Aysha ahmed

Aysha ahmed Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aysha ahmed, Grocers, Dire Dawa.

05/09/2026
05/09/2026

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ ነው - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የማይነጣጠል ታሪካዊ ቁርኝት ያላትና የባሕር በር ጥያቄዋም የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና አጀንዳ መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፥ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ከጥንት ጀምሮ ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ግዛት ወሰን አካል ሆኖ መኖሩን አውስተዋል።

ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎችም የራሳቸውን መገበያያ ገንዘብ በመጠቀም በቀይ ባሕር በኩል እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ድረስ ይነግዱ እንደነበር አውስተዋል።

ከ1950ዎቹ በኋላም አሰብና ምፅዋ የኢትዮጵያ ዋና የባሕር በር ወደቦች ሆነው ማገልገላቸውን አስታውሰዋል።

ሆኖም የኢህአዴግ መንግሥት ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት በሌለው ሁኔታ፣ ያለምንም የሕዝብ ውይይትና ያለ በቂ ጥናት በድንገተኛ ውሳኔ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታጣ ማድረጉንም አብራርተዋል።

ለሀገርና ለሕዝብ ኃላፊነት በማይሰማው መንግሥት የተፈጸመው ይህ የጥፋት ውሳኔ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ጠባሳ መፍጠሩን ጠቁመዋል።

በባሕር ንግድ በተሳሰረች ዓለም ውስጥ 130 ሚሊዮን ሕዝብን ይዞ ያለ ምንም የባሕር መውጫ ረጅም ጉዞ ማሰብ አይቻልም ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ።

የባሕር በር ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ በቁጭት የቆየ መሆኑን ጠቅሰው፥ አሁን ያለው መንግሥት ኃላፊነት የሚሰማው በመሆኑ የባሕር በር አጀንዳን ፊት ለፊት ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል።

የባሕር በር ለንግድ ብቻ ሳይሆን ሀገርን ከጥቃት ለመከላከልም ወሳኝ የብሔራዊ ደህንነት ዓምድ ነው ብለዋል።

አክለውም የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድና የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ጠቅሰው፣ ጉዳዩ ትውልድ የማይተወው የህልውና አጀንዳ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል።

በቀይ ባሕር ዙሪያ ያሉ ሀገራት የሕዝብ ብዛትና ኢኮኖሚ ተደምሮ የኢትዮጵያን ግማሽ አቅም እንኳ እንደማይደርስ የጠቆሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መምጣት ለእነዚህ ሀገራትም ትሩፋት እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ቀጣናው የኃያላን ሀገራት መራኮቻና የተለዋዋጭ ሁኔታዎች ሰለባ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዚህ አኳያ የቀጣናው ሀገራት በጋራ መልማት የምርጫ ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረዋል ።

የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመቀነስ በኢኮኖሚና በታሪክ የተሳሰረውን ሕዝባቸውን ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደሚገባቸውም ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ በአካባቢው ግዙፍ ኢኮኖሚ የምታንቀሳቅስ መሆኗ ፋይዳው ድንበር ዘለል ነው ያሉት አንጋፋው ፖለቲከኛ፥ ከባሕር በር ተነጥላ ልትኖር ስለማትችል የአካባቢው ሀገራት የመውጫ በር ሊሰጧት ይገባል ነው ያሉት።

ይህ ካልሆነ ግን ግዙፍ የህዝብ ቁጥር ያላት በመሆኗ በጊዜ ሂደት በተፈጥሯዊ መንገድ የታፈነው ጥያቄ መፈንዳቱ አይቀሬ ነው ብለዋል።

ይህ እንዳይሆን የቀጣናው ሀገራት በሰላማዊ መንገድ የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት በመከላከልና ሀብትን በጋራ በመጠቀም መርህ ለኢትዮጵያ የባሕር በር በማመቻቸት የጋራ ህልውናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ

05/09/2026
05/09/2026

የኢትዮጵያ ህዝብ ሌብነት በቃኝ ብሏል፤
ሌቦችን ከዉስጣችሁ አጥሩ ብሏል፤
ሌብነት የተንሰራፋበት ብልጽግና የመጨረሻ ዉጤት አያመጣም ብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)

05/09/2026

በሐረሪ ክልል በ2018 በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ዘላቂ ሰላምን በመገንባታችን የተገኙ ናቸው" — አቶ ጌቱ ወዬሳ

በሐረሪ ክልል በ2018 የበጀት ዓመት በጤና፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ አበራታች ስኬቶች በክልሉ የተረጋገጠው ዘላቂና አንፃራዊ ሰላም ውጤቶች መሆናቸውን የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ።

አቶ ጌቱ ወዬሳ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ በበጀት ዓመቱ በጤናው ዘርፍ በርካታ የጤና ተቋማት ተገንብተው ወደ ሥራ ከመግባታቸው ባሻገር፤ ተጨማሪ አዳዲስ ግንባታዎችና የማስፋፊያ ሥራዎች ተከናውነው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።

አቶ ጌቱ አያይዘውም ክልሉ ከ40 በላይ ብሔረሰቦች በሰላምና በፍቅር አብረው የሚኖሩበት ልዩ የኅብረብሔራዊነትና የመቻቻል ተምሳሌት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ አብሮነትና በገጠርና ከተማ ነዋሪዎች መካከል ያለው ጠንካራ ትስስር ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ ትልቁን ድርሻ ማበርከቱን ተናግረዋል።

"ሕዝባችን ከማንኛውም በላይ ሰላምን የሚወድ ነው" ያሉት አቶ ጌቱ፤ በክልሉ የተገኘው ሰላም ዜጎች በ24 ሰዓት ሙሉ በነፃነትና በሰላም ወጥተው እንዲሠሩ ዕድል በመፍጠሩ ለምርጫው ሂደት፣ ለከተማና ገጠር ልማት እንዲሁም ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች መሳካት መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።

ለዚህ አስተማማኝ ሰላም መረጋገጥ የሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ እንዳለ ሆኖ የክልሉ ፖሊስና ሚሊሻ፣ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የምሥራቅ ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቅንጅት የሠሩት ሥራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከአጎራባች የኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሐረርጌ ዞንና ማያ ሲቲ አመራሮችና ሕዝብ ጋር እንደ አንድ ቤተሰብ በመሆን በልማትና በሰላም ላይ በጋራ መሠራቱ ለውጤቱ መገኘት አወንታዊ ሚና መጫወቱን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በ2018 የበጀት ዓመት የሐረሪ ክልል ሕዝብ በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መድረኮች ላይ ተወካዮቹን በመላክና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣቱን የጠቀሱት አቶ ጌቱ ወዬሳ፤ የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

05/09/2026
05/09/2026
04/09/2026

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aysha ahmed posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category