Weeqayti Haawa

Weeqayti Haawa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Weeqayti Haawa, Grocers, Afar, Awassa.

31/03/2026
05/02/2026
29/09/2025
29/09/2025
10/09/2025

አዲሱ ዓመት ሰላም የሚጸናበት እና የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በስኬት የሚጠናቀቁበት ይሆናል - የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፡- አዲሱ ዓመት ሰላም የሚጸናበት እና የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በስኬት የሚጠናቀቁበት እንደሚሆን የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ ገለጹ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ፤ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፤ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት እንኳን ለ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የስኬት እንዲሆንም ተመኝተዋል።

2018 ዓ.ም በመላው አገራችን ሰላም በተሟላ መንገድ የሚሰፍንበት እና የተጀመሩ ስራዎች በስኬት የሚጠናቀቁበት ይሆናል ነው ያሉት፡፡

ያለፈው ዓመት ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገሩን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ረገድ ውጤታማ ስራዎችን ያከናወነበት እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ይህን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረው፤ አመራሩም በዚህ ረገድ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያን የሚመጥናት ከፍታ ላይ እንድትደርስ እየተጋ ካለው ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን የተለመደ አጋርነቱን እንዲያሳይ አደራ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ አገርን እየፈተኑ የሚገኙ የውስጥ ባንዳዎችን ነቅሶ በማውጣትና መክሮ ወደ ሰላም አማራጭ እንዲመጡ በማድረግ ረገድም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

#ኢዜአ #ኢትዮጵያ

Address

Afar
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Weeqayti Haawa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category