18/12/2024
ቢሠረዝ ....የማይደበዝዝ
ቢደለዝ ......እያደር ሚ'ደምቅ፣
ቢጣጣል .....ገዝፎ ሚ'ጎላ
ቢዋረድ ....ከቅኔ ሚ'ረቅቅ፣
በደቦ ቢገረስሱት
ቃልኪዳን ......ከፍ የሚያደርገው፣
በሴራ ቢያወሳስቡት
ነጭ ሃቅ .....በክብር ሚ'ያልቀው፣
ቢገሉት ቢገድሉት... ማ'ይሞት
ሺ ጊዜ ቢያርዱት .....ማ'ይደማ፣
ወደ እንጥሮጦስ ቢገፉት
መገኛው ...ከፍ ያለ ማማ፣
አለም ተስማምቶ ቢተጋ
ሊጋርድ... ደማቁን እውነት፣
ማ'ያስችል... አንዳች ሃይል ያለው
ምስጢር ነው ጀዋር ሲራጅ መሀመድ።