የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ / Marburg Virus Disease Daily update

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ / Marburg Virus Disease Daily update

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ / Marburg Virus Disease Daily update Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ / Marburg Virus Disease Daily update, Grocers, Addis Abeba, Addis Ababa.

የማር-በርግ ቫይረስ ከሌሎች ቫይረሶች አኳያ የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ነዉ ተባለ📌በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች አስክሬን ለቤተሰብ አይሰጥም  | በቅርቡ በኢትዮጵያ የተገኘዉ የማር-በ...
21/11/2025

የማር-በርግ ቫይረስ ከሌሎች ቫይረሶች አኳያ የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ነዉ ተባለ

📌በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች አስክሬን ለቤተሰብ አይሰጥም

| በቅርቡ በኢትዮጵያ የተገኘዉ የማር-በርግ ቫይረስን አስመልክቶ በዛሬው እለት የጤና ሚኒስቴር ለመገናኛ ብዙሃን ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ቫይረሱ በሞት ከተለየ ሰው የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ በመሆኑም መቃብር ስፍራ ላይም ጥንቃቄን ይፈልጋልም ነው የተባለው፡፡

በመድረኩም ከጤና ሚኒስቴር የተወከሉ እና በዘርፉ ልምድ ያላቸው የህክምና ባለሙያዎችም ተሳትፈዋል፡፡ በመድረኩ ከተነሱ ሀሳቦች መካከል ማር-በርግ ከሌሎች ቫይረሶች አንፃር የሞት ምጣኔው ከ 18 - 88 በመቶ ያህል እንደሆነም ተጠቅሷል።

ቫይረሱ በቀጥታ እንደ የለሊት ወፍ ካሉ አዕዋፋት ጋር በሚኖር ንክኪ የሚፈጠር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ በሌላ በኩል ቫይረሱ በሞት ከተለየ ሰው የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ በመሆኑም መቃብር ስፍራ ላይም ልዩ ጥንቃቄን የሚፈልግም ነው ተብሏል።

ለህክምናው የሚያስፈልጉ ግብዐቶች ወጪያቸው ከፍተኛ ስለመሆኑ የተገለፀ ሲሆን ድንገተኛ ትኩሳት፣ድካም፣የምግብ ፍላጎት ማነስ እና ሰውነት የመድማት ሁኔታዎች ከምልክቶቹ መካከል ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

ቫይረሱ ከ2-21 ቀን የመቆየት እድል እንዳለው የተገለፀ ሲሆን በሳይንስ የተረጋገጠ ህክምናም ሆነ መድሃኒት የለዉም ተብሏል፡፡

በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች አስክሬን ለቤተሰብ እንደማይሰጥ ምክንያቱ ደግሞ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ በመሆኑ ፥ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው ተብሏል፡፡

ቫይረሱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጅንካ ከተማ የተከሰተ ሲሆን በቫይረሱ እስካሁን 33 የላብራቶሪ ምርመራዎችን እንደተደረጉ የጤና ሚኒስቴር መረጀ ያመላክታል ያለው መናኸሪያ ኤፍ ኤም ነው፡፡

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታህዳር 12/ 2018 በተጨማሪም በዛሬው ዕለት በተደረገው ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ታማሚ ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ...
21/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ
ህዳር 12/ 2018

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት በተደረገው ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ታማሚ ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆኑ በተመሳሳይ ቦታም የህክምና ክትትላቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።

Marburg Virus Disease Daily update
Ethiopia
November 21/ 2025



Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

21/11/2025

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዕለታዊ ሁኔታ / Marburg Virus Disease Daily update posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category