Akaki Woreda 4 Cooperative office አቃቂ ወረዳ 4 ህብረት ስራ ጽ/ቤት

Akaki Woreda 4 Cooperative office
አቃቂ ወረዳ 4 ህብረት ስራ ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Akaki Woreda 4 Cooperative office
አቃቂ ወረዳ 4 ህብረት ስራ ጽ/ቤት, Grocers, Addis Ababa.

 !!*********ሚያዝያ 05/08/2018 ዓ.ም*******በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ስራ ጽ/ቤት ወርቃማ ሰኞን በአብሮነት ቀን ከጽ/ቤቱ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር የመልካም ...
13/04/2026

!!
*********ሚያዝያ 05/08/2018 ዓ.ም*******
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ስራ ጽ/ቤት ወርቃማ ሰኞን በአብሮነት ቀን ከጽ/ቤቱ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር የመልካም ተሞክሮ እና ልምድ ልውውጥ ተደርጓል።

ለትንሳኤ በዓል ዝግጅት፡ በወረዳ 4 የሸቀጦች አቅርቦት ተጠናክሮ ቀጥሏል # # # # # # # # የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር፣ የትንሳኤ በዓልን በድምቀት ለማክበር የሚያስ...
09/04/2026

ለትንሳኤ በዓል ዝግጅት፡ በወረዳ 4 የሸቀጦች አቅርቦት ተጠናክሮ ቀጥሏል
# # # # # # # #

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር፣ የትንሳኤ በዓልን በድምቀት ለማክበር የሚያስችሉ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለህብረተሰቡ በበቂ ሁኔታ እየቀረቡ መሆናቸውን አስታወቀ።

የወረዳው አስተዳደር እንደገለጸው፣ በዓሉን ታሳቢ በማድረግ የሸማች ማህበራት እና የንግድ ተቋማት አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን ያለ ምንም የዋጋ ጭማሪ እና የንግድ ወከባ ለነዋሪው እንዲያቀርቡ ክትትል እየተደረገ ይገኛል። በተለይም የግብርና ምርቶች፣ የኢንዱስትሪ ውጤቶች እና ሌሎች ለበዓል አስፈላጊ ግብዓቶች በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ መስተጓጎል እንዳይኖርባቸው ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።

ነዋሪው ጥራቱን የጠበቀ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው። ይህም ለበዓሉ አከባበር ሰላማዊ እና ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም በላይ፣ የኑሮ ጫናን በመቀነስ ረገድ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል።

አስተዳደሩ አክሎም፣ ነዋሪዎች የህግ እና የሰላም ደንቦችን በመጠበቅ በዓሉን በሰላም እንዲያሳልፉ ጥሪውን አስተላልፏል።

ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም

06/04/2026
የኮንድምንየም የጋራ መኖርያ ህብረት ስራ ማህበራት ከመንግስት ጋር በጋራ በመሆን የስራ ፈላጊዎችን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ መንግስት ባመቻቸዉ የመስሪያ ቦታ ተደራጅተዉ ለመስራት እና  ህይወ...
04/04/2026

የኮንድምንየም የጋራ መኖርያ ህብረት ስራ ማህበራት ከመንግስት ጋር በጋራ በመሆን የስራ ፈላጊዎችን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ መንግስት ባመቻቸዉ የመስሪያ ቦታ ተደራጅተዉ ለመስራት እና ህይወታቸዉን ለመቀየር ያላቸዉን ቁርጠኝነት ተጠቃሚዎች ገለፁ።
*********** 26/07/2018 ዓ.ም************

በከተማችን የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍና ዜጎች በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የታለሙ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል። ከእነዚህ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነውና በፋሚሊ ቢዝነስ መርህ የተደራጁ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የሥራ ማስጀመሪያ ኮንቴነሮች የምረቃና የማስረከብ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ በይፋ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ተከናውኗል።

ይህ የሥራ ዕድል ፈጠራ መርሃ-ግብር በተለይ የቤተሰብን አቅም በማቀናጀት ላይ ትኩረት ማድረጉ ለየት የሚያደርገው ሲሆን፣ ለተጠቃሚዎች የተላለፉት የንግድ ኮንቴነሮችም ዜጎች ከዚህ ቀደም ይገጥማቸው የነበረውን የመስሪያ ቦታ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀርፉ ናቸው። ይህም ተጠቃሚዎች ያለምንም ስጋት በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ በመግባት ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉና የኑሮ ሁኔታቸውን እንዲያሻሽሉ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

በዛሬው ዕለት በኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤት ለሚኖሩ ነዋሪዎይ ከ20 በላይ ማህበራት በስራቸው ከ60 በላይ አንቀሳቃሾችን ያቀፈ በፋሚሊ ቢዝነስ በማደራጀት የንግድ ቦታዎች አስመርቆ አስረክቧል።

የንግድ ቦታዎች የዜጎችን የሥራ አጥነት ቅሬታ ከመቅረፍ ባለፈ፣ በየአካባቢያቸው የሚታየውን የንግድ እንቅስቃሴ በማቀላጠፍ ለከተማዋ የኢኮኖሚ እድገት የራሳቸውን አዎንታዊ አሻራ እንደሚያሳርፉ ይጠበቃል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደርም እንዲህ ያሉ የንግድ ዘርፎችን በመደገፍ ዜጎችን የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

 #የኮንድምንየም ማህበራት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ጀምረዋል!!      **********15/07/2018***********በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ...
24/03/2026

#የኮንድምንየም ማህበራት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ጀምረዋል!!
**********15/07/2018***********
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ስራ ጽ/ቤት ድጋፍና ክትትል ከሚየደርጋቸው ተቋማት አንዱ የጋራ መኖርያ ቤቶች (ኮንድምንየም ማህበራት) የመኖርያ አከባቢያቸውን ምቹና ሳቢ ብሎም ማራኪ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር የመረጃ አደረጃጀታቸውንም አዲስ በበለጸገው የእፎይ ፕላስ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት የመድረግ ስራቸውን ጀምረዋል።
🎤ምንጭ አቃቂ ወረዳ 4 ህብረት ስራ ጽ/ቤት

 !!የወረዳ 4 ነዋሪዎች ሸማቾች ህብረት ኃላ/የተ/የህብረት ስራ ማህበር በሰንበት ገበያ ላይ የተለያዩ ምርቶችን ለገበያ አቅርቧል። 12/07/2018 ዓ.ም
21/03/2026

!!
የወረዳ 4 ነዋሪዎች ሸማቾች ህብረት ኃላ/የተ/የህብረት ስራ ማህበር በሰንበት ገበያ ላይ የተለያዩ ምርቶችን ለገበያ አቅርቧል። 12/07/2018 ዓ.ም

21/03/2026

Quality products at reasonable prices for citizens!!

21/03/2026

ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ "ለዜጎች"!!

በተለያየ ምክንያት ፈርሶ የጠፋ የመንግስት (የቀበሌ) ቤት በተደረገ ማጣራት እንዲገኝ እና ለተፈቀደላቸው ግለሰቦች የማስረከብ ስራ ተሰርቷል።********************************...
14/02/2025

በተለያየ ምክንያት ፈርሶ የጠፋ የመንግስት (የቀበሌ) ቤት በተደረገ ማጣራት እንዲገኝ እና ለተፈቀደላቸው ግለሰቦች የማስረከብ ስራ ተሰርቷል።
***************************************
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቤቶች አስተዳደር
07/06/2017 ዓ.ም
****************************************
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቤቶች አስተዳደር ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ምክንያት ፈርሶ የጠፋ 2 የቀበሌ ቤት ከቤቱ ተወራሽ በነበሩት ግለሰቦች ይዞታ ጋር በመቀላቀል ለረጅም ጊዜ ሲገለገሉበት የነበሩ ቤቶችን በማጥራት ሂደት ተገኝቷል። ነገር ግን ተወራሽ የነበሩት ግለሰቦች በተደጋጋሚ ለማስረከብ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የፌ/የመ/ደ/ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ለወረዳው መንግስት ቤቶች አስተዳደር በወሰነው ውሳኔ መሠረት በቀን 07/06/2017 ዓ. ም ከጸጥታ አካላት ፣ ደንብ ማስከበር፣የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት አስተዳደር ቡድን መሪ፣ ባለሙያ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ለተፈቀደላቸው ግለሰቦች የማስረከብ ስራ ተሰርቷል።
የወረዳው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ትዝታ ነጋሽ አክለውም በተለያዩ ምክንያቶች የፈረሱ፣ በህገወጥ አካላት የተያዙ እና የጠፉ የመንግስት (የቀበሌ) ቤቶች ስለሚኖሩ ነዋሪዎች የዘውትር ጥቆማቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው እና የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡም በአደራ ጭምር አሳስበዋል።

Address

Addis Ababa
INNERCITYOFKALITY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akaki Woreda 4 Cooperative office አቃቂ ወረዳ 4 ህብረት ስራ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category