15/06/2026
#ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡
ድምጻዊው ለሕዝብ ካበረከታቸው የሙዚቃ ሥራዎች መካከል ነይ ዘመድዬ፣ እንዴት ነሽ፣ ደቦት እንስራ፣ ዘና በይ፣ ባላገር እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት እንደነበር ተነግሯል ፡፡
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡
credit via FBC