Bokku

Bokku Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bokku, Grocers, Nek'emte.

21/08/2026
20/08/2026
20/08/2026

ሀገራዊ የጋራ ትርክት የመፍጠር አስፈላጊነቱ:-

🧩 ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት፣
🧩 የሀገርን ልማት እና ዕድገት ለማፋጠንን፣
🧩 የሕግ የበላይነት እና ፍትሕን ለማረጋገጥ፣
🧩 የዜጎችን ክብር እና ደህንነት ለማስጠበቅ፣
🧩 እንደ ሀገር ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር፣
🧩 በሕዝቦች መካከል ዘላቂ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን ለመፍጠር ያስፈልጋል።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

19/08/2026

ቀጣይ ምን ክፍል በስራ ላይ እናሳያችሁ?‌‌

የሰላም ትጋታችን ከካሜራዉ በስተጀርባ! 🕊

በየዕለቱ 962 ላይ በነፃ የስልክ እና የፅሁፍ መልዕክት የምትሰጡንን ሰላማችንን የሚያደፈርሱ የአመላካች እና የክስተት መረጃዎችን የምንቀበልበት የጥሪ ማዕከላችን ይህ ነው።



ሰላም ለኢትዮጵያችን! 🇪🇹

Which executive team would you like to see next?

Our Peace efforts behind the Scene! 🕊

Every day on 962 your free call and SMS information on indicators and incidents that disturb our Peace is received by this contact center.



Peace for our Ethiopia! 🇪🇹

19/08/2026

የሰላም ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሐሳብ ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ ፕሮግራም በመንደፍ እየሰራ ይገኛል። በፕሮግራሙ ከ66 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳትፈው ለሰላም፣ ለአብሮነት እና ለማኅበረሰብ አገልግሎት አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ከፕሮግራሙ አስተዋጽኦዎች መካከልም፦
🎯 ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን እና ወንድማማችነትን ያጠናክራል
🎯 የሀገር ፍቅር፣ የመተማመን እና የአብሮነት እሴቶችን ያጎለብታል
🎯 ወጣቶች የተለያዩ የሀገራችንን ማኅበረሰቦች እንዲያውቁ ያስችላል
🎯 ዕውቀታቸውን እና አቅማቸውን ለማኅበረሰቡ እንዲያበረክቱ ያበረታታል

ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ወጣቶች ጊዜያቸውን፣ ዕውቀታቸውን እና አቅማቸውን ለማኅበረሰቡ በፈቃደኝነት በማበርከት ለዘላቂ ሰላም፣ ለአብሮነት እና ለልማት የሚያበረክቱበት ሀገራዊ ፕሮግራም ነው።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

ሀገራዊ አደራን ቡድናዊ በማድረግ ሀላፊነትን አለመወጣት ነውር ነውየህዝብን አደራና እምነት ወደ ጎን በመተው በቡድተኝነት መንቀሳቀስ፣ አስታራቂ ሀሳብ ይዞ ከመቅረብ ይልቅ የግልን አቋም ብቻ ማ...
16/08/2026

ሀገራዊ አደራን ቡድናዊ በማድረግ ሀላፊነትን አለመወጣት ነውር ነው

የህዝብን አደራና እምነት ወደ ጎን በመተው በቡድተኝነት መንቀሳቀስ፣ አስታራቂ ሀሳብ ይዞ ከመቅረብ ይልቅ የግልን አቋም ብቻ ማራመድና ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር ቡድናዊ ማድረግ ሀላፊነትን አለማወቅ እንዲሁም የተሰጠን አደራ በትክክል አለመወጣት ነው። ከዚህም በላይ በጀርባ ማሴርና አላስፈላጊ ግሩፕ እየከፈቱ መንቀሳቀስ ለሀገርና ለወደፊት ትውልድ ከመጨነቅ ይልቅ የግልንና የቡድንን ጠባብ ፍላጎት ማደላደልን ያሳያል።

ከምክክሩ አዳራሽ ቡድን ውጪ እውቅና የሌለውና ወገንተኛ የሆነ ሀሳብ ለማራመድ ቡድን ከፍቶ ለብቻ ተሰባስቦ መዶለት ለነገ አለማሰብንና የሌላን ሀሳብ ለማድመጥ ዝግጁ አለመሆንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በተመሳሳይ መልኩ በምክክሩ ሂደት ገና ከውጪ አቋም ይዞ መግባትና ግትር ሆኖ የሌላውን ሀሳብ አስቀድሞ መጣል ለስኬታማና አካታች ውይይት በሩን የሚዘጋ ጎጂ አካሄድ ነው።

15/08/2026

Address

Nek'emte

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bokku posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category