አ/ሀምድ ሻራፍ

አ/ሀምድ ሻራፍ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አ/ሀምድ ሻራፍ, Grocers, ሀለባ, Addis Ababa.

አንድ ጥያቄ ልጣይቃቹ ይዝህ ሰዉዬ ስራ ምንድኖ ?እስት አስርዱኝ!
17/08/2023

አንድ ጥያቄ ልጣይቃቹ ይዝህ ሰዉዬ ስራ ምንድኖ ?እስት አስርዱኝ!

13/07/2023

ግብር ክፋል:

02/07/2023
29/06/2023

ለመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ተጠናቀቀ - ትምህርት ሚኒስቴር
*********************************************

የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን እውቀትና ብቃት ለመለካት የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦቸ መካከል አንዱ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ የማድረግ ግብን ለማሳካት እየሰራች ነው።

እንደ አገር በትምህርት ተደራሽነት ላይ ባለፉት 25 ዓመታት በስፋት ቢሰራም በጥራት በኩል ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንሚገኝ በመረጋገጡ ይህን ማሻሻል የሚያስችል የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷል።

በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን እንዲያስመርቁና የትምህርት ጥራታቸውን እንዲያሻሽሉ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይህን ጉዳይ በማስመልከት በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ ዶክተር ኢዮብ አየነው ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በዚህም በዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ራስ ገዝ የማድረግ፣ በተልዕኮ የመለየት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መረጃ በአንድ የዲጂታል ማዕከል ማስተዳደር እና የመውጫ ፈተና መስጠትን ማዕከል ያደረጉ የለውጥ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

በዚህም ዘንድሮ የሚመረቁ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውንና በተማሩበት ሙያ አጠቃላይ መሰረታዊ እውቀት ስለመጨበጣቸው የብቃት መለኪያ በማዘጋጀት የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል ነው ያሉት።

የመውጫ ፈተና ለዩኒቨርሲቲዎች አዲስ እንዳልሆነ የገለጹት ኃላፊው፤ የህግ እና የጤና ተማሪዎች ከ10 ዓመታት በላይ የመውጫ ፈተና ሲወስዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ያንን ልምድ በማስፋትና እንደ ሀገር ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የመውጫ ፈተናው ከ2015 ጀምሮ በሁሉም የትምህርት መስኮችና መርሐ ግብሮች መስጠት እንዲቻል ስራዎች ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰሩ ቆይተዋል ነው ያሉት።

ፈተናውም ከሃምሌ ሶስት እስከ ስምንት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ስለፈተናው ለተማሪዎችና ለትምህርት ማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራታቸውን እና ምክክር ሲደረግ መቆየቱንም ጠቅሰዋል።

ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ከተማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የሚባሉ ከ12 እስከ 17 የትምህርት ዓይነቶች ፈተና እንደሚወጣ ገልጸው፤ ለዚህም የፈተና ንድፍ እና የብቃት መመዘኛ መስፈርቶች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

በመውጫ ፈተና አዘገጃጀት መመሪያ መሰረትም ከግንቦት 15 ጀምሮ ለ211 የትምህርት ፕሮግራሞች የፈተና ጥያቄዎች በማውጣት ለፈተናው ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንዲሆን ተደርጓል ነው ያሉት።

ፈተናው በኦንላየን የሚሰጥ በመሆኑም አስፈላጊ የቴሌኮም እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ ካሉ 325 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 161 እና ከመንግስት ደግሞ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስፈትኑ ጠቅሰዋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትክክለኛ ተፈታኞችን ቁጥር እንዲያጣራ በማድረግ፤ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 95 ሺህ 755 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ 74 ሺህ 706 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ጠቁመዋል።

ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎቸ ዲግሪ እንደማይሰጣቸው እና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው የፈተና ጊዜ መሰረት ድጋሚ እንደሚፈተኑ ተናገረዋል።

ፈተናው ለበርካታ ተማሪዎች አዲስ ቢሆንም የዓመታት ልፋታቸውንና የገበዩትን እውቀት የሚለካ መሆኑን በመገንዘብ በተረጋጋ ሁኔታ ለመፈተን እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።

ወላጆችም ልጆቻቸው ብቁ ሆነው እንዲመረቁላቸው በስነ-ልቦና ማገዝ እንዳለባቸው ነው ዶክተር ኢዮብ የጠየቁት።

28/06/2023
28/06/2023
27/06/2023

ሀበይ ለ1444ለኜይ ለኢድ-አል-አደሀ/አረፈ ዲነኜ ሙሊ ቦገሬት አጄጄሙ

ሀበይ ቦገሬት ቂጦም አጄጄና

ሙሊ አያሚ ዮገሬት የሙሃባ ዋ የአፍራን ዮንናነኮ ትልትሜኝ ዐረፋይ ቲሃብዲ ወገሬትነ አብዞኔ በቂሮት፣ ነግዳዶነ(ፋኖይ) በአፍራን በነሻጣ በትቂበሎት፣ ጩጠይ ባልብሶትዋ ስንቀ ባብሎት፣ በዋጀ ማጥነት፣ ለሳድ ባድነ በትምረሮት፣ በጉትነ ኢቦርሳን ታይነብሪቢነ ባፍራን በኢሽቅ ያቴልፉያን ዮናነኮ ያሽነ ኢላው አኩም ሀበይ ለሙሊ ዐረፋ ቦገሬት አጄጄና አጄጄሙ!

ለታላቁ የዒድ አል-አደሃ የዐረፋ በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ እያልኩ በዓለሙ በሰላም፣ በጤና፣ በደስታ፣ በፍቅር፣ በመተሳሰብ፣ እንዲያልፍ ጥብቅ ምኞቴ ነዉ።

በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስር ❝ሸገር❞ ተብሎ በሚጠራዉ ከተማ ባሉ አከባቢዎች የሚገኙ በርካታ መስጂዶች፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ወኪል ከሆነዉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እዉቅና ውጭ መፍረሳቸዉን ተከትሎ ግንቦት18 /09/15 ጁምዓ፣ ግንቦት 25/09/15 ጁምዓ በአንዋር መስጂድ በተደረገዉ ሰላማዊ ተቃዉሞ ሰማዕት ለሆኑ የሸሂድነት ደረጃ እንዲሰጣችሁ፣ ለቆሰሉና ጉዳት ለደረሰባቸዉ የእምነት ወንድሞቼና ወገኖቼ እንትበረቱ፤

በሕመም ላይ ሆናችሁ፣ በየሆስፒታል ለምትገኙ እህት ወንድሞቼ እናትና አባቶቼ፣ አሏህ(ሱ.ወ) ለጤናችሁ መሻሻልና ለአከላችሁ ብርታት እንዲሰጥ፤

በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ መኖሪያ ቤታችሁ ፈርሶባችሁ፤ ከልጅና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ችግር ላይ ለምትገኙ ዉድ ወገኖቼ አሏህ(ሱ.ወ) ሶብርና ብርታት እንዲሰጣችሁ፤

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በየትኛዉም መልኩ ለተፈናቀላችሁ፣ ጉዳት ለደረሰባችሁ፣... በሙሉ አሏህ(ሱ.ወ) የተሻለ ኑርና ሰላምን እንዲያጎናጽፋችሁ፤

ከልብ የመነጨ ምኞቴ ነዉ።

የሙሀበ፣ ዮገሬት፣ የቲጋገዞትዋ ለሳድባድ የትማረሮት ሙሊ ዮናነኮ በትሚኖት የስልጤ ዞን መቲንዳደሬ በድባየ ሀበይ ለ1444ለኜይ ያረፈ /ኢድ አል አድሃ/ ሙሊ ቦገሬት አጄጄሙ ኢድሙባረክ ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሳሊሃል አእማል ይላዉ።

27/06/2023

በሃሰተኛ የባንክ መልዕክት 60 ኩንታል ጤፍ በማታለል የወሰደ ግለሰብ ከነግብራበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

ገንዘብ ገቢ ስለመደረጉ የሚገልፅ ሃሰተኛ የባንክ የፅሁፍ መልዕክት አዘጋጅቶ በመላክ ከአንድ ነጋዴ ላይ ከ650 ሺህ ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለውን 60 ኩንታል ጤፍ በማታለል የወሰደ ግለሰብ ከነግብራበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ወንጀሉ የተፈፀመው በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ውጪ ወደሚገኙ አንድ የጤፍ ነጋዴ ስልክ በመደወል ስልክ ቁጥራቸውን ከሰው አፈላልጎ እንዳገኘ እና 60 ኩንታል ጤፍ እንደሚፈልግ ይነግራቸዋል፡፡ የግል ተበዳይም ለማላውቀው ሰው እንዴት እልካለሁ ብለው በጠየቁት ወቅት ችግር የለውም ጤፉ የሚራገፈው ገንዘቡን ወደ ባንክ ካስገባሁልዎት በኋላ ነው ብሎ ያግባባቸዋል፡፡

የግል ተበዳይም በዚህ ሃሳብ ተስማምተው አንዱን ኩንታል ጤፍ የሚሸጡት በ10ሺህ 850 ብር መሆኑን ከተነጋገሩ እና ከተግባቡ በኋላ 60 ኩንታል ጤፍ አስጭነው ወደ አዲስ አበባ ይልካሉ፡፡

ተጠርጣሪው ግን ገንዘብ ገቢ ከተደረገ በኋላ ባንኩ በሞባይል ባንኪንግ የሚልከውን የፅሁፍ መልዕክት አስመስሎ ሃሰተኛ ፅሁፍ በማዘጋጀት ገንዘቡን አስገብቻለሁ ብሎ መልዕክቱን ከላከላቸው በኋላ ጤፉን ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል አካባቢ በተለምዶ አስክሬን በር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኝ አንድ ወፍጮ ቤት ውስጥ እንዲራገፍ አድርጓል፡፡

የግል ተበዳይም ገብቷል የተባለውን ገንዘብ ለማውጣት ወደባንክ በሄዱበት ወቅት ምንም አይነት ገንዘብ ገቢ እንዳልተደረገላቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጉዳዩን በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለፈረንሳይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡

ፖሊስም የቀረበለትን አቤቱታ ተቀብሎ የምርመራ እና የክትትል ስራ ከጀመረ በኋላ ጤፉ ተራገፈ ወደተባለበት ወፍጮ ቤት በመሄድ ከተላከው 60 ኩንታል ጤፍ ውስጥ 35 ኩንታሉን ሊያገኝ ችሏል፡፡

የማታለል ወንጀሉን የፈፀመውን ዋናውን ተጠርጣሪ ጨምሮ አባሪ ተባባሪ በመሆን ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 3 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡

በንግድ ግንኙነት ወቅት በነጋዴ እና በሸማቹ መካከል የሚፈጠር መተማመን አልፎ አልፎ ለመሰል ወንጀል የሚያጋልጥ በመሆኑ አስፈላጊው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

ጥቅም ሰዉና ነጭ ልብስ ቶሎ ብሎኖ ምቆሽሻሁ፡
27/06/2023

ጥቅም ሰዉና ነጭ ልብስ ቶሎ ብሎኖ ምቆሽሻሁ፡

18/06/2023

Address

ሀለባ
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አ/ሀምድ ሻራፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category