ኮልፌ ስራና ክህሎት Kolfe Labor and Skill

ኮልፌ ስራና ክህሎት  Kolfe Labor and Skill Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኮልፌ ስራና ክህሎት Kolfe Labor and Skill, Grocers, Kolfe keranio 06, Addis Ababa.

የሀገር ውስጥ ምርቶች የመጠቀም ባህል እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸየአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተር ፕራይዞች ምርታማነት ለሀገር ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ ሳምንታዊ የኢንተርፕራይዝ ባዛር...
01/04/2026

የሀገር ውስጥ ምርቶች የመጠቀም ባህል እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተር ፕራይዞች ምርታማነት ለሀገር ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ ሳምንታዊ የኢንተርፕራይዝ ባዛር መክፈቻ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ መንግስት ለዜጎች የስራ ዕድልን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ጊዜያት ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

በዚህም አምራች ኢንተርፕራይዞች የሥራ ዕድል በመፍጠርና ተኪ ምርቶችን በማምረት ለገበያ በማቅረብ ረገድ ሚናቸው የጎላ ስለመሆናቸው አንስተዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ለኢንተርፕራዝ አምራቾች አሰፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በሀገር ውስጥ ምርቶች የመኩራትና የመጠቀም ባህላችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ኢንተርፕራይዞችን መደገፍ ይገባል ብለዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፣ የኢንተርፐራይዝ ሳምንት ባዛሩ እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበትና ለአምራቾቹ የገበያ ትስስር የሚፈጠርበት ነው ብለዋል።

የኢንተርፕራይዞችን ምርታማነት በማሳደግ ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር እየተሠራ መሆኑንም አንስተዋል።

ባዛሩ በከተማ ደረጃ የተዘጋጀ ሲሆን፣ 300 የሚደርሱ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን አቅርበዋል።

በኤግዚቢሽንና ባዛሩ አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የምግብ ምርቶችና የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች የቀረቡ ሲሆን፣ ባዛሩ ከመጋቢት 23 እስከ 27 እንደሚቆይ ተገልጿል።

ምንጭ AMN

።።።።።።።።።።።።።የተጠቃሚዎች ልየታ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ ።።።።።።።።።። ።።።።።       በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት  ክፍለ ከተማው ውስጥ በሚገኙ ...
23/03/2026

።።።።።።።።።።።።።የተጠቃሚዎች ልየታ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ ።።።።።።።።።። ።።።።። በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ክፍለ ከተማው ውስጥ በሚገኙ 11ዱም ወረዳዎች የAF3 የተጠቃሚዎች ልዬታ ምዝገባ ማካሄድ መጀመሩ ታውቋል። ይህንን ምዝገባ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አከበረኝ ወጋገን በይፋ ያስጀመሩ ሰሆን የልየታ ምዝገባው እስከ መጋቢት 29/2018 እንደሚቆይ ለኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ኮሚኒኬሽን ኮሚቴ በደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። በምዝገባው ሂደት ላይ የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ተመዝጋቢዎች ባለሙያዎቻችን በሚጠይቁት መረጃ መሰረት መመዝገብና የሚጠየቁትን መረጃዎች በታማኝነት በማስሞላት መመዝገብ የሚቻል መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። መልካም ጊዜ!

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የምግብ ዋስትናና ሴፍቲኔት ቡድን ለክ/ከተማው እና ለወረዳ አስተባባሪዎች፣ለቴክኒካል ኮርድኔሽን ኮሚቴዎች(TCC)፣ለቡድን መሪዎች እና ለባለ...
14/03/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የምግብ ዋስትናና ሴፍቲኔት ቡድን ለክ/ከተማው እና ለወረዳ አስተባባሪዎች፣ለቴክኒካል ኮርድኔሽን ኮሚቴዎች(TCC)፣ለቡድን መሪዎች እና ለባለሙያዎች በAF3 ልየታ ስራ ዙሪያ እንዲሁም ስራዎቹ የሚከናወኑበት የጊዜ ሰሌዳ ላይ በ3/7/2018ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል።

 # # # የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራም ተካሄደ # # # # # # # የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት በየሳምንቱ ሰኞ የሚያካሂደውን የወርቃማው ሰኞን ፕሮግራም አካሄደ። በዛሬው ማ...
12/01/2026

# # # የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራም ተካሄደ # # # # # # # የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት በየሳምንቱ ሰኞ የሚያካሂደውን የወርቃማው ሰኞን ፕሮግራም አካሄደ። በዛሬው ማለትም 4/05/2018 ዓ.ም ፕርግራም ላይ የጽ/ቤታችን ባልደረባ ወ/ሮ ኮከብ ተዘዋውረው በሰሩባቸው የተለያዩ ክ/ከተሞችና ጽ/ቤቶች ያገኙትን ልምድ ያካፈሉን ስሆን በፕሮግራሙ ላይም ክቡር አቶ አከበረኝ ወጋገን የኮ/ቀራንዮ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ኃላፊ እንዲሁም አቶ ሄኖክ አሰፋ የኮ/ቀራንዮ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ተገኝተው በቅደም ተከተል የስራ መመሪያና አበቃላይ የግማሽ ዓመቱን ስራ በተመለከተ አጭር ምልከታ አድርገው ሁሉም ሰራተኛ ከፊታችን ለምጠብቀን የግማሽ ዓመት ምዘና መረጃዎችን ጥንቅቅ አድርጎ ጨርሶ ለምዘና እንድዘጋጅ አጠር ያለ መመሪያ በመስጠት የዛሬው የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራም ተጠናቅቆአል። የስ/ክ/ወ/ሰ/ኮሚቴ

በኮልፌ ቀራኒዮ  ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ90 ቀናት የስራ እድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት   ስራዎች  የተግባራት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሔደ።ኮልፌ ስራና ክህሎት ታህሳስ 21 /2018 ዓ....
30/12/2025

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ90 ቀናት የስራ እድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራዎች የተግባራት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሔደ።

ኮልፌ ስራና ክህሎት ታህሳስ 21 /2018 ዓ.ም

በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በ90 ቀናት በስራ እድል ፈጠራ ዘርፉ እና በሌማት ትሩፋት ተግባራት አፈፃፀም ዙሪያ የክፍለ ከተማዉና የወረዳ በተገኙበት የጋራ ዉይይት ተካሔዷል።

በ90 ቀናት በእቅድ ተይዘው የተሰሩ ተግባራትን አፈጻጸም የስራና ክህሎት ጸህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሔኖክ አሰፋ አቅርበው ውይይት ተካሔዶበታል።

የቀረበውን የአፈፃፀም መነሻ በማድረግ የክፍለ ከተማዉ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን እንደተናገሩት በ90 ቀናት በስራ እድል ፈጠራና በሌማት ትሩፋት ተግባራት ላይ የተሰሩ ስራዎችን የጋራ በማድረግ የተሻሉ አፈፃፀሞችን ለማስቀጠልና ውስንነት ያለባቸው የዘርፍ አፈፃፀሞችን ደግሞ በትኩረት ለመስራት በሚያስችል መልኩ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ምክትል ስራ አስፈፃሚዉ ጨምረዉም ስራ አጥ ዜጎችን በስራ እድል ፈጠራ ዘርፉ ውጤታማ ለማድረግ በየዘርፉ የሚመለከታቸው ተቋማትና አካላት በቅንጅትና በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረው የክፍለ ከተማዉ የዘርፍ አመራሮችም በስራ እድል ፈጠራም ሆነ በሌማት ቱሩፋት ተግባራት ሁሉም ወረዳዎች ወደ ተሻለ አፈፃፀም እንዲመጡ ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት መዘርጋት ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል።

በተመሳሳይ በሌማት ትሩፋት ስራዎችም በየወረዳዉ ያሉ አፈፃፀሞችን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት መከናወን እንደሚገባም ምክትል ስራ አስፈፃሚው አፅንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።

ኃላፊው አያይዘውም በስራ እድል ፈጠራ ስራዎችም ሆነ በሌማት ትሩፋት ተግባራት ጋር ተያይዞ የወጣቶችን፣የሴቶች እና የነዋሪዎች ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ የነባር የሌማት ትሩፋት ተጠቃሚዎችን ምርት እንዲጨምሩ እና አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ወደ ተግባር እንዲገቡ ግንዛቤ በማስጨበጥ የተቀናጀና ተመጋጋቢ የሆነ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የተጀመረው ተግባር ይበልጥ በማጠናከር ሁሉንም ተግባራትን በውጤት መፈፀም ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ላይም በቀጣይ የስራ እድል ፈጠራ እና የሌማት ቱሩፋት ተግባራትን አፈጻጸም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ ተቋማትና የስራ እድል ፈጠራ ግብረ ኃይል አባላት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ የአፈጻጸም አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

29/12/2025

ገጹን ላይክ ሼር አድርጉ። እናመሰግናለን!

።።።።።።።።።።።የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የወርቃማው ሰኛ ፕሮግራም ተካሄደ።።።።።።።።።።።።               በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ...
29/12/2025

።።።።።።።።።።።የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የወርቃማው ሰኛ ፕሮግራም ተካሄደ።።።።።።።።።።።። በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የወርቃማው ሰኞ ፕሮግራም ሁሉም የጽ/ቤቱ ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት ተካሄደ። በዛሬው ማለትም 20/04/2018 ሰኞ በጽ/ቤቱ የሴፍትኔትና ምግብ ዋስትና ቡድን ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀ አማካኝነት "ሙያዊ ስነ-ምግባር" በሚል ርዕስ ስለ ሙያ ስነ-ምግባር ምንነትና ሙያዊ ስነ-ምግባር ምን ምን ሐሳቦችን ማሟላት እንዳለበት ነጥብ በነጥብ አንስተው ጥሩ ግንዛቤ የሰጡ ስሆን ከቤቱም የዚህ አይነቶች አጫጭር የግንዛቤ መስጫ ስልጠናዎች አስፈላጊ እና በዚህች አጭር ሰዓት በጣም ጥሩ የሆነ ግንዛቤ እንድናገኝ ስለምረዳን ለወደፊቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የሚሉና ሌሎችም ሐሳቦች ከተሰጡ በኋላ የዛሬውን አጠናቀናል። ቪድዮና ፎቶዎችን ይመልከቱ። መልካም ቀን!

Address

Kolfe Keranio 06
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኮልፌ ስራና ክህሎት Kolfe Labor and Skill posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category