22/03/2024
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታሪክ አሻራ የትውልድ የማይዘነጋ ደማቅ ታሪክ ነው። ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሻራውን ያላሳረፈ ኢትዮጵያዊ ከቶውንም አታገኝም። ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከተረፋቸው ሳይሆን ከምታስፈልጋቸው ቀንሰው የገነቡት ነው።
የኮልፌ ወጣቶች ሊግ መጋቢት 2016 ዓ.ም
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወጣቶች ሊግ በ13 ዙር አንደኛው ምዕራፍ የህዳሴው ግድብ የቦንድ አሰባሰብ ላይ ባስመወገበው የላቀ ውጤት ክፍለ ከተማው ላይ ካሉት ሁሉም ሴክተሮች በመቅደም ከተሰጠው እቅድ በላይ በመሠብሰብ የ1ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችላል።
በእለቱ የተገኙት አቶ ኢብራሂም መሀመድ የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራ ኢንተርፕራይዞች ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት የህዳሴ ግድብ የታሪካችን አሻራ የማንነታችን የላብ ፊርማ ያረፈበት ነው። ለዚህ ከፍተኛ የዘመቻ ተግባር አስተዋጽኦ ለነበራቸው የሊጉ አመራሮች እንዲሁም ወጣቶች ምስጋና አቅርበዋል በቀጣይ ለሚካሄደው ሁለተኛ ዙር ንቅናቄ ወጣቶች የበኩላቸውን አሻራ ማሳረፍ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡