ይችላሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳለሁሉም #ፋይዳመታወቂያ

09/11/2025

የኒውክሌር ኃይል ለማመንጨት የተጀመረው ሥራ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተደማጭነት ያሳድጋል
+++++++++++++++++++

| ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ለማመንጨት የጀመረችው ሥራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተደማጭነት ከፍ ለማድረግ እንደሚያስችል የኒውክሌር ፊዚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተስፋዬ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ኮምፒውቴሽናል ሳይንስ የኒውክሌር ፊዚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተስፋዬ (ዶ/ር) ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኢነርጂ ወደ ማበልፀግ መግባቷ በአጠቃላይ በዓለም ላይ ያላትን ተደማጭነት ከፍ ያደርገዋል፡፡
እስካሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ በኒውክሌር ልማት ላይ ያተኮሩ ስብሰባዎችን ተካፍሎና ተመልክቶ ከመምጣት ያለፈ ሚና አልነበራትም ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤ አሁን ላይ ግን ኒውክሌር የማበልፀግ ተስፋ ሰጭ የጅማሮ ምዕራፍ ላይ ነች ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ደረጃ ደቡብ አፍሪካ የራሷን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ መገንባቷንና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከሚመረተው ኃይል አምስት በመቶው የሚሆነው ከኒውክሌር የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ በከፍተኛ ደረጃ የረዳትና በዘርፉ በአፍሪካ ደረጃ መሪ ያደረጋት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያም የኒውክሌር ኃይል ወደ ማበልፀግ መግባቷ በምሥራቅ አፍሪካ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከፍ እንደሚያደርገው አመልክተው፤ በተለይም በአካባቢው የሳይንስና የቴክኖሎጂ መሪ እንድትሆን አቅም ይፈጥርላታል ብለዋል፡፡

ሀገሪቷ በቀጣናው የኃይል ምንጭ ሆና እንድትቀጥልም ዕድል ይፈጥራል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኒውክሌር ኃይል ልማት አስተማማኝ የሆነ የኃይል ምንጭ እንዲኖር ያስችላል ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤ በተለይም በኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት በመቀነስና ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው አመልክተዋል፡፡

ሀገሪቱ በየዓመቱ ለነዳጅ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ በመታደግ ረገድም የላቀ አበርክቶ እንደሚኖረው በመጠቆም፤ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠርና በዘርፉ የሠለጠነ ኃይል ለማፍራት የሚያስችል እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

በማሕሌት አብዱል
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ _ ፕላስ # ኒውክሌር # ኢትዮጵያ

09/11/2025
24/08/2025
01/08/2025

Address

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ADWA MIDYA አድዋ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category