Ambassel Worda Ethicsየአምባሰል ወረዳ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽ

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessi
  • Ambassel Worda Ethicsየአምባሰል ወረዳ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽ

Ambassel Worda Ethicsየአምባሰል ወረዳ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ambassel Worda Ethicsየአምባሰል ወረዳ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽ, Grocers, ወሎ አምባሰል, Dessi.

11/06/2025

የሙስና ወንጀል ጉዳቶች
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

👉ፖለቲካዊ ጉዳት፡-ሙስና መልካም አስተዳደርንና ዲሞክራሲን ክፉኛ የሚጎዳ ወንጀል በመሆኑ የፖለቲካ አመራሩን ጥራት ያበላሻል፣ እከከኝ ልከክልህን፣ የማይፈጸም ቃል መግባትን ያባብሳል፣ ህዝብን ማዳመጥና ማማከር ይቀራል፣ መሰረታዊና ሰብአዊ መብቶች ይጣሳሉ፡፡ፖለቲካዊ ማን አለብኝነት፣ አምባገነንነት፣ የጎሳ ፖለቲካና ዘረኝነት እንዲባባስ ያደርጋል፡፡ ሙስና ህዝብ በመንግሥትና በሕግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው ያደርጋል፣ ይህም እየተባባሰ ሲሄድ ወደከፋ ግጭት ያመራል፣

👉 የፍትህ ጉዳት፡- ሙስና የህግ የበላይነት እንዲዛባ ያደርጋል፡፡ ከሚያመጣቸዉ ጉዳቶች ዉስጥ ዋናዎቹ፡- የህግና ፖሊሲዎች አለመተግበር፣ ፍትህን ማግኘት አለመቻል፣ መጓተትና መከልከል፣ ችግር ያለበት የህግ አፈጻጸም፣ በህግ ስርአቱ ያለዉ የህዝብ መተማመንና እምነት እንዲቀንስ፣ ስጋት እንዲጨምር፣ ህገ ወጥነት እንዲበዛ ማድረግና የህግና ስርዓት መፈራረስን ያመጣል፡፡

o ከአጥፊዎች ይልቅ ያላጠፉት የሚቀጡበት፣ ፍትህ የሀይለኞችና የሃብታሞች ብቻ እንድትሆን የሚያደርግ ነዉ፡፡ የዚህ ጥቅል ዉጤት ፍትህ ከፍተኛዉን ዋጋ ለሚያቀርብ የሚሸጥ ሸቀጥ በማድረግ በተለይ ለአብዛኛዉና ድሃ ህዝብ ፍትህን ማግኘት አስቸጋሪና ዉስብስብ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

👉 የኢኮኖሚና ፋይናንስ ጉዳት፡- ሙስና የህዝብና የአገር ኢኮኖሚ እድገት ፀር ነው፣ ድህነት እንዲስፋፋ ያደርጋል፣(ገንዘብ ብቻ ሣይሆን የገፀ-ምድርንና የከርስ ምድር፤ ብዝሃ ሕይዎትን፤ ቅርሶችን እንዲመዘበር ያደርጋል፡፡) የኢንቨስትመንት እድሎችን ይዘጋል፣ አመች የንግድ ከባቢ እንዳይኖር ማድረግ፣አገልግሎት ፈላጊው የተፈጠረዉን ቢሮክራሲ ለማለፍ በሚያደርገው ጥረት ለከፍተኛ ወጭ እንዲዳረግና ጉዳዮች እንዲጓተቱ በማድረግ ለከፍተኛ እንግልት እንዲጋለጥ ያደርጋል።

o በመንግሥት ገቢ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ በማሣደር የመንግሥት የኢኮኖሚ አቅምን ያዳክማል፣ የሥራ ውጤታማነትና ምርታማነትን ይቀንሣል/ የሠራተኛውንና የአምራቹን ሞራልና የሥራ ፍላጐት እጅጉን ይጐዳል፤ የገበያ ውድድርን ይቀንሳል፤ ለህዝብ የሚቀርቡ የፍጆታ ዕቃዎች መጠንና ጥራትን በመቀነስ ህዝብን ለከፋ የኢኮኖሚ እና ለጤና ችግር ይዳርጋል፣ በመንግስት ሴክተር ዉስጥ ደግሞ ሙስና ለትምህርት፣ ለጤና፣ የንጹህ መጠጥ ዉሃ፣ ለቤት ልማት፣ ለመንገድና ለመብራትና ሌሎችም መሰረተ ልማት ግንባታዎች መዋል የሚገባዉን ሃብት በቀላሉ ሊመዘበርበት ወደሚችል አቅጣጫ እንዲዞር በማድረግ፣ ትልልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች ተሰናክለዉና ተዘግተው ግለሰቦች ተጠቃሚ እንዲሆኑና ብዙሃኑ እንዲጎዳ የሚደረግበት ሁነታ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

o ሚዛናዊ ባልሆነ የኢኮኖሚ እድገትና የመንግስት ሃብትና ንብረት ወደ ሌላ አቅጣጫ በመዞሩ ምክንያት ድህነትና የሀብት ልዩነት መጠን ስለሚሰፋ ድግግሞሹ በበዛ አዙሪት ዉስጥ ግለሰቦችና አገር እጅግ በከፋ ሁኔታ እንዲራቆቱ የሚያደርግ ነዉ፡፡

👉 ስነልቦናዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ጉዳቶች፡-ሙስና ቀስ በቀስ በዜጎች መካከል ያለውን የኑሮ ደረጃ ልዩነት የሚፈጥርና የሚያሰፋ ነዉ፡፡ የሀብት ልዩነት ማህበራዊ አንድነትን በመናድ ማህበረሰብ እንዲከፋፈል፣ ህግና ስርአት እንዲወድቅ፣ ሥርዓት አልበኝነት እንዲሰፋ፣ ወንጀለኝነት፣ ምን ቸገረኝነትን፣ ስንፍናንና ተስፋ መቁረጥን የሚያስከትል ይሆናል፡፡

o ሙስና የሰዉ ልጅ ሰብአዊ ክብርን የሚሸረሽር፤ ምሁራዊ ስንፍናን (intellectual impotency) እና ወሬኛነትን የሚያሰፋ፣ እያወቁ እዉነታን መደበቅ፣ ችላ ባይነትንና ደንታ ቢስነትን፣ ትኩረት አለመስጠትን የሚያባብስ

ፍትሀዊነት ከጥቅምና ከግዴታ አኳያ🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿ዜጎች በሀገራቸው መንግሥት ከሚሰጡ ማንኛውም የማህበራዊ አገልግሎት  ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የሚገባቸውን ጥቅምና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው ...
30/05/2025

ፍትሀዊነት ከጥቅምና ከግዴታ አኳያ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ዜጎች በሀገራቸው መንግሥት ከሚሰጡ ማንኛውም የማህበራዊ አገልግሎት ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የሚገባቸውን ጥቅምና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡

በመሆኑም መንግሥት በሚሰጣቸው የትምህርት፣ የጤና፣ የመዝናኛና የመሳሰሉ አገልግሎቶች እኩል የመጠቀም መብት አላቸው፡፡

ፍትሀዊ የሀብትና የአገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ የመገለልና የተበዳይነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ በዚህም የተነሳ በመንግሥት ላይ እምነት በማጣት ሀገራቸውን መጥላትና መኮብለል ይጀምራሉ፡፡ ግዴታቸውንም ለመወጣት እልክ ስለሚጋቡ በሀገር እድገት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራሉ፡፡

ዜጎች ያለምንም አድሎ የእኩል እድል ተጠቃሚነት መብት ሊከበርላቸው እንደሚገባ ሁሉ፣ ግዴታቸውንም ያለአድልዎና ያለልዩነት ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለምሳሌ ግብርን በአግባቡ መክፈል፣ ለህዝባዊ ተቋማት ግንባታ በጉልበትም ሆነ በገንዘብ መደገፍ፣ ለተገነቡት ተቋማት አስፈላጊውን እንክብካቤና ጥበቃ ማድረግ፣ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡

በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ሙስና እንዳይከሰት የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሙስና ከተስፋፋ ግን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት የሚባለው ሀሳብ ህልም ሆኖ ይቀራል፡፡

ስለሆነም ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በህብረት እንታገል!

08/11/2024

ሙስና መኖሩን የሚያመላክቱ ዋናዋና ማሳያዎች
**
ሙስና በተለያዩ መንገዶች ሊገለፅ ይችላል፡፡ ሙስና በባህሪው ተለዋዋጭ ውስብስብ ቢሆንም ሙስና መኖሩን የሚያመላክቱ ዋናዋና ማሳያዎች የሚከተሉት ናቸው:-

1 የግልፀኝነት ጉድለት
👉ግልፅ ያልሆነ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ሲኖሩ
👉መረጃዎችን ለህዝብ ወይም ለባለድርሻ ተደራሽ ያለማድረግ ችግሮች ሲበራከቱ

2 የጥቅም ግጭት ሲፈጠር
👉የግል ፍላጎትን ከሙያ ፍላጎቶች የሚጋጭበት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ

3 ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም
👉ውሳኔ ሰጪ አካላት ለግል ጥቅማቸው ስልጣንን አለአግባብ ሲጠቀሙ ሙስና ሊከሰት ይችላል፡፡

4 መመሪያዎችን ችላ ማለት
👉ከመመሪያ ውጪ የሚሰሩ ስራዎች ሲበራከቱ

5 ከመጠን ያለፈ ዋጋ ወይም ያልተለመደ ቅናሾች
👉በድንገት የዋጋ ጭማሪ ወይም ከገበያ ዋጋ ጋር የማይጣጣሙ ግዢዎች ሲፈፀሙ፡፡

6 የሙስና ተጠቋሚዎችን ቅሬታ ችላ ማለት
👉ሪፖርት የተደረጉ ስጋቶችን ችላ ማለትና የሙስና ጠቋሚዎችን ከለላ ችላ ማለት፡፡

7 የተጠያቂነት ማነስ
👉ደካማ የተጠያቂነት ስርዓት ሲኖር

8 የክትትል ማነስ
👉ደካማ የውስጥና የውጪ ክትትልና ቁጥጥር ሲኖር

የሙስና ምልክቶችን ለይቶ በማወቅና ምልክቶችን በመቅረፍ መልካም አስተዳደር በማስፈን የሙስና መከላከል ሚናችንን እንወጣ፡፡

“ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን

Address

ወሎ አምባሰል
Dessi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ambassel Worda Ethicsየአምባሰል ወረዳ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category