ተስፋ አለኝ በሀገሬ

ተስፋ አለኝ በሀገሬ I love Ethiopia & Ethiopian

04/09/2026

"ኦሮሞ ህዝባችን ነው"
ሞጣ

በፍፁም ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ድርጊት ነው!! በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የተስተዋለውና አንድ አሽከርካሪ የትራፊክ ደንብ በመጣሱ ምክንያት ቅጣት ሲጣልበት ከትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ወደ...
02/09/2026

በፍፁም ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ድርጊት ነው!!

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የተስተዋለውና አንድ አሽከርካሪ የትራፊክ ደንብ በመጣሱ ምክንያት ቅጣት ሲጣልበት ከትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ወደ አካላዊ ግጭትና ድብድብ ሲገባ የሚያሳየው ምስል እጅግ አሳፋሪ ነው።

ህግ አስከባሪዎች የራሳቸውን የግል ፍላጎት ሳይሆን የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ በስፍራው የተገኙ የመንግስት እና የህዝብ ወኪሎች ናቸው። እነሱን መንካት፣ መሳደብ ወይም መደብደብ ቀጥታ ህግንና ስርዓትን እንደመደብደብ፣ እንዲሁም የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ እንደመጣል ይቆጠራል።

በዚህ ድርጊት ዙሪያ የሚነሱ ክርክሮች አብዛኛውን ጊዜ የሚያተኩሩት "ቅጣቱ በዛ" ወይም "ለምን ታርጋ ይፈታል" በሚሉ የቅጣት አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ነው። ነገር ግን ትልቁና መሰረታዊው ጥያቄ መሆን ያለበት፣ "አሽከርካሪው ገና ከመነሻው ለምን የትራፊክ ህግን ጥሶ ተገኘ?" የሚለው ነው።

የትራፊክ ህጎች የተነደፉት የዜጎችን ውድ ህይወት ለመታደግ እና የሀገርን ሀብት ከውድመት ለመጠበቅ ነው። የትራፊክ አደጋ በሰው አካል፣ ህይወት እና በንብረት ላይ የሚያደርሰው ዘግናኝ ጉዳት በቀላሉ የሚታይ አይደለም፤ ስንት ቤተሰብን በትኗል፣ ስንቱን አካል ጉዳተኛ አድርጓል። ይህንን እልቂት ለማስቆም፣ ስርዓት እንዲከበርና አደጋዎች እንዲቀንሱ ከተፈለገ፣ ህግን መተላለፍ የሚያስከትለው ዋጋ እጅግ ከባድ ሊሆን ይገባል።

ያደጉትን ሀገራት ተሞክሮ ብንመለከት፣ ለምሳሌ በአሜሪካ የትራፊክ ህግን መተላለፍ የሚያስከትለው የገንዘብ ቅጣት እጅግ በጣም ከፍተኛ እና አንዳንዴም የመንጃ ፈቃድን እስከማሳጣት የሚያደርስ ነው። ከቅጣቱ ክብደት የተነሳ አሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ ህግን ላለመጣስም ይጥራሉ።

ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ ግን "ትንሽ ተሳሳቱ፣ ስለዚህ ትንሽ ይቀጡ" የሚል የተሳሳተ አመለካከት ይስተዋላል። በሰው ህይወት ላይ የሚቀለድበት "ትንሽ ጥፋት" የለም፤ ምክንያቱም አንዲት ትንሽ የምትመስል የትኩረት ማጣት ወይም የህግ ጥሰት የብዙዎችን ህይወት በሰከንዶች ውስጥ ልትቀጥፍ ትችላለችና። ህግ ህግ ነው፤ ጥፋት ከተፈጸመ ተመጣጣኝ እና ዳግም እንዳይደገም የሚያደርግ አስተማሪ ቅጣት ሊኖር ግድ ይላል።

አንድ ግለሰብ የራሱን ጥፋት ለመሸፈን፣ ወይም ከቅጣት ለማምለጥ ብሎ የህግ አስከባሪዎችን በጉልበት ለማሸነፍ መሞከሩ ፍጹም አጸያፊና ስርአት አልበኝነት ነው።

ይህ ዓይነቱ ድርጊት ማህበረሰባዊ ቀውስን የሚጋብዝ እና በምንም ዓይነት መለኪያ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

የህግ አካላት ስራቸውን በአግባቡ ሲሰሩ ሊደገፉና ሊበረታቱ እንጂ፣ በአደባባይ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው አይገባም። ማንኛውም ዜጋ ቅሬታ ካለው በሰለጠነና በህጋዊ መንገድ ማቅረብ ሲችል፣ አቋራጭ እና የጉልበት መንገድን መምረጥ ትልቅ ድንቁርና ነው።

ማህበረሰባችን ይህንን አሳፋሪ ድርጊት በጽኑ ሊያወግዘው እና የህግ የበላይነት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲከበር በጋራ ሊቆም ይገባል። ህግን ማክበር የፍርሃት ሳይሆን የስልጣኔ እና የኃላፊነት ስሜት መገለጫ መሆኑን ተረድተን፣ ለህግ እና ህግን ለማስከበር ለቆሙ አካላት ተገቢውን ክብር መስጠት የሁላችንም የማይደራደር ግዴታ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ከ900 ኪሎ ዋት በላይ የሚያመነጩ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ​ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) - በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዊ ጉዲና ወረ...
20/08/2026

በኦሮሚያ ክልል ከ900 ኪሎ ዋት በላይ የሚያመነጩ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

​ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) - በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዊ ጉዲና ወረዳ በዓለም ባንክና አጋር አካላት ድጋፍ (በADELE ፕሮግራም) የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
• ​ በ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡት እነዚህ ፕሮጀክቶች በባቴ (200 ኪ.ዋ)፣ ቶርበን (125 ኪ.ዋ)፣ ሃሮ ኦባ (225 ኪ.ዋ) እና ሃሎ ጎባ (350 ኪ.ዋ) ቀበሌዎች ላይ የተዘረጋ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከ900 ኪሎ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም አላቸው።

• ​ፕሮጀክቶቹ 7.74 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣ 30.29 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እና 10 ትራንስፎርመሮችን ያካተቱ ናቸው።

• ​ፕሮጀክቶቹ ከ5 ሺህ በላይ አባወራዎችን እንዲሁም የጤናና የትምህርት ተቋማትን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የማድረግ አቅም ያላቸው ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ከ840 በላይ አባወራዎች አገልግሎቱን ማግኘት ጀምረዋል።

• ​ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ህብረተሰቡ ንብረቶቹን እንደግል በመንከባከብ የአገልግሎት ክፍያውን በወቅቱ ሊከፍል ይገባል ብለዋል።

• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬም አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

​በምርቃቱ ላይ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም አከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

   !​ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) — የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቁንቢ ወረዳ ያስገነባቸው 850 ኪ...
17/08/2026

!

​ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) — የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቁንቢ ወረዳ ያስገነባቸው 850 ኪሎ ዋት አጠቃላይ አቅም ያላቸው የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች (Solar Mini-grid) መመረቃቸውን አሳወቁ።

​ፕሮጀክቶቹ የተገነቡባቸው ዋና ዋና ቦታዎች፡-
• ​ሀሪሮ ከተማ፡ 600 ኪሎ ዋት ማመንጨት የሚችል ሲሆን፣ በ408 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብቶ 2,943 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

• ​ሀሮጉራቲ ቀበሌ፡ 250 ኪሎ ዋት የሚያመነጭ ሲሆን፣ በ232 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብቶ 703 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

​በምረቃ መርሃግብሩ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ፤ ፕሮጀክቶቹ ከግሪድ ርቀው የሚኖሩ ነዋሪዎችን የኃይል ጥያቄ የሚመልሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም እ.ኤ.አ. በ2035 70% ከግሪድ እና 30% ከግሪድ ውጪ ያሉ ማህበረሰቦችን የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል።

​የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ በበኩላቸው፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ 26 የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልጸዋል።

12/08/2026
01/08/2026
Planting a tree isn't just for today—it’s a gift of breath, climate resilience, and life for generations to come. Join u...
31/07/2026

Planting a tree isn't just for today—it’s a gift of breath, climate resilience, and life for generations to come. Join us as we plant 800M seedlings in 1 day! 🌍🌱

29/07/2026

ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ሳሂባ ጋፋሮቫ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነታችንን እና የጋራ እድገታችንን ይበልጥ በሚያሳድጉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማና ውጤታማ ውይይት አካሂደናል።

Af-yaa'ii Mana Maree Biyyaalessaa, Rippabiliika Azarbajaan, Kabajamoo Sahiba Gafarova, waliin dhimmoota michummaa keenya tarsiimowaafi guddina keenya waloo caalaatti cimsan irratti haala milkaa'aa ta'een marii'anneerra.

It was a pleasure to speak with H.E. Mrs. Sahiba Gafarova, Speaker of the Milli Majlis of the Republic of Azerbaijan. We engaged in productive discussions on strengthening our bilateral relations, building on a shared commitment to a deeper strategic partnership and mutual growth.

ግብጽ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መሰረተ ቢስ ክስ ከማቅረብ ይልቅ መደራደር ያዋጣታል - ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018  ግብጽ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መሰረ...
29/07/2026

ግብጽ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መሰረተ ቢስ ክስ ከማቅረብ ይልቅ መደራደር ያዋጣታል - ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018

ግብጽ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መሰረተ ቢስ ክሶችን ከማሰማት ይልቅ በጋራ ማዕቀፎች ተስማምታ መደራደር ያዋጣታል አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፡፡

ሚኒስትሩ ግብጽ የምታቀርባቸውን የሀሰት ውንጀላዎች አስመልክተው በሰጡት ምላሽ፥ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካውያን የጋራ ሀብት የሆነው የሕዳሴ ግድብ ከዓድዋ ድል በመቀጠል የአንድነትና የትብብር ማሳያ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

አፍሪካውያን በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ደስተኞች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ነገር ግን ግብጽ የግድቡ ግንባታ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በርካታ ክሶችን ስታቅርብ መቆየቷን አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ያለማንም ርዳታ በራሳቸው ገንዘብና ጉልበት የገነቡትን ግድብ ግብጽ ያለበቂ ምክንያት እንደ ስጋት መቁጠሯ አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለግብጽ እና ለተፋሰሱ ሀገራት ስጋት ሳይሆን በረከት መሆኑን ጠቁመው፥ ግድቡ በግብጽ እና ሱዳን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ያስቀረ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ግድቡ ቀጣናውን በኃይል በማስተሳሰር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸው፥ ለአብነትም ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ ከግድቡ የአሌክትሪክ ኃይል በመግዛት ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ግብጽ ኢትዮጵያ በያዘችው ውሃ ምክንያት የግድቦቿ የውሃ መጠን እንደቀነሰ አድርጋ ክስ ማቅረቧ ተቀባይነት የለውም ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርና የጋራ እድገት መርህን እንደምትከተል የገለጹት ሚኒስትሩ፥ ግብጽ ተጨባጭ ያልሆኑ ክሶችን ከማቅረብ ይልቅ በትብብር መንፈስ በጋራ ማዕቀፎች ተስማምታ መደራደር ያዋጣታል ሲሉ አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን የማልማትና የመጠቀም መብት ያላት ሉዓላዊ ሀገር በመሆኗ ከብልጽግና ጉዞዋ በተቃራኒ ለቆሙ ኃይሎች ቦታ የላትም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

5️⃣  !በሁሉም የሀገራችን ማዕዘናት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጸናች ኢትዮጵያ ያላቸውን ጠንካራ አንድነት እና የጋራ ኃላፊነት በሚያንጸባርቀው፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሥር ለታሪካዊው ሀ...
29/07/2026

5️⃣ !
በሁሉም የሀገራችን ማዕዘናት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጸናች ኢትዮጵያ ያላቸውን ጠንካራ አንድነት እና የጋራ ኃላፊነት በሚያንጸባርቀው፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሥር ለታሪካዊው ሀገራዊ ዘመቻ በጋራ በመሰብሰብ በአንድ ቀን 800 ሚሊዮን ችግኞችን ይተክላሉ።

📅 ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

እርሶም የዚህ ታሪካዊ ንቅናቄ አካል ይሁኑ!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

#ተስፋንእንትከል #አረንጓዴዐሻር

Address

Addise
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ተስፋ አለኝ በሀገሬ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category