የአቡነ ገብርኤል ትውልድ

የአቡነ ገብርኤል ትውልድ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአቡነ ገብርኤል ትውልድ, Grocers, �, Addis Ababa.

“እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። ማቴዎስ 16፥18
27/04/2025

“እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። ማቴዎስ 16፥18

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣም...
19/04/2025

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰብዓቱ ዓመተ ምሕረት፤

በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ኣምላክ አሜን!

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣
በትንሣኤው የሕይወት መንገድን ያሳየን ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤው በሰላም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“ወኣርኣይከኒ ፍኖተ ሕይወት፡- የሕይወትን መንገድ ኣሳየኸኝ” (መዝ.፲፭÷፱-፲፩)፤
ሕይወት በዓለመ ፍጡራን ውስጥ ከሚገኘው ድንቅ ነገር ሁሉ ተወዳዳሪ የሌላት ድንቅ ነገር ናት፤ ሕይወት ኣካልን የማንቀሳቀስ፣ የማመዛዘን፣ የመወሰንና የመስራት ሀብተ ጸጋ ያላት ልዩ ፍጥረት ናት፡፡

በዚህም ምክንያት ሕይወት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ወይም የሚመስል ጠባይ ኣላት፤ ሰው የእግዚአብሔር መልክና ኣምሳል ኣለው የሚለው መጽሓፍ ቅዱሳዊ ኣስተምህሮም ከዚሁ ጋር የሚስማማ ነው፤ ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ የተጣበቀ ወይም የተሳሰረ ግንኙነት ኣላት፤ “ወኅብእት ሕይወትክሙ ምስለ ክርስቶስ፡- ሕይወታችሁ ከክርስቶስ ጋር የተሳሰረች ናት” የሚለው ሐዋርያዊ አባባልም ይህንን ያመለክታል፡፡

ሕይወት ፈጣሪንና የፈጣሪ ርዳታን ስትሻ የመኖርዋ ምስጢርም ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝ ጸጋ ስላላት ነው፤ ሕይወት መልካም ስትሰራ ደስተኛ፣ ክፉ ስትሰራ ደግሞ ስቅቅተኛ የምትሆንበት ምክንያትም ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኛት ጸጋ ስለሚነግራት ነው፡፡ ምክንያቱም መልካምን መውደድ፣ ክፉን መጥላት የእግዚአብሔር የማይለወጥ ጠባይ ስለሆነ፣ ክፉን ሰርታ ከእርሱ ጋር በደስታና በነጻነት መኖር በፍጹም ኣትችልምና ነው፡፡

የመጀመሪያው ሰው ኣዳም ክፉውን ከሰራ በኋላ ወዲያውኑ መሸሸግና መደናገጥ ሊወረው የቻለው ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላት ውሳጣዊት ሕይወቱ ከእግዚአብሔር ጋር ኣብራ መቀጠል የማትችልበት ደረጃ እንደደረሰች ስለተረዳች ነው፡፡ ከዚህ ኣንጻር ሕይወት የመኖር ጸጋ ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ተሳስሮ የመኖር ጸጋም ያላት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

ሕይወት የማትጠፋ ብትሆንም የመሞት ስጋት ያልተለያት ፍጡር ናት፤ በተለይም እግዚአብሔርን የበደለች ዕለታ ከባድ የሞት ኣደጋ ያጋጥማታል፤ ይህም ሞት የሥጋ ሳይሆን ከእግዚአብሔርና የእግዚአብሔር ከሆነው ሁሉ መለየት ነው፤ የሕይወት ከባዱ ሞትም ይኽ ነው፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
እኛ ሰዎች በኃጢኣት ጠንቅ ያጣነው ሕይወት እንዳለ ቅዱስ መጽሓፍ “በኣንድ ሰው በደል ኃጢኣት ወደ ዓለም ገባ፤ በዚህም ምክንያት ሰው ሁሉ ሞተ ወይም ከእግዚአብሔር ተለየ” በማለት የእኛ ከእግዚአብሔር መለየት ዋናው ሞት እንደሆነ ያስረዳል፡፡ይህ ገለጻ ከእግዚአብሔር ጋር የመኖር ሕይወታችን በበደል ምክንያት ማጣታችንን የሚያሳይ ነው፡፡ እኛ በደለኞች ሆነን ከእግዚአብሔር የተለየንበት የመጀመሪያው ምክንያት በደለኞች ከሆኑ ኣዳምና ሔዋን የተገኘን መሆናችን ነው፡፡

በመሆኑም የሁላችንም ሥጋዊና መንፈሳዊ ኣካል የተከፈለው ከነሱ እንደመሆኑ መጠን ያለን ሁሉ እንደነሱ ቀድሞውኑ የሞተና

ለአንዳንድ ሰዎች የይሁዳ ክፋት የገባቸውን ያህል የክርስቶስ ፍቅር የገባቸው አይመስለኝምምክንያቱም ሰፊውን ትንተናቸውን የሚወስድባቸው የክርስቶስ ጉዳይ ሳይሆን የይሁዳ ጉዳይ ነው በጥቅሉ የነዚ...
19/04/2025

ለአንዳንድ ሰዎች የይሁዳ ክፋት የገባቸውን ያህል የክርስቶስ ፍቅር የገባቸው አይመስለኝም
ምክንያቱም ሰፊውን ትንተናቸውን የሚወስድባቸው የክርስቶስ ጉዳይ ሳይሆን የይሁዳ ጉዳይ ነው በጥቅሉ የነዚህ ሰዎች አጀንዳ ይሁዳ እንጂ ክርስቶስ አይመስልም ወዳጆቼ ይሁዳ ላይ ሳይሆን መስቀሉ ላይ እንጣበቅ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለ ነገረ መስቀሉ ሲጽፍ ይሁዳንም ሆነ አይሁድን የጽሁፉ አካል አላደረጋቸውም ስለ ተሰቃየው መሲህ ጀመረ ስለ እርሱ ብቻ ተርኮ ጨረሰው።
"እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን"(1ቆሮ 1÷23)

Inni garuu balleessaa keenyaaf ni waraaname,sababii yakka keenyaafis reebamee ni caccabsame;nuyi nagaa akka argannuufinn...
18/04/2025

Inni garuu balleessaa keenyaaf ni waraaname,
sababii yakka keenyaafis reebamee ni caccabsame;
nuyi nagaa akka argannuuf
inni ni adabame,
madaa'uu isaatiinis fayyinni
nuuf argame. Isay 53:5
Gooftaa sababa cubbuu keenyaaf fannifameef Galanni ha ta'u!

Ani barsiisaan keessanii fi gooftaan keessan ergan miilla isiniif dhiqee, isin immoo miilla walii walii keessaniif dhiqu...
17/04/2025

Ani barsiisaan keessanii fi gooftaan keessan ergan miilla isiniif dhiqee, isin immoo miilla walii walii keessaniif dhiquun isiniif in ta'a.

15 Ani akkuman isiniif godhe, isinis immoo akka gootanitti fakkeenya isiniif ta'eera, 16 Dhuguma, dhuguman isinitti hima, hojjetaan isa isa hojjechiifatu irra hin caalu, inni ergames isa ergate irra hin caalu. (Yoh 13:12)

ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና ከ፲ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተ...
15/04/2025

ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና ከ፲ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል።

ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና ማግኘታቸውን የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ገልጸዋል።

ምንጭ ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Address


Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአቡነ ገብርኤል ትውልድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category