Arba Minch Conffrence Park

Arba Minch Conffrence Park Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arba Minch Conffrence Park, Grocers, Adiss Ababa, Arba Minch'.

11/04/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ625 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መጪውን የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 6 መቶ 25 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፤ ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር የነበራቸው እና በሕግ በተደነገገው የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ ናቸው።

የሕግ ታራሚዎቹ በመደበኛ የይቅርታ ሕግ እና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተብለዉ በልዩ ሁኔታ የቀረቡ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡

በዚሁ መሰረት የይቅርታው ተጠቃሚዎች ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው በማረሚያ ቤት የቆዩ፤ ከተፈረደባቸው ሲሶ (1/3) እና ከግማሽ (1/2) በላይ የፍርድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ እንዲሁም በማረሚያ ተቋማት ስለመታረማቸውና ስለመልካም ባህሪያቸው ማረጋገጫ የቀረበላቸው መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የይቅርታው ተጠቃሚዎች ከተጎጂ ወገኖች ጋር ታርቀው የእርቅ ሰነድ ማቅረባቸው የተረጋገጠ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ርዕሰ መተዳድሩ የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑ የሕግ ታራሚዎች የይቅርታን እሴት ተላብሰው ሰላም ወዳድ፣ ለሕግ ተገዥና አምራች ዜጋ በመሆን የበደሉትን ህብረተሰብ በማገልግል በልማት የሚክሱ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡም በይቅርታ የተለቀቁት የሕግ ታራሚዎች በፈፀሙት ጥፋት የተፀፀቱና በአግባቡ ታርመው የወጡ መሆኑን በመረዳት መልካም እና አምራች ዜጋ ይሆኑ ዘንድ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ መንግስት ይቅርታ ካደረገላቸው 6 መቶ 25 የሕግ ታራሚዎች መካከል:- 5 መቶ 91 ወንዶች እንዲሁም 32ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ ከነዚህም 6 መቶ 23ቱ ከእስር የሚፈቱ እና ቀሪ 2 ታራሚዎች የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው መሆኑም ታውቋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

11/04/2026

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ ለስቅለት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አርባምንጭ ፣ ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም(አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)፦

ከንቲባ መስፍን መንዛ(ዶ/ር) ባስተላለፉት የ2018 የስቅለት በዓል መልዕክት ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህንን ታላቅ መንፈሳዊ ፀጋ ያለውን በዓል ሲያከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም በፍቅርና በአብሮነት መንፈስ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

የመልዕክታቸዉ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

የተወደዳችሁ የከተማችን ነዋሪዎች፣ እንግዶች እና መላው የክርስቲና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በሠላምና በጤና አደረሳችሁ! አደረሰን!።

በክርስትና እምነት አስተምህሮት ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል በመስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ያሳየውን ፍጹም ፍቅርና የይቅርታና የማዳኑን ሚስጥር በማስታወስ የሚከበረው " በዓለ ስቅለት " በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ሥርዓቶች በመላው ዓለም ይከበራል።

ከ2 ሺህ 18 የምህረት ዓመታት በፊት በእስራኤል የሔሮድስ ንግስና ዘመን ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ዐደባባይ ተገርፎ፣ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ መስቀል አሸክመው እየተገፈተረ በምድር ላይም እየተጣለ ተወስዶ በቀራኒዮ አደባባይ በመስቀል ላይ ሲሰቀል ምንም ሐጢያትና በደል ሳይኖርበት ስለሰው ልጅ ፍፁም ፍቅር ብቻ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠባትን "ዕለተ-አርብ" የስቅለት ቀን ቤተክርስቲያን በፆም፤በፀሎት፣ በስግድትና በአርምሞ ትቀደሳለች።

ሕዝበ ክርስቲያን የሆንን እኛ የክርስቶስን አርዓያ በመከተል መስጠትን የህይወታችን አካል አድርገን በፍቅር እንድንኖር ያሳዬን የፅድቅ መምህራችን እርሱ ነውና ምሳሌነቱን በሕይወት ዘመናችን ሙሉ እንተግብረው።

በመሆኑም ይህን ታላቅ ሀይማኖታዊ በዓል ስናከብር በአብሮነት መንፈስ ያለንን ማህበራዊ አንድነታችንን በማጠናከር፣ በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም በመጋራት እንዲሆን ጥሪዬን በአክብሮት አቀርባለሁ ።

በከተማችን የሚገኙ የእድሜ ባለፀጋ ከሆኑ አረጋውያን፣ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ከተጎዱና ከተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ጎን ሆንና በመተጋገዝ በዓሉን በፍቅር ልናከብር ይገባል።

ከሕዝባችን ጋር የጀመርናቸው በርካታ የልማት ሥራዎችና የመልካም አስተዳደር እና የፍትሕ ጥያቄዎችን በጋራ ለመፍታት በትጋት የምንሰራበት ወቅትም በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣም እጠይቃለሁ ።

በዓሉን በሰከነ ሁኔታ እንድናከብር ጥሪ እያቀረብኩ ድንገተኛ አደጋና አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲገጥማችሁ ለሚመለከተው አካልና ለጸጥታ አካላት በጥቆማ በማሳወቅ የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደረጉ ስልም መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

በድጋሚ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የስቅለት በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ ።

ፈጣሪ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ !

መስፍን መንዛ (ዶ/ር)

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
ሚያዚያ 2/2018 ዓ፣ም
አርባምንጭ || ኢትዮጵያ

የተከበሩ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአዲስ መዋቅር በተቋቋመበት ወቅት ሀላፊነቱን ተረክበው በግልጽ ራዕይ፣ በጽኑ አመራር እና በማይናቅ ትጋት ክልሉን ወደ ሰ...
22/03/2026

የተከበሩ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአዲስ መዋቅር በተቋቋመበት ወቅት ሀላፊነቱን ተረክበው በግልጽ ራዕይ፣ በጽኑ አመራር እና በማይናቅ ትጋት ክልሉን ወደ ሰላም፣ ልማት እና ብልፅግና ለመመራት እየሰሩ ያሉ ተስፋ ሰጪ መሪ ናቸው።

ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ ክልሉን በሁሉም ዘርፎች ለማሻሻል በታላቅ ቁርጠኝነት የተሞላ እና የሚያስደንቅ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ክልሉን ሲረክቡ ብዙ ችግሮችና ፈተናዎች ቢኖሩም፣ በብልሃት፣ በትዕግስት እና በጥንካሬ መሪነታቸው እያንዳንዱን ችግር በመፍታት ክልሉን ወደ ዘላቂ ሰላም እና እድገት መንገድ እየመሩ ናቸው።

አቶ ጥላሁን በፈተናዎች የተጋረጠ ክልል ውስጥ ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር የህዝብ አንድነትን ማጠናከር፣ ሰላምን መጠበቅ እና ሕግና ስርዓትን ማስከበር ውስጥ ታላቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። ክልሉን ለማፍረስ የሚሞክሩ ኃይሎችን በጽናት በመታገል እና በውይይት መፍትሄ በመፈለግ ከአደጋ መጠበቅ ችለዋል።

በሰላም ዘርፍ፣ የተነሱ ግጭቶችን በመቆጣጠር ህዝቡ በመረጋጋትና በእርግጥ እንዲኖር ያስችሉ ዘላቂ የሰላም መንገዶችን አበርክተዋል። እንዲሁም ማኅበራዊ አንድነትን በማጠናከር እና የህዝብ መተማመንን በመጨመር ክልሉ የተረጋጋ የሰላም መሠረት እንዲኖረው አስተዋፅኦ አድርገዋል።

በልማት ዘርፍ ደግሞ፣ መንገዶች፣ ትምህርት፣ ጤና እና የመሠረተ ልማት ስራዎች በሰፊው እንዲከናወኑ በትጋት እየሰሩ ናቸው። ክልሉ ከነበረበት ሁኔታ ወደ ተሻለ ደረጃ መሻሻሉ የመሪነታቸው ግልፅ ምልክት ነው። ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር፣ ኢኮኖሚውን ማነቃቃት እና ክልሉን ወደ ብልፅግና መምራት ላይ በቀንና በሌሊት እየሰሩ ናቸው።

በቱሪዝም ዘርፍም ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ፣ ውብ አካባቢዎች እና ባህላዊ ቅርሶች በማስተዋወቅ ወደ ክልሉ የቱሪዝም ፍሰት እንዲጨምር ታላቅ ስራ አከናውነዋል። ይህም ለክልሉ ኢኮኖሚ እድገት ብቻ ሳይሆን ለዜጎች የስራ እድል ፍጠር ውስጥ አስፈላጊ ሚና ተጫውቷል።

ከዚህ በላይ ለህዝብ ቅርብ የሆነ አመራር በመስጠት፣ ችግር ሲኖር በቦታው በመገኘት ፈጣን መፍትሄ የሚያመጡ እና የህዝቡን ድምፅ በእውነት የሚሰሙ መሆናቸው ለዜጎች ታላቅ እምነት ፈጥሯል። ይህም ያላቸውን የአገልግሎት መንፈስ እና ልዩ የመሪነት ባህሪ ያሳያል።

በአጠቃላይ፣ አቶ ጥላሁን ከበደ ክልሉን ወደ ሰላም፣ ልማት እና ብልፅግና ለመመራት በራሳቸው መስጠት የሚሰሩ ተስፋ ሰጪ እና የሚያነሳሳ መሪ ናቸው። ያደረጉትና እየሰሩት ያለው ሥራ ለቀጣይ ትውልድ የሚታሰብና የሚዘከር ታላቅ ምሳሌ ነው፤ ለሌሎች መሪዎችም አርአያ ይሆናል።

10/02/2026

"ፍትሐዊነት የሰፈነበትና የሕዝብ ድምፅ በተከበረበት አካባቢ ልማት ይፋጠናል፤ ሰላምም ይረጋገጣል። ራዕያችንን ለማሳካት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው ነፃ የምርጫ ሂደት ማረጋገጥ ዋነኛው መንገዳችን ነው።"

ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

10/02/2026

"የሕዝብ ድምፅ የሚከበርበት፣ ፍትሃዊነት የሰፈነበትና በሰላም የሚጠናቀቅ ምርጫ በማካሄድ፤ ለሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ጉዞ የማዕዘን ድንጋይ እናስቀምጣለን" ዶ/ር መስፍን መንዛ አርባምንጭ ከተማ ከንቲባ

07/02/2026
አቶ ሰብስቤ ቡናቤ ላመነበት ጉዳይ ደሬቱን የሚሰጥ:የማንነት ቀውስ(Identity crisis)የለለበት ኩሩ የጋሞ ልጅ ነው!! በቃ አትንጫጩበት!! በ2018ቱ ምርጫ አርባ ምንጭ ምርጫ ክልልን ...
03/02/2026

አቶ ሰብስቤ ቡናቤ ላመነበት ጉዳይ ደሬቱን የሚሰጥ:የማንነት ቀውስ(Identity crisis)የለለበት ኩሩ የጋሞ ልጅ ነው!! በቃ አትንጫጩበት!!
በ2018ቱ ምርጫ አርባ ምንጭ ምርጫ ክልልን ወክሎ ተወካዮች ም/ቤት መግባት አለበት የምል የግል አስተያየት አለኝ::የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሚሆንበትን ጊዜ ተመኘሁ::
ህንፔ ኤክቴ Wasoppite!

‎ "የአርባ ምንጭ ከተማ  የብልፅግና ጉዞ፣ስትራቴጂካዊ አመራርና የልማት ስኬቶች"‎‎ ከየማችን በአሁኑ ወቅት የሚታየው የልማት እንቅስቃሴ ""ከዕቅድ ወደ ተጨባጭ ውጤት"የመሸጋገር ትልቅ ማሳያ...
03/02/2026

‎ "የአርባ ምንጭ ከተማ የብልፅግና ጉዞ፣ስትራቴጂካዊ አመራርና የልማት ስኬቶች"

‎ ከየማችን በአሁኑ ወቅት የሚታየው የልማት እንቅስቃሴ "
"ከዕቅድ ወደ ተጨባጭ ውጤት"የመሸጋገር ትልቅ ማሳያ ነው። ይህ ጉዞ መሪነትን ከንድፈ-ሀሳብ አውጥቶ በከተማችን ላይ በሚታዩ ለውጦች የሚለካ እንዲሆን አድርጎታል።

‎በተለይም በከተማችን ያለውን የተፈጥሮ ጸጋ ወደ ኢኮኖሚያዊ እሴት የመለወጥ ስራ የመሪነትን "ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብ" በግልጽ ያሳያል።

‎ በልማት ረገድ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት ነው። እንደ 40 42 ደረጃ የጫካ ፕሮጀክት ልማት በማስፋፋት የቱሪዝም መዳረሻዎችን ተጨማሪ ግብዓት መጨመር ፣ወኮኪንግ ዶክ ግንባታ በአባያ ሀይቅ አዞ እርባታ አከባቢ መጀመሩና የጀልባ ትራንስፖርት መጀመር በከተማው በዓለም አቀፍ ስታድየም ግንባታ በጥራት መሠራቱ እንዲሁም ለከተማው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ።

‎ከመሪነት ጥበብ አንጻር ሲታይ፣ ይህ የሚያሳየው መሪዎች ያሉትን ድብቅ ሀብቶች ለይቶ የማወቅና እነዚያን ሀብቶች ወደ ብልጽግና ምንጭነት የመቀየር አቅምን ነው። ይህም "ሀብትን መፍጠር" እንጂ "ያለውን ብቻ መጋራት" አለመሆኑን ያስመሰክራል።

‎ ከመሠረተ ልማት አውታሮች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚታዩት በከተማው የኮሪደር ልማት ስራዎች : የትምህርት ተቋማት ማስፋፋትና ተጨማሪ ግንባታዎች : የጤና ተቋማት ግንባታ እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማዘመን ስራ እንቅስቃሴዎችም የከተማውን ገጽታ እየቀየሩት ይገኛሉ። ይህ ለውጥ ከመሪነት ጥበብ አንጻር "የለውጥ አላማኝነት" ውጤት ነው። መሪዎች ትኩረታቸውን በረጅም ጊዜ ውጤት ላይ በማድረግ፣ ዛሬ የሚተከሉ ፕሮጀክቶች ነገ የከተማውን የኢኮኖሚ እንደሚያረጋግጡ በማመን የሚሰሩት ስራ ነው ።

‎አንድ ውጤታማ መሪ ትልቁ ሀብቱ የሰለጠነና ጤናማ ዜጋ መሆኑን ይገነዘባል። በመሆኑም በከተማው እየታየ ያለው የልማት ጉዞ፣ ቁሳዊ እድገትን ከሰው ልጅ እድገት ጋር አቀናጅቶ ለመጓዝ የሚደረግ ጥረት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

‎ በአጠቃላይ፣ በከተማችን የልማትና የለውጥ ጉዞ በጠንካራ የሥራ ባሕል፣ በፈጠራ የታጀበ ሀብት አጠቃቀምና በሕዝብ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው ደግሞ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በጥራት ማጠናቀቅና አዳዲስ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በየጊዜው መፈለግ የመሪነት ቀዳሚ ተግባር ሆኖ ይቀጥላል።

01/01/2026
አርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት በምሰሰል
14/12/2025

አርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት በምሰሰል

Well Come ....
03/11/2025

Well Come ....

loading......party

Address

Adiss Ababa
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch Conffrence Park posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category