Gammo dara

Gammo dara Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gammo dara, Grocers, Addis Ababa.

14/07/2026
14/07/2026
ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!በየካ ክፍለከተማ የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም  የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የወረዳ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ...
06/01/2026

ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!
በየካ ክፍለከተማ የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የወረዳ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት ተገመገመ።

በግምገማውም በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 25 ንዑስ አንቀፅ 6 በዝርዝር ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት በመነሳት በበጀት አመቱ ቁልፍ ተልዕኮዎች አንፃር የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራትና ሥነ-ምግባር ጤንነት ከማስጠበቅ፤ የአባላት መብት በማስጠበቅ እና የፓርቲውን ሀብት እና ንብረት ከማስጠበቅ አኳያ አበረታች ውጤቶች እደተመዘገበ ከግዜ ወደግዜ ከፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ለጋራ ዓላማ እና ግብ ኮሚሽኑን በመደገፍ ረገድ በጣም ስኬታማ መሆን በ6 ወር ተገምግሟል። ከዚህ በተጨማሪ የኮሚሽኑና የፓርቲ አባላት በራስ አቅምና ከማዕከል በሚወረዱ ስልጠና በጋራ በመስጠት እንዲሁም በመከታተል በመደገፍ ፤ የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራት ከማረጋገጥ በሱፐር ቪዥንና በኢንስፔክሸን ሥራ በማረጋገጥ የነበሩ ክፍተቶች እንዲታረሙ ለማድረግ የተሠራው ቅንጅታዊ ስራ በጣም የተሻለ እንደነበር ተገልጿል።

በመድረኩም የክ/ከተማው ኢንስፔክሽንና የስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተፈራ ማሞ እንደገለፁት የተሠሩ ስራውችን በጥራት ከመጠመር፣ መረጃ በጥራት ከማደራጀት፣ የፓርቲ አሰራር ስርዓት ከማስከበርና ከማክበር፣ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከመስጠት አኳያ እንዲሁም የኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዥን በወቅቱ በመስራት አንድ ደረጃ ከፍ ላለው መዋቅር ከመላክ አንፃር የነበሩ ክፍተቶች በቀጣይ ትኩረት ተሰቷቸው መታረም እና መስተካከል እዳለባቸው በግልፅ አስቀምጠዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራትና የሥነ ምግባር ጤንነት ከማስጠበቅ፤ የአባላት መብት በማስጠበቅ እና የፓርቲውን ሀብት እና ንብረት ክትትል ድጋፍ በማድረግ ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ መመዝገብ በርካታ ውጤቶች እንዲመጡ አስችሏል።
በአጠቃላይ የክ/ከተማው የኢንስፔክሽንና የስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተፈራ ማሞ በቀጣይ በየደረጃው ያለው ኮሚሽን በግማሽ መንፈቅ ዓመት የታዩ ጥንካሬዎችን በመልካም ተሞክሮ እንዲሰፉ ማድረግ እና የነበሩ ክፍተቶችን በማረም የፓርቲን እሳቤ በመላበስ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታችን ሁሉም የኮሚሽን አባል የደርሻውን በመወጣት እንደሚገባው ተገልጿል።

18/11/2025
18/11/2025

የውስጠ ፓርቲ ኢንስፔክሽን ፐርፎርማስ ኦዲት/ Perfomance Audit Inspection Procedure/ ግብረ- ግብረ መልስ ከክፍለከተማ እና ወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር የጋራ ተደረገ!!
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸

ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም፤
👇✖️✖️✖️👇
የውስጠ ፓርቲ ፐርፎርማስ ኦዲት በ4 ክላስተር ፤ ልዩ ወረዳን ጨምሮ በ13 ወረዳዎች 26 ህብረቶች፤104 ቤተሰቦች፤ 1080 አባላትን ባሳተፈ መልኩ በወረዳ ፤ በክላስተር የተጠመረ ሪፖርት ያቀረቡት የየካ ክፍለከተማ ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ሽፈራ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በመመርኮዝ በዝርዝር ሪፖርቱ ቀርቦ በመድረኩ ውይይት ተደርጎበታል!!

በመድረኩም የተገኝተው መድረኩን የመሩት የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ የተከናወነው ውጤታማ የኢንስፔክሽን ስራ በበጀት አመቱ መጨረሻ ማሳካት ላሰብነው ውጤታማ አፈፃፀም ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው በኢንስፔክሽን እና ስነምግባር የሚሰጡ ግብረ መልሶችን በፍጥነት በማረም፣ ጠንካራ ፓርቲ የመገንባት ሂደታችንን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በመቀጠልም ፓርቲያችን ብልፅግና እራሱን በራሱ ለማረም በተቋም ግንባታ አንዱ ሪፎርም ያደረገበት ተቋም የብልፅግና ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን መሆኑን ይህም ተቋም ጠንካራ ፓርቲ የመገንባት ግባችንን ለማሳካት እደአንድ ወሳኝ አቅም መጠቀም ተገቢነት እዳለው በመግለፅ ተቋሙን ማመን ፤ መደገፍ እና የሚሰጡ ግብረ -መልሶችን ወስዶ በአፋጣኝ የማሻሻል እዲሁም በመፍጠር እና መፍጠን መርህ በመመራት ያለንን አባላት ሙሉ አቅም በመጠቀም ፤ ፓርቲው ያወጣቸውን መመሪያዎች ስራ ላይ በማዋል ፤ በየደረጃው የሚገኙ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ጠንካራ ፓርቲ እየገነባን መሄድ እዳለብን በፐርፎርማስ ኦዲቱ በየደረጃው የተሰጡ ግብረ-መልሶችን መነሻ በማድረግ ጥንካሬዎችን ይበልጥ አጠናክሮ በመቀጠል በሂደቱ የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ መልሶ በአጭር ግዜ ምልከታ በማድረግ በተደጋጋሚ ተደግፎ ለውጥ የማያመጡ አካላትና አመራሮች ላይ አሰራሩን ተከትሎ ተጠያቂ የሚደረጉ መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ሀይሌ ግልፅ አቅጣጫ ሰተዋል!!
የየካ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የሆኑት አቶ መገርሳ ገላና በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በፀደቀው መተዳደሪያ ደንብ ኮሚሽኑ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ የወጡ መመሪያዎችን በስራ ላይ መዋላቸውን በመከታተል የቀረቡ የፐርፎርማስ ኦዲት ግኝቶች በቃል ግብረ መልስ ከተሰጠበት ግዜ ጀምሮ ጥንካሬዎችን አልቆ በመፈጸም ክፍተቶችን በትግል በማረም ረገድ የተሰሩ አበረታች ስራዎች መኖራቸውን ገልፀው የአባላት አደረጃጀት፤ የፖለቲካ ግንባታ ፤ የፓርቲውን ፕሮግራም አቅጣጫ በመከተል በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተግባር እና ኃላፊነታቸውን በብቃትና በትጋት በመፈፀም መድረኩን የሚመጥን ተልዕኮና ስምሪት በመስጠት በተለይ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ፤ ስንፍናና ልግመኝነት፤ ውጤት አልበኝነትን በትግል ማረም ማስተካከል እደሚያስፈልግ በዚህም ጉዳይ ላይ ለአንድ ዓላማና ግብ መሳካት ከኮሚሽኑ ጋር በተናበበና በተደራጀ አግባብ መፈፀም እዳለበት አቅጣጫ ሰተዋል!!

የየካ ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ሽፈራው በተነሱ ጥያቄዎች እና ሀሳቦችን መሠረት በማድረግ የክፍለከተማው ከፍተኛ አመራሮች እደገለጹት ፓርቲችን ብልፅግና ትናንትን ፤ዛሬን እና ነገን በተገቢው መልኩ ለማስተሳሰር በውስጠ ፓርቲ ጤናማነት ፤የፓርቲ አባላት መብቶች እና የፓርቲ ሀብቶች በማስጠበቅ ረገድ ሚናውን ሊወጣ የሚችል ተቋም መፍጠሩ "ጠንካራ ኢንስፔክሽን ፤ ለጠንካራ ፓርቲ የሚለውን መርህ በመከተል ብዙ ስራዋች በመስራት ተጨማሪ ዕሴት እና አቅም ለመሆን ከፍተኛ ስራ ሲሰራ መቆየቱን በመድረኩ የተሳተፉ አካላት ምስክርነታቸውን መስጠታቸውን በመግለፅ በፐርፎርማስ ኦዲቱ የታዩ አጠቃላይ ጥንካሬዎች በዝርዝር በሪፖርቱ በንፅፅር የተቀመጠ መሆኑን በተመሳሳይ የነበሩ ዕጥረቶችም በንፅፅር በማቅረብ በሁሉም ደረጃ የቃል እና የፅሁፍ ግብረ መልስ መሰጠቱን ጥቅል ግብረ መልስ ደግሞ ከዚህ መድረክ በኃላ የደሰበትን ደረጃ በመለየት የሚሰጥ መሆኑን በመግለፅ በዚህ በፐርፎርማስ ኦዲት የተሰማሩ አካላትና በየደረጃው የሚገኙ የአስተባባሪ ኮሚቴ አመራሮች በማመስገን ለአንድ ዓላማ እና ግብ መሳካት ሁላችንም በመተዳደሪያ ደንባችንንና እሱን ተከትለው የወጡ መመሪያዎችን በመገንዘብና በማስገንዘብ እዲሁም በመተግበር ረገድ የበኩላችንን ሚና በመወጣት 3ቱን "መ"ዎች ሳይሸራረፉ ተግባር ላይ እዲውሉ ማመን ፤መደገፍ ፤ የሚሰጡ ግብረ መልሶችን መተግበር በየደረጃው ተጠናክረው እዲቀጥሉ በማሳሰብ የዕለቱ የግብረ መልስ መድረክ ተጠናቋል!!

📕 ጠንካራኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲ፤📕

የየካ ክፍለከተማ ብልፅግና ኢንስፔክሽን ሥነ - ምግባር ኮሚሽን ቅርጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ጥቅምት ወር ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም ዋና ዋና የህዳር እና የታህሳስ ወር  የሚመራበትን አቅጣ...
14/11/2025

የየካ ክፍለከተማ ብልፅግና ኢንስፔክሽን ሥነ - ምግባር ኮሚሽን ቅርጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ጥቅምት ወር ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም ዋና ዋና የህዳር እና የታህሳስ ወር የሚመራበትን አቅጣጫ አስቀመጠ !!
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
ህዳር 04 ቀን 2018ዓ.ም፤
👇✖️✖️✖️👇
የመድረኩ አጀንዳዎች
✅ 1ኛ፦ የ2018 ዓ.ም የጥቅምት ወር ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ግብረ መልስ በዝርዝር ሰጠ፤
✅ 2ኛ፦ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ አመት የሱፐር ቪዥን ግብረ -መልስ የደረሰበትን ደረጃ በሁሉም ወረዳ ደረጃ ተገመገመ፤
✅ 3ኛ፦የ2018 ዓ.ም ከተማው በሰጠው ግብረ መልስ መነሻናት በተከለሰው ዕቅድ ውይይት ተደረገ፤
✅4ኛ፦ የህዳር 2018 ዓ.ም ዕቅድን መነሻ ያደረገ ባለ 11 ነጥብ መሠረት ያደረገ የትኩረት አቅጣጫ ተቀመጠ፤

በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እና የተግባር ምዕራፍ ዕቅድ አፈጻጸም አያይዞ ለመገምገም የተቻለ ሲሆን አብዛኛው ወረዳዎቻችን ካስቀመጡት ግብና ዝርዝር ተግባራት አካያ በሁሉም የትኩረት መስኮች የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገባቸውን የተገመገመ ሲሆን ለአደረጃጀትና ለመረጃ ጥራት ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራበት አግባብ አበረታች ከመሆኑም በላይ በመፍጠርና በመፍጠን አልቆ በመፈጸም ደረጃ የተግባር ምዕራፍ የመጀመሪያው ወር አፈጻጸም የተሻለ ጅምር መሆኑ ተገምግሟል!!

በሂደቱም የነበሩ ዕጥረቶች በዝርዝር የተገመገሙ ሲሆን አሁን ከኮሚሽን ህብረት ጋር ተያይዞ አደረጃጀቱን ወደተቀራራቢ አፈጻጸም ማምጣት ላይ ያሉ ክፍተቶች የተገመገመ ሲሆን ከባለፈው ግዜት አንፃር ሲነፃፀር በሁሉም ማህበራዊ መሠረት ሞዴል የሚሆኑ አደረጃጀት መኖራቸውን መመልከት ተችሏል!!

በቀጣይ እዛም እዚም የሚታዩ ትናንሽ ክፍተቶችን በማረም በተለይ ጠንካራ አደረጃጀቶች ልምድና ተሞክሮ በመቀመር ወደሁሉም አደረጃጀት የማዛመት ስራ መሠራት እዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል!!

የ2018ዓ.ም ከተማው በሰጠው ግብረ መልስ መነሻነት ዕቅዱን መልሶ በመከለስ እዲሁም ባለፉት 4 ወረዳ አፈጻጸም በመገምገም የነበሩ ክፍተቶችን ሊሞላ በሚችል የወረደውን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የኮሚሽን ህብረት ድረስ ዕቅድ ተከልሶ በአግባቡ ተዘጋጅቶ ወደተግባር መገባቱን ገምግሞ በቅርቡ ለተከለሱ ዕቅዶች ተጨማሪ ግብረ መልስ በየደረጃው መሰጠት እዳለበት የጋራ መግባባት ተችሏል!!

በመጨረሻም በህዳር እና ታህሳስ ወር ከዕቅዱ በመነሳት 11 ዋና ዋና ነጥቦችን 35 ዝርዝር ተግባራት መሠረት ያደረገ አቅጣጫ ተቀምጦ ውይይት ተደርጎበት ወደተግባር መግባት የሚያስችል አቅም በመፍጠር በየደረጃው ውይይት ተደርጎበት ወደተግባር እዲገባ ቆጥሮ የመስጠት ሥራ በመስራት የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል!!

📕📕 ጠንካራ ኢንስፔክሽን ፤ ለጠንካራ ፓርቲ፤ 📕

በወል እውነት የተገነባ ኢትዮጵያዊነት ለሀገር ማንሰራራት!! “በወል እውነት የተገነባ ኢትዮጵያዊነት ለሀገር ማንሰራራት!!” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የተዘጋጀ ...
04/11/2025

በወል እውነት የተገነባ ኢትዮጵያዊነት ለሀገር ማንሰራራት!!

“በወል እውነት የተገነባ ኢትዮጵያዊነት ለሀገር ማንሰራራት!!” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የተዘጋጀ የኪነ-ጥበብ ምሽት እየተካሄደ ይገኛል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 “በወል እውነት የተገነባ ኢትዮጵያዊነት ለሀገር ማንሰራራት!!” በሚል መሪ ቃል የኪነ-ጥበብ ምሽት ፕሮግራም በውቡ ወንዝ ዳርቻ እየተካሄደ ይገኛል።

በኪነጥበብ ምሽቱ ላይ ወረዳ አመራሮች፣ የኪነጥበብ ባለሞያዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ የሙዚቃ ስራዎች ፣ የባህላዊ ውዝዋዜዎች፣ መነባንብን፣ ወግ፣ መዝሙርን ጨምሮ በርካታ የኪነ-ጥበብ ስራዎች በመቅረብ ላይ ይገኛል።

የካ ወረዳ 02 ኮሙኒኬሽን

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gammo dara posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category