FETU Ya Abate page ፈቱ አበታ

FETU  Ya Abate page  ፈቱ አበታ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FETU Ya Abate page ፈቱ አበታ, Grocers, Halaba, Addis Ababa.

20/01/2026
14/12/2025
27/10/2025
27/10/2025
‎ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ‎‎(አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12/ 2018 ዓ.ም) የሴቶች ኢኮኖሚ ማብቃት ብሔራዊ ስትራቴጂ ዝግጅት ላይ የግብ...
22/10/2025

‎ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ

‎(አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12/ 2018 ዓ.ም) የሴቶች ኢኮኖሚ ማብቃት ብሔራዊ ስትራቴጂ ዝግጅት ላይ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ነው።

‎በመድረኩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ኸይረዲን፥ መንግስት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ማካሄዱን ተከትሎ ለውጦች መመዝገባቸውንና በሂደቱም የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

‎በተካሄደ ሰፊ የንቅናቄ ስራ በህብረት ስራ ማህበራት የተደራጁ ሴቶች ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ መቆጠብ መቻላቸውን ገልፀዋል።

‎የገጠር ሴቶች በተናጠልና በጋራ በመሆን ግብርናን ማዕከል ባደረጉና በሌሎችም መስኮች በመሰማራት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛል ብለዋል።

‎ይሁንና አሁንም የብድር፣ የዋስትና፣ የመስሪያ ቦታ፣ የክህሎትና መሠል ችግሮች መኖራቸው ለሴቶች የኢኮኖሚ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ ማነቆ ስለመሆናቸው አንስተዋል።

‎ሚኒስቴሩ የሴቶች ፖሊሲ ክለሳ እና የስርዓተ ፆታ እኩልነትና ማብቃት ፖሊሲ ዝግጅትን እየተጠናቀቀ መሆኑንና ሌሎች ደጋፊ የአሰራር ማዕቀፎች እንዲቀረፁና በስራ ላይ እንዲውሉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

‎ዩኤን ውመን/UNWOMEN/ በሴቶች የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ ፎረም ከማቋቋም በተጨማሪ ለስትራቴጂው ዝግጅት ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል።

‎ስትራቴጂው እንደሀገር የሴቶች የኢኮኖሚ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት እና የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን የበኩሉን አገዛ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልፀው ለተግባራዊነቱ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

‎የዩኤን ውመን ኢትዮጵያ ሀገራዊ ፕሮግራም ተወካይ ሚስተር ሻድራክ ዱሳቤ በበኩላቸው፥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሴቶች መብት መከበር፣ ለስርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ለማብቃት የተጓዘውን ርቀትና የተገኘውን ውጤት አድንቀዋል።

‎በቀጣይም ዩኤን ውመን ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በጋራ እንደሚሰራና ድጋፍም እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

22/10/2025
21/10/2025
15/10/2025
የታክስ ህጎች ተገዢነትን ለማረጋገጥ ከፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ የቁሊቶ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ።ጥቅምት 05/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶየታክስ ህጎች ተገዢነትን ለማ...
15/10/2025

የታክስ ህጎች ተገዢነትን ለማረጋገጥ ከፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ የቁሊቶ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ።

ጥቅምት 05/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

የታክስ ህጎች ተገዢነትን ለማረጋገጥ ከፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

የውይይት መድረኩን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ም/ከንቲባ እና የገቢ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲልቃድር ኢማም ሎላሶ መርተዋል።

የገቢ አሰባሰብን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት የቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ እንደሆነ አቶ አብዲልቃድር ኢማም ሎላሶ ገልጸዋል።

በከተማው አዲሱን የገቢ ግብር ህጎችን ማሻሻያ ተከትሎ ግብር ከፋዮች ግዴታቸዉን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል የህግ ግንዘቤ ሥራ በስፋት እየተሰራ መሆኑን አቶ አ/ቃድር ገልፀው ህገወጥ ተግበራት ላይ የሚገኙ አካላት ላይ ጠንካራ ህግ ማስከበር ሥራ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

ያለህግ ማስከበር የገቢ አሰባሰብ ውጤታማነት አስቸገር በመሆኑ የፍትህ ተቋማት በህግ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ ልወጡ እንደሚገባ ነው የገለጹት።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የፖሊስ፣ የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም የፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊዎችም በከተማ ጠንከራ የህግ የመስከበር ሥራ በመስራት የገቢ አቅማችንን ለማሳደግ በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም ተቋማቱ በቅንጅት ለመስራት በሚያስችላቸው ሥራዎች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመው የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Address

Halaba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FETU Ya Abate page ፈቱ አበታ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category