Wondie nigussie EBooks

Wondie nigussie EBooks Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wondie nigussie EBooks, Grocers, dessie, Dessie.

30/08/2025

390ሺህ ብር በላይ የተፈፅመ የማጭበርበር ታሪክ. . . (እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ)
ከዚህ በታች የምናጋራችሁ ከ390ሺህ ብር በላይ ስለተጭበረበረች የባንካችን ደንበኛ ታሪክ ይሆናል. . .

ወ/ሪት ሄለን ተሾመ (ስም የተቀየረ) በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ በአካውንቲንግ ሙያ ተቀጥራ እያገለገለች የምትገኝ ወጣት ሴት ናት። ወ/ሪት ሄለን በዚህ በምታገኘው ደሞዝ ህይወቱን ትመራለች። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የኑሮ ውድነት እና መሰረታዊ ፍላጎቶቿን ለማሟላት፣ በአንድ ገቢ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ የእሷን እና የቤተሰቧን ህይወት ማሻሻል ከባድ መሆኑን በመገንዘብ ተጨማሪ የኦንላይን (online) ስራዎችን መፈለግ ከጀመረች ሰነባብታለች።

ከእለታት አንድ ቀን ይህ ውጥኗ ተሳክቶ በፌስቡክ ላይ ያየችው ማስታወቂያ ቀልቧን ይስበዋል። ይዘቱም በፎሬክስ ንግድ ላይ ለመሰማራት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ የሚል ነበር። ወ/ሪት ሄለንም ፌስቡክ ላይ የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀለች።

ይህ ቴሌግራም ቻናል ከ አርባ ሶስት ሺህ በላይ ሰዎች ስብስክራብ ያረጉት ሲሆን ሰዎች ኢንቨስት አድርገው ትርፋማ እንደሆኑ ምስክርነታቸውን በአማራኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የሚሰጡ ሰዎች ስታይ በይበልጥ ጉጉት አደረባት። 10,000 ብር ኢንቨስት ስታደርጊ 180,000 ብር ትርፍ እናከፋፍላለን የሚሉ ማባበያዎችን እንዲ በቀላሉ ማለፍ አልቻለችም ነበር። ቴሌግራም ላይ ያለ ኤጀንት መጀመሪያ በትንሹ ጀምራ ከዛ እያሳደገች እንድትሄድ እና እንዴት
እንደሚሰሩ እንድታይ ምክረ-ሀሳብ ያቀርብላታል። ከዛም ወ/ሪት ሄለን ገንዘቡን አስገብታ ቃል የተገባላት ገንዘብ ከ 24 ሰዓት በኋላ ይገባላታል። ይህ ድርጊት ወ/ሪት ሄለንን በጣም ያስደሰተ እና ከሌሎች ሰዎች ተበድራም ቢሆን ኢንቨስት በማድረግ ትርፏን ማሳደግ እና ብድሮቿን ቶሎ መመለስ እንደምትችል በማመን በተለያዩ ሰዎች ስም ከፍ ያለ ገንዘብ ኢንቨስት ታደርጋለች። የምታገኘው ተመላሽ ገንዘብ ከፍ ማለቱን ተከተሎ ትላንት አምናቸው ኢንቨስት ያደረገችባቸው ተቋም ደብዛቸውን አጥፍተው ባዶ እጇን ሲያስቀራት ነበር የደረሰባትን ማመን ያቃታት። ወ/ሪት ሄለን በአጠቃላይ ከ 390ሺህ ብር በላይ በአጭበርባሪዎች አጥታለች።

ጥቃት አድራሾች ወ/ርት ሄለንን ለማታለል የተጠቀሙበት ዘዴ ምን ነበር?
ጥቃት አድራሾች ሄለንን ለማታለል የተጠቀሙበት ቴክኒክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር (Investment Scams) የሚባለውን ሲሆን ይህም የሰዎችን ልምድ አለመኖር እና ፍራቻን በማጫር የሚፈፅም የማታለል ዘዴ ነው።

በክፍል ሁለት ቀጣይ ሳምንት ስለ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር (Investment Scams) ምንነት፣ ባህሪያት እና መከላከያ መንገዶችን የምንጠቁማችሁ ይሆናል።

በምንለቃቸው የደህንነት ምክረ-ሀሳቦች ላይ ተመሳሳይ ታሪክ፣ ሀሳብ እና አስተያየት ካሎት በ t ያጋሩን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

30/08/2025

ፓምፕ እና ዳምፕ (Pump and Dump) ክሪፕቶ ማጭበርበር ምን ያህል ያውቃሉ ?
ዘመን ዘመንን እየተካ ሲመጣ እንደ ክሮፕቶ (crypto) ያሉ ምናባዊ የዲጂታል የመገበያያ ገንዘቦች በፊት ከነበሩት ወረቀት እና ሳንቲሞችን በመተካት በብዛት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛል። ይህን ክሮፕቶ ገንዘብ አይነት በእጃችን አንዳስሰውም፣ በአይናችን አናየውም ነገር ግን ይገዛል፣ ይገዛበታል፣ይሸጣል። አጭበርባሪዎች በ crypto ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለውን የቁጥጥር ስርዓት እጥረት እና የተጠቃሚዎችን ፈጣን የትርፍ ፍላጎት መሰረት በማድረግ የተለያዩ ማጭበርበሮችን ሲፈፅሙ ይስተዋላል። በዚህ አምድ ፓምፕ እና ዳምፕ (Pump and Dump) ስለሚሰኘው የክሪፕቶ ማጭበርበር የምንዳስስ ይሆናል።

ፓምፕ እና ዳምፕ (Pump and Dump) ክሪፕቶ ማጭበርበር ገበያን ላልተገባ አላማ በማዋል የሚፈፅም ተግባር ሲሆን ይህም አንድ የዲጂታል ምናባዊ ገንዘብን ዋጋ ወደፊት እንደሚንር በመንገር/በማስተማር ሰዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማባበል የሚፈፅም ነው

30/08/2025

አንድ የማጭበርበር ገጠመኝ ላጋራችሁ::
ሐያት (ስም የተቀየረ) የሷን እና የቤተሰቧን ኑሮ ለማሻሻል ስትል የ10ኛ ክፍል ትምህርቷን እንደጨረሰች ነበር ከአንድ ገጠራማ የኢትዮጵያ ክፍል በመነሳት በነዳጅ ሀብቷ ከምትታወቀው እና በዓለም ላይ ካሉ ግዙፍ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ተርታ 18ኛ ደረጃ ላይ ወደ ተቆናጠጠቺው፣ የመካከለኛ ምስራቋ ሀገር ሳውዲ አረቢያ ያቀናችው። ጉዟዋ ገና የመጀመሪያ እና እንግዳ ነገር ስለሆነባት አጠገቧ ተቀምጣ ወደ ሳውዲ ስትሄድ ከነበረችው ሶፊያ (ስም የተቀየረ) ጋር የተዋወቁት። ሶፊ ከዚህ በፊት ወደ ሳውዲ በስራ ምክንያት ስለምትመላለስ ያላትን ልምድ እንደምታካፍላት እና ምንም ሀሳብ እንዳይገባት ትነግራታለች። ሐያት የሶፊን መልካም አሳቢነት በማየቷ የነበራት ጭንቀት በጣም ቀሏታል። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ጓደኝነታቸው እያደገ እና እየጠነከረ በመምጣቱ ከጓደኝነትም አልፈው ወደ ቤተሰባዊነት ዘልቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሶፊ ብዙ አመት ሳውዲ በመቆየቷ እና ሀገር ቤት ተመልሳ ትዳር ለመመስረት በማሰቧ፣ ኢቃማ ተመቶላት (ድጋሚ ወደዛ ሀገር ላለመመለስ ፓስፖርት ላይ ሚታተም) ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰች ሰነባብታለች። ሶፊ ጠቅልላ ወደ ሀገሯ ብትመለስም ከሐያት ጋር ያላትን ግንኙነት በመካከላቸው ያለው እርቀት ሳይገድባቸው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በድምፅም እና በአጭር ፅሁፍ መልዕክት ማስቀጠል ችለዋል። ከእለታት አንድ ቀን ሶፊ በፌስቡክ በጣም እንደተቸገረች እና ሀምሳ ሺህ ብር (50,000)
በአስቸኳይ እንድትልክላት ለሐያት በፅሁፍ ታሳውቃታለች። ሐያትም በነገሩ በመደናደጥ ምን እንዳጋጠማት ለማወቅ በተደጋጋሚ የድምፅ መልዕክቶችን ብትልክላትም ሶፊ ቤተሰቧ ችግር ላይ መውደቁን፣ ያላቻት ብቸኛ ተስፋ እሷ መሆኗን በፅሁፍ ቶሎ ገንዘቡን እንድታስገባላት ታሳስባታለች። ሐያትም ካላቸው ቅርበት የተነሳ የኢ.ን.ባ አካውንቷን እንድትልክ ትጠይቃታለች። በዚህን ጊዜ ሶፊ የሷ የየኢ.ን.ባ አካውንት እንደተዘጋ እና በሌላ መሃመድ ሰኢድ (ስም የተቀየረ) በሚባል ግለሰብ እንድታስገባ አካውንቷን ትልክላታለች። የዚህን ጊዜ ሐያት ስጋት ስለገባት በስልክ ደውላ ለማረጋገጥ ወደ ሶፊ ስልክ ትደውላለች። የስልክ ልውውጣቸው እንደሚከተለው ቀርቧል (ከድምፅ ጥሪው የተቀነጨበ)።

ሐያት፦ እንዴት ነሽ ሶፊ?

ሶፊያ፦ አንቺንም በሉሽ?

ሐያት፦ ምኑን ነው ሚበሉኝ?

ሶፊያ፦ ውይ አልሰማሽም! የፌስቡክ አካውንቴ ተሰርቆ እኮ እኔን በመምሰል ገንዘብ እየጠየቁ እያጭበረበሩ ነበር። አንቺንም ገንዘብ አስልከው ከሆነ ብዬ ነው።፦ እኔማ አንቺ መሆንሽን እና አካውንቱ ልክ ነው ልልሽ ነበር የደወልኩት።

ሶፊያ፦ ፌስቡክ አካውንቴ በሌላ ሰው ሲምካርድ ስለተከፈተ የይለፍ-ቃሉን መቀየር አልቻልኩም።

ሐያት፦ እኔ በድምፅ መልዕክት ስልክ፣ በፅሁፍ ስትመልሺልኝ ተጠራጥሬ፣ አይ ባይመቻት ነው ብዬ አስቤ ነው ዝም ያልኩት።

ሶፊያ፦ ለማንኛውም ተርፈሻል እህቴ፣ ቻው።

ሐያት፦ ቻው።

ከዚህ ታሪክ መረዳት የምችለው ሐያት ገንዘቧን ማትረፍ የቻለችው ምንም ያህል ከምታውቀው የፌስቡክ አካውንት ወይም ምታውቃት ልጅ የእርዳታ ጥሪ ቢደርሳትም፣ በስልክ ደውላ የምትልክበት አካውንት ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ቆም ብላ በማሰቧ እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን።

23/08/2025
21/08/2025

Since Ethiopia is preparing to launch the Ethiopian Securities Exchange (ESX), understanding the role of Fundamental Analysis (FA) and Technical Analysis (TA) is very importa
📈 Role of Fundamental & Technical Analysis for ESX
1. Fundamental Analysis (FA)

English:
In the Ethiopian Securities Exchange (ESX), fundamental analysis will help investors assess the true value of companies that list on the exchange. Since many Ethiopian companies may be new to public markets, investors will rely on their financial statements, profitability, growth potential, and sector performance to make long-term investment decisions.

Role in ESX:

Identifying undervalued or overvalued stocks.

Analyzing company reports, earnings, and dividends.

Evaluating Ethiopia’s macroeconomic factors (GDP, inflation, FX, interest rates).

Supporting long-term investment strategies.

Amharic (የመሠረት ትንተና በESX ውስጥ):
በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ገበያ (ESX) ውስጥ የመሠረት ትንተና ተወዳዳሪ ኩባንያዎች እውነተኛ ዋጋ ለመገመት ዋና ቁልፍ ይሆናል። ከመጀመሪያ ጊዜ የወጡ ኩባንያዎች በገበያ ላይ ስለሚኖሩ፣ ኢንቨስተሮች የእነሱን የፋይናንስ ሪፖርቶች፣ ትርፍ አቅም፣ የኢንዱስትሪ አቅጣጫ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ በጥልቅ ይመርመራሉ።

በESX ውስጥ ተግባር:

ዋጋው ዝቅተኛ ወይም ከፍ ነው ተብሎ የሚታወቀውን አክሲዮን ማስረዳት

የኩባንያ ሪፖርቶችን፣ ትርፍና ትርፍ መከፋፈልን መመርመር

የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን (ጂዲፒ፣ ዋጋ እድገት፣ የገንዘብ ተመን) ማስተካከል

ለረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ስትራቴጂ መርዳት

2. Technical Analysis (TA)

English:
In ESX, technical analysis will play an important role in short-term trading and understanding market psychology. Since ESX will be a new market, there may be high volatility at the beginning, and traders will use price charts, volume data, and patterns to predict price movements and decide when to buy or sell.

Role in ESX:

Identifying short-term price trends and momentum.

Helping traders decide entry and exit points.

Analyzing demand and supply pressures in the market.

Supporting active trading strategies for liquidity.

Amharic (የቴክኒክ ትንተና በESX ውስጥ):
በESX ውስጥ የቴክኒክ ትንተና በአጭር ጊዜ ንግድና በገበያ ስነ-ልቦና መረዳት ዋና ሚና ይጫወታል። አዲስ ገበያ ስለሆነ በመጀመሪያ ወቅት የተጨናነቀ እንቅስቃሴ ሊኖርበት ይችላል፣ ትሬደሮችም የዋጋ ገበታዎች፣ መጠን መረጃና ንድፎችን በመጠቀም የግዢ ወይም የሽያጭ ውሳኔ ያደርጋሉ።

በESX ውስጥ ተግባር:

አጭር ጊዜ የዋጋ አቅጣጫና እንቅስቃሴ መለየት

የግቢና የውጪ ጊዜ መወሰን ለትሬደሮች ማገዝ

በገበያ ውስጥ የእቃ እና የፍላጎት ግፊት መተንበይ

ለንቁ ንግድና ለልምድ መድረክ መርዳት

✅ Summary / መደረግ

Fundamental Analysis will guide long-term investors in ESX by focusing on company value and economic growth.

Technical Analysis will help short-term traders by focusing on price action and market behavior.

For ESX to succeed, both FA and TA knowledge will be essential for Ethiopian investors and institution .
ከተስማማወ ሸር አትርሱ, አስተያየት ስጡኝ አሠሰግናለሁ

Address

Dessie
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wondie nigussie EBooks posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category