Ameya City Prosperity Party Branch Office

Ameya City Prosperity Party Branch Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ameya City Prosperity Party Branch Office, Grocers, Ameya, Addis Ababa.

የመንግስትን እና የፓርተውን ተግባር በብቃት በመወጣት ከወረዳ ወደ ዞን ማዕከል በሹመት ለወጡ የሥራ ኃላፊዎች ሽኝት ተደረገላቸው።የኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ መንግስት በክብር ከወረዳ አመራ...
08/06/2026

የመንግስትን እና የፓርተውን ተግባር በብቃት በመወጣት ከወረዳ ወደ ዞን ማዕከል በሹመት ለወጡ የሥራ ኃላፊዎች ሽኝት ተደረገላቸው።

የኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ መንግስት በክብር ከወረዳ አመራርነት ወደ ዞን አመራርነት ለተቀላቀሉ አመራሮች የሽኝት መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የቀድሞ የአመያ ዙሪያ ወረዳ ም/አስ/ሪና የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢዮብ ስለሽ እና የወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ማሬ በቀለ የክብር አሸናኘት ተደርጓላቸዋል።

በሽኝት መርሃ ግብር ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ዋና አስ/ር አቶ ወንድማገኝ ኡቴ ጠንካራ አመራር ሆነው መንግስትንና ሕዝብን በትጋት በማገልገል በተግባር ውጤታቸው ወደ ዞን አመራር ሆነው በመሄዳቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው መልካም የሥራ ጊዜ እንድሆንላቸውም ተመኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የዞኑ ም/አስ/ሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ወጁ ሽኝት የተደረገላቸው አመራሮች በወረዳው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ህዝቡን በቀናነት ሲያገለግሉ በመቆየታቸው ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም መንግስት አምኖ የሰጣቸውን አደራ በበለጠ ትጋት ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመጨረሻም በክብር ለተሸኙ አመራሮች የወረዳው አስተዳደር ስጦታ በማበርከት የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።

በመድረኩም የዞኑ ም/አስ/ሪና የገብዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ወጁ ፣ የወረዳው ዋና አስ/ር አቶ ወንድማገኝ ኡቴ ፣ የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሻግሬ አለማየሁ፣የዞኑ ደጋፊ አመራሮች፣ የወረዳው ስራ አስፈፃሚዎች እና ፑል አመራሮች በተገኙበት የሽኝት ሥነ-ስርዓት ተደርጓል።

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህልውና የተረጋገጠበትና ተጨባጭ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የተንፀባረቀበት ነው፤ አቶ ነጋ አበራበ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የታየው የህዝብ ተሳትፎና የባለድር...
07/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህልውና የተረጋገጠበትና ተጨባጭ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የተንፀባረቀበት ነው፤ አቶ ነጋ አበራ

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የታየው የህዝብ ተሳትፎና የባለድርሻ አካላት ሚና በሀገሪቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ማካሄድ ማስቻሉም ተገልጿል።

በኮንታ ዞን በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የግምገማና የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ከቅድመ ምርጫ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ የተሰሩ ተግባራት ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪና ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሀገሪቱ ብሎም በዞኑ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ነፃ እንዲሆን እና በብልፅግና ፓርቲ አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም የህዝብ ተሳትፎ ከፍ እንዲል ግብ ተጥሎ ሲሰራበት እንደነበር ገልፀዋል።

በተለይም ምርጫውን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህልውና የተረጋገጠበትና ተጨባጭ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የተንፀባረቀበት እንዲሁም የተቀመጡ ዕቅዶች ተሳክተው የሚጠበቀው ውጤት የተመዘገበበት እንደሆነ አስረድተዋል።

የተሰጠው የህዝብ ድምፅ ከፍተኛ ኃላፊነት በመሆኑ ይህንን ቅቡልነት በስራ ማረጋገጥና ተስፋውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የትብብር መንፈስ ማጠናከር፣ በአጠቃላይ አመራሩና ህዝቡ ከምርጫ ማግስት ወደ መደበኛ የስራ እንቅስቃሴ በመግባት በትጋት መስራትና በውጤት መለካት እንደሚያሻ አስገንዝበዋል።

አክለውም ለምርጫው ስኬት የጎላ ድርሻቸውን ለተወጡ አመራር አካላት፣ ባለድርሻ አካላትና ለመላው ህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ በዞኑ ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ሰፊ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን ገልፀው በምርጫው ዜጎችና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለስኬቱ ያሳዩት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል።

በምርጫው ሂደት ላይ ካጋጠሙ ተግዳሮቶችና ከተገኙ ስኬቶችን እንዲሁም ከታዩ ተሞክሮዎች ለቀጣይ ሰፊ ልምዶች የተገኙበት ነው ያሉት አቶ ታከለ ከተሰጠው ድምፅ መነሻ በየአካባቢው ጉድለቶችን ለቅሞ መስራት ይገባል ብለዋል።

በቀጣይም ህዝቡ በሰጠው ዕድልና አደራ ልክ በየደረጃው የሚገኘው አመራር ህዝቡን በማስተባበር የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማጠናከር የላቀ ውጤት በማስመዝገብ መካስ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪና ብልፅግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ በሀገሪቱ ብሎም በዞኑ ሀገራዊ ምርጫውን ለማሳካት መንታ ግቦች ተጥለው ወደ ስራ መገባቱን አመላክተው በዋናነት ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ነፃ እንዲሆን እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ሰፊ ስራዎች ተሰርተው በስኬት ተጠናቋል ብለዋል።

ከምርጫው ሰፊ ልምድና ትምህርት የተገኘበት በመሆኑ በቀጣይ ከልማት ባሻገር ህዝብን በተገቢው ማዳመጥ ይገባል ያሉት አቶ ገዛኸኝ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተሰራው ስራ የተሻለ ተግባር ማከናወን መቻሉንም አክለዋል።

ከምርጫ ስራ ጎን ለጎን የልማትና የፀጥታ ስራዎች በየደረጃው በተደራጀ ሁኔታ ሲመሩ እንደነበረ አውስተው ይህንንም በተጀመረው ልክ በበለጠ አቅም አጠናክረን መምራት ይገባናል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ አመራር አካላት ምርጫው ሰፊ ልምዶች የተወሰዱበት እንዲሁም የፖለቲካ ስነ-ምህዳር በማስፋትና ምቹ በማድረግ የዴሞክራሲ ልምምድ በተግባር የታየበት እንደሆነ ተናግረዋል።

በከተማው ዘንድሮ በመኸር ወቅት 55 ሄ/ር መሬት ላይ 1 መቶ 137,500 ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው  ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ ‎‎በኮንታ ...
06/06/2026

በከተማው ዘንድሮ በመኸር ወቅት 55 ሄ/ር መሬት ላይ 1 መቶ 137,500 ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ

‎በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ በ2018 ዓ.ም በመኸር ወቅት 55 ሄ/ር መሬት ላይ 137500 ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፓፓያ፣ ግራብል፣ ጽድ፣ ቡና፣ እንሰትንና ሌሎች ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጸዋል።

‎የአመያ ከተማ አስተዳደር ግብርና፣ ኢንተርፕራይዝ፣ ህብረት ስራ፣ መንገድ ትራንስፖርት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ወዳጄ እንደገለፁት ባለፉት ዓመታት በከተማው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መከናወን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንደተገኙበት ተናግረዋል ።

‎ደንን ጨምሮ ሌሎች ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ የተከላው አካል መሆናቸውን የገለፁት ስሆን እንደ ከተማ አስተዳደሩ 137,500 ችግኝ ተከላ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ ስለመሆኑን ጠቁመዋል።

‎እየተዘጋጁ ያሉ ችግኞች አረንጓዴ ኢኮኖሚን ከመገንባት ባለፈ የአካባቢን ስነ-ምህዳር ለመጠበቅ ከፍተኛ ድርሻ ይኖራቸዋል ያሉት አቶ ወንድማገኝ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚያግዙና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ላላቸው ችግኞች ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።

‎በወቅቱ በመንግስት ድጋፍ ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስኬታማነት አስፈላጊ የሆኑ ችግኞችን የማፍላትና ለተከላ የማዘጋጀት ስራ በከተማ አስተዳደራችን በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

‎ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በኮንታ ዞን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አፈፃፃም ላይ ያተኮረ የዞን አመራር አካላት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።ምርጫው ከቀደሙት ምርጫዎች የተለየና ሰፊ ልምዶች የተወሰዱበት እንደሆነ ተገልጿል።በዞ...
05/06/2026

በኮንታ ዞን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አፈፃፃም ላይ ያተኮረ የዞን አመራር አካላት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ምርጫው ከቀደሙት ምርጫዎች የተለየና ሰፊ ልምዶች የተወሰዱበት እንደሆነ ተገልጿል።

በዞኑ የፖለቲካ ስነ-ምህዳር በማስፋትና ምቹ በማድረግ የዴሞክራሲ ልምምድ በተግባር የታየበት እንደሆነም ተነግሯል።

በመድረኩ በዞኑ የሚገኙ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር እና የሶስት ወረዳዎች የምርጫ ስራ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እስከ ድህረ ምርጫ የሚሰሩ ተግባራት ዕቅዶች ወጥተው ሲተገበሩና እንደብልፅግና ፓርቲ መንታ ግቦች ተጥለው ሲሰራ እንደነበረ ቀርቧል።

መድረኩን የመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ፣ የጎላ የህዝብ ተሳትፎ የታየበትና ከተፎካካሪ ፓርቲዎችና ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረው ቅንጅታዊነት ውጤታማ ስራ የተሰራበት እንደሆነ ገልፀዋል።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ለማጠናከርና የተጀመረው ሀገረ መንግስት ጎልብቶ እንዲሄድ የተደረገው ስራ ልምድ የሚወሰድበት ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ነፃ እንዲሆን የተጣለው ግብ በሁሉም ደረጃ መሳካቱን ገልፀዋል።

በቀጣይም በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በማተኮር መስራት እንደሚገባ በመግለፅ ለምርጫው ውጤታማነት የጎላ ድርሻቸውን ለተወጡ አመራር አካላት፣ ለፀጥታው መዋቅሮችና ለመላው ዞኑ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ እንዲሆን በመንግስትና በፓርቲ ቅንጅት ግብ ተጥሎ በተሰራው ስራ ውጤት መገኘቱ አስረድተዋል።

በዘንድሮ ምርጫ ለሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹ የመወዳደሪያ ምህዳር ከመፍጠር ጀምሮ በየደረጃው የሚገኘው መራጩ ህዝብ በምርጫው ተሳታፊ እንዲሆን በተሰራው ስራ የተሻሉ ተግባራት ስለመፈፀማቸው አክለዋል።

በሂደቱም ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እየተወያዩና መፍትሄ እየሰጡ ማሳካታቸውን አንስተው በቀጣይም ህዝቡን በተገቢው እያዳመጡ የሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች በሚመለሱበት ሂደት ላይ ማተኮር ይገባናል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙ አመራር አካላት ምርጫው ከቀደምት ምርጫዎች የተለየና ሰፊ ልምዶች የተወሰዱበት እንዲሁም የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋትና ምቹ በማድረግ የዴሞክራሲ ልምምድ በተግባር የታየበት እንደሆነ ተናግረዋል።

ምርጫው አመራሩና አባሉ ለፓርቲ ያለውን ውግንና ያሳየበት እንዲሁም መራጩ ህዝብ የተሰሩትንና ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮችን በድምፁ የጠቆመበት እንደሆነ አንስተዋል።

በቀጣይም ህዝቡ በሚያነሷቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት፣ ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት መገንባት፣ የመንግስት አገ/ሎት አሰጣጥ ማሻሻል፣ የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ማሳደግ እና መሠል ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመድረኩ የዞኑ ስራ አስፈፃሚዎችን ጨምሮ አጠቃላይ የዞኑ ፑል አመራር አካላት ተገኝተዋል።

ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

🙏የኮንታ ሕዝብ ለውድ ልጆቹ የሰጠው ድምጽ የታላቅ እምነት ምልክት ነው🙏ኮንታዎች ለቃላቸው ታማኝ ናቸው! ይህንም በምርጫው አስመስክረዋል።የ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በኮንታ ልዩ ምርጫ ክልል...
05/06/2026

🙏የኮንታ ሕዝብ ለውድ ልጆቹ የሰጠው ድምጽ የታላቅ እምነት ምልክት ነው🙏

ኮንታዎች ለቃላቸው ታማኝ ናቸው! ይህንም በምርጫው አስመስክረዋል።

የ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በኮንታ ልዩ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የክልል ምክር ቤት ውጤት ይፋ ሆነ።

በዚህ መሠረት ብልጽግና ፓርቲ በኮንታ ልዩ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎችን በከፍተኛ ድምጽ አሸንፏል።

የኮንታ ሕዝብ ሁሌም ለቃላቸው ታማኝ ናቸው፤ ቃላቸውንም በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በተግባር አስመስክረዋል።

በምርጫው ሕዝቡ ለፓርቲያቸውና ለሚወከላቸው ሕዝብ ድምጻቸውን በመስጠት ታሪካዊ ተሳትፎ አሳይተዋል።

 በአመያ ከተማ አስተዳደር የኢዜማ ፓርቲ የምርጫ ምልክት  ወረቀት  የቀደደው ግለሰብ በ3 ወር የቀላል እስራት ተቀጣ።ተከሳሸ አቶ አሰፋው ጋሞ አልታዬ የተባለዉ ግለሰብ በግንቦት 11/9/201...
05/06/2026



በአመያ ከተማ አስተዳደር የኢዜማ ፓርቲ የምርጫ ምልክት ወረቀት የቀደደው ግለሰብ በ3 ወር የቀላል እስራት ተቀጣ።

ተከሳሸ አቶ አሰፋው ጋሞ አልታዬ የተባለዉ ግለሰብ በግንቦት 11/9/2018 ዓ.ም ዕለተ ማክሰኞ በግምት ከጠዋቱ ሁለት ስዓት በሚሆንበት ጊዜ በአመያ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ውስጥ ልዩ ስም ሆስፒታል ሰፈር ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ተከሳሹ የኢዜማ ፓርቲ የምርጫ ምልክት በመቅደድ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ተከሳሸ በ3 ወር የቀላል እስራት እንዲቀጣ የአመያ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።

የአመያ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግንቦት 28/9/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አቶ አሰፋው ጋሞ አልታዬ የምርጫ ምልክት በመቅደድ የፈጸመው ድርጊት በዐ/ህግ ማስረጃ በመረጋገጡ ተከሳሹ ራሱን የመከላከል መብት ቢሰጠውም ችሎት የቀረቡ 3 የመ/ምስክሮች ምንም አናዉቅም፣ አላየንም፣ አልሰማንም የፍ/ቤት መጥርያው ስለደረሰን መጥተናል ብለዉ መስክረው የተመለሱ በመሆናው የዐ/ህግ ምስክሮቹን ቃል ባለማስተባበላቸው ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ነው በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል።

እንደ ፍርድ ቤቱ መግለጫ ከሆነ ተከሳሹ ጥፋተኛ የተባለው በኢትዮጵያ የምርጫ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 158 ሥር የተደነገገውን የተከለከለ ተግባር በመጣሱ ነው።

ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ቅጣቱ ተከሳሹን የሚያርምና ሌሎች መሰል ድርጊት ከመፈጸም እንዲቆጠቡ ትምህርት የሚሰጥ መሆን አለበት በማለት የ3 ወር የቀላል እስራት ቅጣት መወሰኑን አስታውቋል።

ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በአግባቡ የተጠቀሙበት ነበረ - ከንቲባ ተመስገን ደጄኔ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የማጠቃለያ ግምገማ መድረክ...
04/06/2026

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በአግባቡ የተጠቀሙበት ነበረ - ከንቲባ ተመስገን ደጄኔ

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የማጠቃለያ ግምገማ መድረክ የዞኑ ደጋፊ አመራሮችና የከተማው ፑል አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

ምርጫው ከዝግጅት ጀምሮ እስከ ድምፅ አሰጣጥ ፍፃሜ ድረስ ባለው ሂደት የፀጥታ መዋቅሩ፣ የከተማው አመራሮች፣ ደጋፊ አመራሮች እንዲሁም የየአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ተመስገን ደጄኔ እንደገለጹት በከተማው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሂደት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጀምሮ በስኬት መጠናቀቁን ገለጸው ለዝህ ስኬት ርብርብ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

አያይዘውም አመራሩና ህዝቡ በምርጫው ወቅት ያሳዩትን ይሄንን ከፍተኛ ርብርብ በቀጣይ በመልካም አስተዳደርና በልማት ስራዎች ላይም ሊደግሙት እንደሚገባ አጭር ሀሳብ በመስጠት የ‹‹እንኳን ደስ አላችሁ›› መልዕክት አስተላልፈዋል ከንቲባው።

የዞኑ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ብርሃኑ አቱሞ በበኩላቸው ለምሬጫው መሳካት የድርሻቸውን የተወጡ አካላትን ያመሰገኑ ሲሆን በተለይ መራጩ ህዝብ የሚፈልገውን ለመምረጥ ድምፁን በነፃነት መጠቀሙ የዜግነት ኃላፊነትን በተግባር የተወጣ መሆኑን ያሳያልም ብለዋል።

አመራሩ ሀገር ለማፅናትና ቀጣይ ተግባራትን በታማኝነትና በትጋት ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በላይ በልዩ ቁርጠኝነት መስራት እንደሚያፈልግ የገለፁት አፈጉባኤ ህዝቡን በትጋትና በትህትና ማገልገልና የህብረተሰቡን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የከተማው የብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ወንድሙ ዋጌ እንዳሉት ለዚህ ስኬት ዋጋ የከፈሉ አመራሮችን ጨምሮ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ውርጭና ብርድ እንዲሁም ፀሃይ ሳይበግረው ድምፅ መስጠቱን አመስግነዋል።

ስኬቱም በአመራሩ በላቀ ርብርብና ቁርጠኝነት እንዲሁም በህዝባችን በሰለጠነ የፖለቲካ ባህል መሆኑን ተናግረው አመራሩ ምንም አይነት ተግዳሮቶች ሳይበግር የተኛውንም ተልዕኮ ማሳካት የሚያስችል አቅም ማሳየት የተቻለበት ተልዕኮ መሆኑንም ገልጸዋል።

የከተማው የመንግስት ረ/ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሩ ሳሙኤል ባለፉት በምርጫ ወቅት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት የምርጫው ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን አመራሮች ትልቁን ድርሻ መወጣት መቻሉን አንስተው በአጠቃላይ ለስኬቱ የበኩላቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አያይዘውም ከተቋም ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድርስ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን በተቀመጠ ጊዜ ገደብ አመራሩ በውጤታማነት መምራት እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ታምሩ አመራሩ ህዝብ የሚያነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በጥሞና በማዳመጥ ደረጃ በደረጃ ምላሽ እንዲያገኝ በልዩ ርብርብ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

በመድረኩ ላይ የምርጫ ሂደቱን አፈፃፀም የተገኙ ውጤቶችን እና የታዩ ተሞክሮዎችን በተመለከተ ዝርዝር ውይይት ተደርጎ በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።

ምክር ቤቱ የአየር አገልግሎት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀግንቦት 27 /2018 ዓ.ም 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ  በካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባው ኢትዮጵ...
04/06/2026

ምክር ቤቱ የአየር አገልግሎት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ

ግንቦት 27 /2018 ዓ.ም

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ በካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባው ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያደረገቻቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡

የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ፈትሂ ማሕዲ ( ዶ/ር ) የአየር አገልግሎት ስምምነት ረቂቅ አዋጆችን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳቦች ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

የአየር አገልግሎት ስምምነት ረቂቅ አዋጆቹ ኢንቨስትመንትን በማሳብና የአየር ትራንስፖርት መዳረሻዎችን በማስፋት ለአገራችን የአየር ትራንስፖርትና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያላቸውን ሚና ወሳኝ መሆኑን ምክትል ሰብሳቢው አስረድተዋል፡፡

ከአየር አገልግሎት ስምምነቶቹ መካከል በኢትዮጵያ መንግሥትና እና በሴራሊዮን ሪፐብሊክ መንግሥት በኩል የተፈረመው አንዱ ሲሆን ስምምነቱ ለአየር መንገዶች ወደ ተመረጡ መዳረሻዎች በቀጥታ ለማረፍና ምቹ የአቪዬሽን አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የህን የአየር አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ምክር ቤቱ አዋጅ ቁጥር 1417 /2018 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በመቀጠል በአንጎላ ሪፐብሊክ ፤ እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል የተፈረመው የአየር አገልግሎት ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን ስምምነቱ በአገራቱ መካከል ያለውን ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ግንኙነት ለማሳደግ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የተከበሩ ፈትሂ ማሕዲ( ዶ/ር ) አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ ይህን ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1418 /2018 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በባንግላዲሽ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መካከል የተደረገው የአየር አገልግሎት ስምምነት በአገራቱ መካከል እያደገ የመጣውን የአየር ትራንስፖርት ፍሰት ከግምት ያስገባ መሆኑን ምክትል ሰብሳቢው የተከበሩ ፈትሂ ማሕዲ( ዶ/ር ) ገልፀዋል፡፡

የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስመንት ለመሳብ ፣ በንግድና ቱሪዝም እና የውጪ ምንዛሬ ለአገራችን በማስገኘት ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ ይህን ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1419/ 2018 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ሌላው በምክር ቤቱ የጸደቀው የአየር አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኢስዋቲኒ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት መካከል የተደረገው ስምምነት ሲሆን ያለ በረራ ድግምግሞሽ ገደብ የጭነት በረራዎችን ማከናወን ጨምሮ ለበረራ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማስገባትን የሚያካትት በመሆኑ የበረራ ወጪን እንደሚቀንስ የተከበሩ ፈትሂ ማሕዲ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ምክር ቤቱ ይህን ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1420/ 2018 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በአጠቃላይ የአየር አገልግሎት ስምምነቶቹ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስጠብቁና በዘርፉ በቀጠናው ያላትን ሚና በማጉላት ተጠቃሚነቷን የሚያሳድጉ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

  የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁሉ የልባዊ ምስጋና በአመያ ከተማ ስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም እናቀርባለን ።‎አቶ ወንድሙ ዋጌ ደስታ‎የአመያ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ቅ...
02/06/2026

የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁሉ የልባዊ ምስጋና በአመያ ከተማ ስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም እናቀርባለን ።

‎አቶ ወንድሙ ዋጌ ደስታ
‎የአመያ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ

  ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊለመላው የኮንታ ህዝብና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ!7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ  ከፍተኛ ዋጋ የከፈ...
02/06/2026

ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
ለመላው የኮንታ ህዝብና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ!

7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ዋጋ የከፈላችሁ የዞናችን አመራሮች፣ ምርጫ ቦርድ፣ የዞናችን ህዝብ፣ ፀጥታ አካላት፣ ምርጫ አስፈጻሚዎች እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ።

የምርጫ ውጤት ምንም ይሁን ምን ህዝባችን እስከ ምሽቱ 6:00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ትዕግሥት በማሳየት ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ማድረጉ መቼም ከልባችን የሚጠፋ አይደለም። ምርጫው ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የኮንታ ዞን ህዝብ ያለውን የሰላም ባህል፣ የዴሞክራሲ እሴት እና የሀገር ፍቅር በተግባር ያሳየበት ነው።

Address

Ameya
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ameya City Prosperity Party Branch Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category