Faris mudin ፋሪስ

Faris mudin ፋሪስ በኣላህ ፍቃድበኣንድነት እና በፍቅር እጅ ለእጅ ተያይዘን ከፍ እንላለን

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ በደረሰዉ ድንገተኛ የጀልባ መስመጥ አደጋ ጥልቅ ኀዘኔን እገልፃለሁ::♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️Far...
21/05/2026

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ
በደረሰዉ ድንገተኛ የጀልባ መስመጥ አደጋ ጥልቅ ኀዘኔን እገልፃለሁ::
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️
Faris Mudin
ዛሬ ግንቦት 13/218 አመታዊ የዋዜማ በዓል ለማክበር በጣና ሐይቅ ላይ በጉዞ የነበሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ጀልባዋ በድንገት በመስመጧ በርካቶች ሕይወታቸዉን ማጣታቸዉን ሰምተናል::

በዚህ አስከፊ የወገኖቻችን አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እየገለጽን፣ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
Facebook for Creators Faris mudin ፋሪስ BBC News FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር

ከዚህ ተማሩ‼የሎተሪ ሿሿ!Faris mudin ፋሪስ ትናንት ረቡዕ ረፋድ ሜክሲኮ ጋ የታሸገ ፖስታ በእጇ የያዘችና ግራ የተጋባች ልጅ ገጠመችኝ። "እስቲ ስልክ ደውልልኝ" አለች በመደናገጥ ስሜት...
07/05/2026

ከዚህ ተማሩ‼

የሎተሪ ሿሿ!
Faris mudin ፋሪስ

ትናንት ረቡዕ ረፋድ ሜክሲኮ ጋ የታሸገ ፖስታ በእጇ የያዘችና ግራ የተጋባች ልጅ ገጠመችኝ። "እስቲ ስልክ ደውልልኝ" አለች በመደናገጥ ስሜት። እየተርበተበተች ቁጥሩን ነገረችኝ። ሞከርኩት "ስልኩ ዝግ ነው ይላል።
ሌላም ተለዋጭ ቁጥር ሰጠችኝ። እሱም ዝግ ነው።
" ኧረ ወይኔ ጉዴ . . . እስኪ ደግመህ ሞክርልኝ ጋሽዬ" አለች። ሞከርኩት። ለውጥ የለም። ላረጋጋጋት እየሞከርኩ የሆነችውን ጠየኳት።

"ሎተሪ ደርሶናል። ግን መታወቂያ የለንም" ያሉ የገጠር ልብስ የለበሱ፣ በገጠር ዘዬ የሚናገሩ 2 ልጆች "የሎተሪ ብር ተቀበይልን አሉኝ። ታሽጎ በቼክ ተሰጥቶን ነው። እኛ ማውጣት ስለማንችል አንቺ አውጪልን" ሲሉ ለመኑኝ።

"እሺ ከቻልኩ ምን ገዶኝ!" አልኳቸው። የሎተሪው ብር በቼክ ተጽፎ እዚህ ፖስታ ውስጥ ነው ያለው። ባንኩ ብቻ ነው መክፈት የሚችለው" ብለው ፈራ ተባ እያሉ የታሸገ ፖስታውን ሰጡኝ።

አንደኛው ግን "የኔ እህት ይቅርታ የምታወጪው ብር ብዙ ነው ከ250 ሺህ በላይ ነው በዚያው እብስ ብትይስ እንዴት እንመንሽ?" አለኝ።

"ችግር የለውም . . . ሀሳብ ከገባህ ስልኬን ያዙ" ስል አንዱ እሺ ብሎ ስልኬን ተቀበለ። ሌላኛው ግን "አይሆንም ያንሳል። ያን ሁሉ ብር እንዴት እንዲሁ በብላሽ . . . " ብሎ ተከራከረ።

ብሩን ካወጣሁላቸው 50 ሺህ ብር እንደሚሰጡኝ ቃል ገቡልኝ። ወደ ባንክ ልገባ ስል አንዱ "አይ አይሆንም . . . ብር ካላት ትስጠን" አለ።

"በእጄ ጥሬ ብር የለም" ስላቸው . . . በቃ በስልክሽ ትራንስፈር አድርጊልን" አሉኝ። ይሉኝታ እየያዘኝ እንዲያምኑኝ ስል በአካውንቴ ያለውን 17 ሺህ ብር በሙሉ በአካውንታቸው አስገባሁ።

እነሱ ውጪ እየጠበቁኝ። እኔ ወደ ባንክ ገባሁ። ከሁለት ሶስት ሰው ወረፋ በኋላ የሰጡኝን ሎተሪ እና የታሸገውን ፖስታ ለባንከሯ እየሰጠሁ የሎተሪ ብር እንድትሰጠኝ ስጠይቃት። "የኔ እህት እንዲህ ዓይነት አሰራር የለንም። ሎተሪውን ለብሔራዊ ሎተሪ ትሰጫለሽ። እነሱ ብሩን በአካውንትሽ ያስገባሉ" አለችኝ።

እንዳልተሳካ ልነግራቸው ስወጣ ልጆቹ በስፍራው የሉም። ይኸው ፖስታና ሎተሪ ወረቀት ይዤ ቀረሁ ብላ ፖስታውን ስንከፍተው ባዶ ምንም ያልተጻፈበት ነጭ ወረቀት ብቻ ነው ያለው።

ክው. . . ድርቅ. . . ብትልም የስልክ ቁጥሮችን ለማስታልወስ አልተቸገረችም። የሷ ስልክ ወዲያው ተዘግቷል። ሲደወል ዝግ ነው ይላል። ሌላ ቦታ ደውላ የሆነችውን በኔ ስልክ አስረዳች።

እኔም ተረጋጊ አንዴ ተበልተሻል። ወደ ቤትሽ ሂጂ ብዬ የትራንስፖርት ሰጥቼ ተሰናበትኳት።
ይሄ የሎተሪ ሿሿ በፊትም የነበረ ቢሆንም አሁን መልኩንና አይነቱን እየቀየረ መጥቷልና ሁላችንም እንጠንቀቅ!
Facebook for Creators Faris Mudin BBC News

29/04/2026

በናፍጣ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት ተከስቶ የነበረው የታሪፍ ጭማሪ እንዲቆምና የትራንስፖርት አገልግሎቱ ወደ ቀድሞ ዋጋው እንዲመለስ ውሳኔ ተላልፏል።
መንግስት ጥሩ ሲሰራ ማመስገን ይለመድ ባይ ነን🙏»

ድርድሩ ተጀመረ!**************Faris mudin ፋሪስ ጦርነቱን በዲፕሎማሲ ለመፍታት የአሜሪካና የኢራን ልዑካን በፓኪስታን የሚያደርጉት ድርድር ተጀመረ። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ...
11/04/2026

ድርድሩ ተጀመረ!
**************
Faris mudin ፋሪስ

ጦርነቱን በዲፕሎማሲ ለመፍታት የአሜሪካና የኢራን ልዑካን በፓኪስታን የሚያደርጉት ድርድር ተጀመረ። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚመሩት የከፍተኛ ባለስልጣናት ቡድን በኢስላማባድ የሰላም ውይይት ጀምረዋል። ለአንድ ወር ተኩል ያህል የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት፣ አሜሪካና ኢራን በፓኪስታን ዋና ከተማ ፊት ለፊት ተቀምጠው መነጋገር ጀምረዋል።

የኢራን መገናኛ ብዙኃንና አልጀዚራ እንደዘገቡት ከሆነ፣ ይህ ወሳኝ ውይይት የተጀመረው ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ነው። የሰላም ንግግሩ ከመጀመሩ አስቀድሞ ሁለቱ ወገኖች ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ ጋር ለየብቻቸው ተገናኝተው መክረዋል። ይህ በኢስላማባድ እየተካሄደ ያለው ንግግር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግጭት ሙሉ ለሙሉ ለመቋጨት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት እርምጃ ሆኖ ተወስዷል።

Facebook for Creators Faris Mudin Al Jazeera English Perú21

Faris mudin ፋሪስ Ethiopia Today, the violence against Muslim guests is a crime. A foreigner, due to his faith, is executi...
10/04/2026

Faris mudin ፋሪስ Ethiopia Today, the violence against Muslim guests is a crime. A foreigner, due to his faith, is executing a system of oppression and taking violent action. What kind of human morality is that??

No, just like the country, just like the Tigray region, peace and stability are important, and the government should either restore that peace or leave it as a historical record.

This ongoing oppression against Ethiopian Muslims, which has been causing suffering for a long time, should not be ignored or dismissed as just the issue. It needs to be addressed every time.

Justice for the Axum Muslims!!

#አክሱም በዛሬው ዕለት ሙስሊም ሰጋጆች ላይ የተፈፀመ ግፍ ነው ዜጋ በሀገሩ በቀዬው በእምነቱ ምክኒያት የአምልኮ ስርዓቱን ሲፈጽም የሃይል እርምጃ መውሰድ ምን አይነት የሰውኛ ሞራል ቢኖራቸው ይሆን ??

አይደለም እንደ ሀገር እንደ ክልል ለትግራይ ክልል ሰላም ጠንቅ የሆነው ህውሓትን መንግስት ስርዓት ሊያሲዘው ወይም ታሪክ ሆኖ እንዲቀር ሊያደርገው ይገባል ።

ይህ የህዋሃት አገዛዝ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ በይደር ያቆየውን ቂም ድሮም ሲያሰቃየው የከረመው መልኩን እየቀያየረ በየግዜው ሊወጣ አይገባም ።
ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች !!
Iran International - English Facebook for Creators Faris Mudin Al Jazeera English CNN BBC News e.tv Ustaz Wadi Annuar Ustaz Ahmad Dusuki Abd Rani

አሜሪካ ለጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ የተቀበለቻቸው 10ሩ የኢራን መደራደሪያዎች ምንድን ናቸው?Faris mudin ፋሪስ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ልየኢራን ከፍተኛው ብሔራዊ የጸጥታው ምክር ቤት ...
08/04/2026

አሜሪካ ለጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ የተቀበለቻቸው 10ሩ የኢራን መደራደሪያዎች ምንድን ናቸው?

Faris mudin ፋሪስ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ል

የኢራን ከፍተኛው ብሔራዊ የጸጥታው ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካ "አሳፋሪ" የተባለ ሽንፈትን አምና በመቀበል፣ ቴህራን ጦርነቱን ለማቆም ያቀረበቻቸውን 10ሩንም ቅድመ ሁኔታዎች ለመቀበል መስማማቷን አስታውቋል።

አሜሪካ በይፋ ተቀብላቸዋለች የተባሉት 10ሩ የኢራን መደራደሪያ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

1. በኢራን ላይ ዳግም ወታደራዊ ጥቃት ላለመሰንዘር ቃል መግባት

2. ኢራን በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ያላትን ሙሉ ቁጥጥር እንድታስቀጥል መፍቀድ።

3. የኢራንን የዩራኒየም ማበልጸግ መብት ሙሉ በሙሉ እውቅና መስጠትና መቀበል።

4. በአሜሪካ የተጣሉትን ቀዳሚ ማዕቀቦች በሙሉ ማንሳት።

5. በኢራን ላይ የተጣሉትን ማንኛቸውንም ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀቦች ማንሳት።

6. የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በኢራን ላይ ያሳለፋቸውን የውሳኔ ሐሳቦች በሙሉ መሰረዝ።

7. የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) የቦርድ ውሳኔዎች በሙሉ እንዲቋረጡ ማድረግ።

8. አሜሪካ በጦርነቱ ለደረሰው ጉዳት ለኢራን የካሳ ክፍያ እንድትፈጽም መስማማት።

9. የአሜሪካ ተዋጊ ኃይሎች ከመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ማድረግ።

10. በሁሉም ግንባሮች እየተካሄደ ያለው ጦርነትና ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ማድረግ።

የኢራን ከፍተኛው ብሔራዊ የጸጥታው ምክር ቤት እንደገለጸው፤ ይህ ስምምነት የኢራን ጀግኖች ጠላትን ወደ ታሪካዊ ሽንፈት ያስገቡበትና የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩበት ታላቅ ድል ነው።

አሜሪካ እነዚህን ነጥቦች ለጊዜያዊ የተኩስ አቁምም ቢሆን ለመቀበል መገደዷ በቀጠናው ያለውን የኃይል ሚዛን የሚቀይር ክስተት መሆኑም ተነግሯል
Faris Mudin Iran International - English Facebook for Creators Al Jazeera English

"ዛሬ ምሽት አንድ ሙሉ ስልጣኔ ይጠፋል" ሲሉ ትራምፕ ያስተላለፉትን ማስጠንቀቂያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አወገዙ። Faris mudin ፋሪስ በኢራን ህዝብ ላይ የሚሰነዘሩ ዛቻዎች "ተቀባይነት...
07/04/2026

"ዛሬ ምሽት አንድ ሙሉ ስልጣኔ ይጠፋል" ሲሉ ትራምፕ ያስተላለፉትን ማስጠንቀቂያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አወገዙ።
Faris mudin ፋሪስ
በኢራን ህዝብ ላይ የሚሰነዘሩ ዛቻዎች "ተቀባይነት የሌላቸው" መሆናቸውን በመግለጽ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎች እየተስፋፋ ያለውን ቀጠናዊ ጦርነት እንዲያስቆሙ የሀገሮቻቸውን የፖለቲካ መሪዎች እንዲወተውቱ አሳስበዋል።
Faris Mudin Facebook for Creators Iran International - English Al Jazeera English

Faris mudin ፋሪስ  የኢራን መንግስት ከአሜሪካ ጋር ሲያደርግ የነበረውን ማንኛውንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ እንዲሁም ቀጥተኛ ያልሆኑ ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን በይፋ አስታውቋል። 'ቴ...
07/04/2026

Faris mudin ፋሪስ የኢራን መንግስት ከአሜሪካ ጋር ሲያደርግ የነበረውን ማንኛውንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ እንዲሁም ቀጥተኛ ያልሆኑ ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን በይፋ አስታውቋል። 'ቴህራን ታይምስ' ይዞት በወጣው ዘገባ መሰረት፣ ይህ የቴህራን ከረር ያለ ውሳኔ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ዛሬ ሌሊት አንድ ሙሉ ስልጣኔ ይጠፋል" በማለት የሰነዘሩትን እጅግ አስደንጋጭ ዛቻ ተከትሎ ነው።

የኢራን መንግስቱ ጦርነቱን በሰላም ለማስቆም በማሰብ ሲካሄዱ የነበሩ ድርድሮች እና ንግግሮች በሙሉ እንዲቋረጡ ጠንካራ ውሳኔ አሳልፏል። ከዚህም ባሻገር፣ ቴህራን ለዋሽንግተን እና አጋሮቿ "ከጥንታዊው የኢራን ስልጣኔ ታሪክ የማይረሳ እና ከባድ ምት ያጋጥማችኋል" በማለት የሞት ሽረት ማስጠንቀቂያዋን አስተላልፋለች።

የዲፕሎማሲ በሮች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸው የሚያሳየው የመጀመሪያው ትልቅ እውነታ፣ ሁለቱ ሀገራት ከቃላት እና ከዛቻ ጦርነት ወጥተው ወደ ለየለት እና ወደማይቀለበስ አውዳሚ ወታደራዊ ፍጥጫ መግባታቸውን ነው። ከዚህ ቀደም በሶስተኛ ወገኖች (እንደ ኳታር እና ኦማን ባሉ ሀገራት) በኩል ይደረጉ የነበሩ ቀጥተኛ ያልሆኑ የሰላም ንግግሮች መቋረጣቸው፣ ጦርነቱን በድርድር የመፍታት ተስፋን ሙሉ በሙሉ ያጨልመዋል።

በሁለተኛ ደረጃ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የ"ስልጣኔን የማጥፋት" ዛቻ በኢራን በኩል የተወሰደው እንደ ትልቅ ብሄራዊ የህልውና አደጋ ነው። በመሆኑም ቴህራን "የጥንታዊ ስልጣኔያችን የማይረሳ ምት" የሚል አጸፋዊ ምላሽ መስጠቷ፣ ኢራን ያላትን የመጨረሻ ወታደራዊ አቅም እና በቀጠናው ያሏትን አጋር ታጣቂዎች በሙሉ ተጠቅማ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቅሞች ላይ የተቀናጀ፣ ምናልባትም ያልተጠበቀ ከባድ ጥቃት ለመሰንዘር መወሰኗን ያሳያል።

ይህ ውሳኔ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እና የነዳጅ ገበያውን ወደ ከፋ ድንጋጤ የሚከት ነው። የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤ በይፋ እንዲዘጋ እና የዓለም የነዳጅ አቅርቦት እንዲስተጓጎል የሚያደርግ ትልቅ የእርምጃ መጀመሪያ ሊሆን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይገምታሉ። በአጠቃላይ ሁኔታው ከመካከለኛው ምስራቅ አልፎ የዓለምን ደህንነት እና ኢኮኖሚ ወደማይወጣው አዘቅት ሊገፋው ከሚችልበት የመጨረሻው የገደል ጫፍ ላይ መድረሱን በግልጽ የሚያሳይ ክስተት ነው።
Faris Mudin
Facebook for Creators
Iran International - English

አስቸኳይ ሰበር ዜና፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላለፉFaris mudin ፋሪስ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ስትሬት (Strait of Hormu...
07/04/2026

አስቸኳይ ሰበር ዜና፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላለፉ
Faris mudin ፋሪስ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ስትሬት (Strait of Hormuz) እንዲከፈት የሰጡት የጊዜ ገደብ እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በኢራን ላይ እጅግ አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት የዛቻ መልዕክት፣ የሰጡት የጊዜ ገደብ ካለፈና መንገዱ ካልተከፈተ *አንድ ሙሉ ሥልጣኔ ዛሬ ምሽት ይጠፋል"ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህ ንግግር በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ከፍተኛ ውጥረት ወደ ከፋ ደረጃ ያሸጋገረ ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ጉዳዩን በስጋት እየተከታተለው ይገኛል።

1. ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ የባህር መስመርን እንድትከፍት ያስቀመጡት ገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተዋል።

2. የባህር መስመሩ ክፍት ካልሆነ አሜሪካ በኢራን ላይ እጅግ ከባድ የሆነ እርምጃ እንደምትወስድ በንግግራቸው አመልክተዋል።

ይህ ሁኔታ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ እና በጸጥታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።
Faris Mudin
Facebook for Creators
Iran International - English
Following

“ፈጣሪ የታላቁን የኢራን ህዝብ ይባርክ” በሚል የፍቅር ቃል የተቋጨው፣ የዶናልድ J ትራብ ፣ መርዛው ዛቻ፣Faris mudin ፋሪስ የታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ በፋርስ ምድር ጦርነ...
07/04/2026

“ፈጣሪ የታላቁን የኢራን ህዝብ ይባርክ” በሚል የፍቅር ቃል የተቋጨው፣ የዶናልድ J ትራብ ፣ መርዛው ዛቻ፣
Faris mudin ፋሪስ
የታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ በፋርስ ምድር ጦርነት የሚጀመረው በከበሮ ድምፅ ሳይሆን፣ በዝምታና በረቂቅ ስሌት ነው።

የዋሽንግተን መንግስትኢራን ታሪኳና ስልጣኔዋ ሊፋቁ ሰአቶችን እየጠበቀች ነው ሲል ፣አደገኛ የጦር ወንጀል ቅስቀሳውን ባደባባይ አሳውቋል::

በቴህራን አውራ ጎዳናዎች ላይ ደግሞ የጥንታዊቷ ፋርስ ( ኢራን) የጥበብና የትግስት መንፈስ ይታያል።

ኢራን ለዚህ "አብዮታዊ ለውጥ" የምትሰጠው ምላሽ እንደ ሸህራዛድ ተረት በብዙ ምዕራፎች የተከፈለ ነው። አገሪቱ ለዘመናት የቆየችው በኃይል ብቻ ሳይሆን በብልሃትም ጭምር ነው። እሱም
ስትራቴጂያዊ ትግስት" (Strategic Patience) የሚባለው መርኋ፣ ማዕበሉ እስኪያልፍ ራስን ዝቅ አድርጎ የመጠበቅ የኢራን ብቸኛ የጥበብ አቋሟ ነው።

ትራምፕ "ዛሬ ሌሊት የቴህራን፣ መሰረት ልማትና ታሪክ ፍፃሜው ይቋጫል አለ:: ኢራን ደግማ''ነገም ሌላ ቀን ነው" በሚል ረቂቅ ስሌት ትመልሳለች።
የኢራን ቃልቨወደፊት በምታደርገው፣ የጦርነት አቋሟ ላይ ሁሉም ነገር በመስታወት ምስል እንዳለ አድርጋ መወሰን ነው። ጫናው ሲበረታ፣ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ የነዳጅ ፍሰቱን የመገደብ ወይም በቀጠናው ያሉትን የአሜሪካ አጋሮችን በማጥቃት የማንቀሳቀስ "ቼዝ" ትጫወታለች። የፋርስ ምንጣፍ እንደሚሰራ ባለሙያ፣ እያንዳንዱን ክር በጥንቃቄ ትፈትላለች፤ በአንድ በኩል ዲፕሎማሲን እያሳየች፣ በሌላ በኩል ደግሞ የመከላከያ ጋሻዋን ታጠነክራለች። ለቴህራን ገዢዎች፣ የአሜሪካ ዛቻ አዲስ ታሪክ አይደለም። ይህንንም እንደ "ብሄራዊ ክብር" መመከቻ በማድረግ ህዝባቸውን ለማስተባበር ይጠቀሙበታል። ለኢራን መንግስት "የውጭ ወራሪ" የሚለው ትርክት ለውስጥ አንድነታቸው እንደ ሀይል ሆኖ ያገለግላቸዋል።

እናም የኢራን ምላሽ እንደ አንድ ውስብስብ ቅኔ ነው። ሰሙ "ሰላም እንፈልጋለን" ሲል፣ ወርቁ ግን "ለማንኛውም መስዋትነት ዝግጁ ነን" የሚል መልዕክት አለው። በአንድ በኩል የኒውክሌር ካርታዋን እንደ ማስፈራሪያ እየተጠቀመች፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከምስራቁ ዓለም በሚስጥር (ሩሲያና ቻይና) ጋር ያላትን ጥምረት በማጠናከር የአሜሪካን ማዕቀብና ጦርነት ለመቋቋም ትጥራለች።

የታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ በፋርስ ምድር ጦርነት የሚጀመረው በከበሮ ድምፅ ሳይሆን፣ በዝምታና በረቂቅ ስሌት ነው።
Faris Mudin Facebook for Creators Iran International - English

Address

ኣ/ኣ
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Faris mudin ፋሪስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category