በየዓይነቱ

በየዓይነቱ Action !

07/06/2026
07/06/2026

‎🌍 የዓለም ዋንጫ ሰኔ 04 ሐሙስ ይጀመራል !
‎=============================
‎የ2026ቱ የዓለም እግርኳስ ዋንጫ በአሜሪካ፣ በሜክሲኮና ካናዳ ጣምራ አዘጋጅነት ከሰኔ 04 እስከ ሐምሌ 12/20/18 ዓም ድረስ በ48 ሀገራት መካከል ለመጀመሪያ ግዜ ይካሄዳል ።

‎በአጠቃላይ ከሰባት አህጉራት የተውጣጡ 48 ሀገራት በ12 ምድብ ተደልድለዋል ። ከአውሮፓ 16፣ ከአፍሪካ 10፣ ከኤጂያ 9፣ ከሴሜንና መካከለኛ አሜሪካ 6፣ ከደቡብ አሜሪካ 6፣ ከኦሺኒያ 1 ተሳታፊ ይሆናሉ ።

‎የመክፈቻ ጨዋታ በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ሰኔ 04 በስታዲዮ አዚተካ ሜክሲኮ ከተማ ይደረጋል።

‎ኡዝበኪስታን፣ ጆርዳን፣ ኩራካዎና ኬፕ ቬርድ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ግዜ በአለም ዋንጫ ይሳተፋሉ ። የሰሜን አሜሪካዋ ኩራካዎ 150 ሺ ህዝብ ብቻ ያላት ትንሿ ተሳታፊ ሀገር ናት ።

‎ብራዚል አምስት ግዜ ሻምፒዮን በመሆን ቀዳሚ ስትሆን ጀርመንና ጣሊያን አራት አራት ግዜ አርጀንቲና ደግሞ ለሶስተኛ ግዜ የዓለም ሻምፒዮን የሆኑ ሀገራት ናቸው ። ዘንድሮስ?

‎በአጠቃላይ በ39 ቀናት ቆይታው 104 ጨዋታዎች ተደርጎ ሐምሌ 12 በአሜሪካ ኒውዮርክ ኒውጄርሲ ስታዲየም ፍፃሜውን ያገኛል።

‎የጨዋታ ፕሮግራሞችና ውጤቶችን እየተከታተልን በየትኩሱ ወደ እናንተ እናደርሳለን። በፕሮግራሞቻችን ላይ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አነጋግሩን። 👉 የስፖርት ገጽ Tamirat Mageto

#ስፖርት #አርሰናል

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በየዓይነቱ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share