Afela አፍላ

Afela አፍላ አፍላ ለፈጣን መረጀጃ

''ኢስላም ለፈጣሪ እጅን መስጠት እና በትእዛዙ ማደር ማለት ሲሆን
አምልኮትን ሁሉ በብቸኝነት ፍጹም ለአላህ ማድረግ ። ሌሎችን ፍጡራን የስልጣኑ ተጋሪ አለማድረግ፡ ይህን ዩኒቨረስ
ብቻውን የፈጠረለፍጡራን ሁሉ ሲሳያቸውን እሱ ብቻውን የሚመግብለስልጣኑ ተጋሪ ወይም እረዳት ተባባሪ የሌለው
ሃያል ጌታ መሆኑን ማመን። ነገ የትንሳኤ ቀን የፍርዱ ቀን ብቸኛ ባለቤት አላህ መሆኑን ማመን። ይህን ይመስላል
ብለን የምንመስልበት አምሳያ የሌለው ሃያል አምላክ አላህ በመባል ይታወቃል።
ኢስላም ማለት ለአላህ በመመሪያው በማደር ለትእዛዞቹ መንበርከክ ፡ እምነትን እና ልቦናን ለአላህ ፍጹም ማድረግ እና
ከአላህ ዘንድ የመጡ መመሪያዎችን በፍጹምነት ማ

መን ነው።
* አንድ ሰው ''ሙስሊም'' ነው ሊባል የሚቻለው የዚህ ግዙፍ አለም ሆነ ሌላ አለ የሚባለው አለም እና በውስጧ
ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ተቆጣጣሪ አስተናባሪ ብቸኛ አምላክ አላህ ነው ብሎ ማመን እና ነቢዩ ሙሃመድ የመጨረሻው
መልእክተኛ ናቸው ብሎ ማመን ነው። ይህም በሌላ አነጋገር በእውነት የሚያመልኩት አምላክ ከአላህ በስተቀር የለም።
ነብዩ ሙሐመድም(ሰላም ለእሳቸው ይሁንና) ባሪያው እና መላክተኛው ናቸው ብሎ ማመን ነው። ይህም በ አረብኛ
«''ላኢላሃ-ኢለሏህ ሙሃመድ ረሱሉሏህ''» በመባል ይታወቃል።
በዓለም ላይ የእምነቱ ተከታዮቹ ከ1.፮ ቢሊዮን በላይ ሆነው ይገኛሉ።
ሱና ማለት የነብዩ ሙሐመድ ንግግር እና ስራ/ስሩ ብለው ያዘዙት እና ሲሰራ እያዩ በዝምታያለፉት (አትስሩ ብለው
ያልከለከሉት) በአጠቃላይ በህይወታቸው የሰሩት ስራ እና እንዲሰራ ያዘዙት ሁሉ ሱና ይባላል።
ማንኛውም ሙስሊም ኢስላምን የሚተገብረው ከነብዩ ሙሐመድ በተማረው መሰረት ብቻ ነው። ኢስላም ሙሉ እምነት ስለሆነ
ከጊዜ ብዛት አነሰ ተብሎ የሚጨመርበት ወይም በዝቷል ተብሎ የሚቀነስለት ነገር የለውም።
- * ሙስሊሞች ለማንኛውም ቦታ እና ጊዜ/ዘመንየሚያገለገል ቁርዓን እና ሃዲስ የሚባል መመሪያ አላቸው። ይህን
መመሪያም ነብዩ ሙሐመድ ባስተማሯቸው ሱና መሰረት ይተገብሩታል።
እነዚህ የ እምነቱን ድንጋጌዎች የሚያስተምሩት መመሪያዎች ቁርአን እና ሃዲስ ሲሆኑ ቁርአን ማለት በ መልአኩ ጅብሪል
አማካኝነት ወደ መሃመድ በወህይ የተወረደ የአላህ ቃል ማለት ነው። ሃዲስ ማለት ደግሞ ነብዩ ሙሐመድ ንግግሮች
ናቸው ።
''ኢስላም'' የነብያት ሁሉ ሃይማኖት መሆኑን ሙስሊሞች ጠንቅቀው ያምናሉ።
ይህ በ መካ አሁን ያለው እና ካዕባ በመባል የሚታወቀው ግንብ በነብዩ ኢብራሂም አብርሃምእና
ልጃቸው ዒስማኤል የተሰራ ነው ብለው ሙስሊሞች ያምናሉ።
ከአላህ ሌላ ያለን ፍጡርም ይሁን ማንኛውም አይነት ነገር ማምለክ በኢስላም ታላቅ ወንጀል ነው።
ኢማን (የልብ ስራ)የእምነት 6 መሰረታዊ ነግሮችን አጠቃልሎ ይዟል።
:1ኛ በአላህ (በአምላክ ወይም በፈጣሪ) ማመን
:2ኛ መላእክት እንዳሉት ማመን
:3ኛ በ''ኪታቡ'' (በመጽሃፎች ማመን)
:4ኛ በ ''ሩሱሎች''(ነብያቶች ማመን)
:5ኛ በመጨረሻው ቀን የፍርድ ቀን (ሞቶ መነሳት) እንዳለ ማመን
:6ኛ በቀደር ማመንን
የሚሉት ሲሆኑ ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ናቸው።
የ''ኢስላም''የተግባር መሰረታዊ ነገሮች 5 ሲሆኑ
:1ኛ አላህ አንድ ነው ሙሀመድ መላክተኛ ነው ብሎ ማመን
:2ኛ ሰላት መስገድ
:3ኝ ዘካ ምጽዋት ማውጣት
:4ና ጾም መጾም
:5ኛ ሃጅ (መካን መጎብኘት)ማድረግ ናቸው።
ከላይ የኢማን መሰረቶች 6 ናቸው ብለናል በመጠኑም ቢሆን በዝርዝር ለማየት እንሞክር
1ኛ በአላህ ማመን ማለት ሲዘረዘር ይህን ዓለም ብቻውን የፈጠረ፡ ብቻውን የሚያስተዳድር እና የሚቆጣጠር፡
ለፍጡራን ሲሳይ የሚለግስ፡ አምላክ አላህ ነው ብሎ ማመን ማለት ነው።
ይህ አለም ካለ ፈጣሪ አልተገኘም። የሰው ልጅም ካለ አላማ ወደዚህ ምድር አልመጣም። ያመጣው አንድ ፈጣሪ
አለው።የመጣውም ለአላማ ነው። የመፈጠራችን አላማም ፈጣሪያችንን ለማምለክ ነው። ይህን አለም መጥኖ አስተካክሎ
የፈጠረው፡ ሰማይን ካለ ምሰሶ ያቆመው
ጸሃይ እና ጨረቃ እንዲሁም ለሊት እና ቀን ሌሎችንም ፕላኔቶች መስመራቸውን ይዘውጠብቀው እንዲጓዙ የሚያደርግ
አምላክ ፈጣሪ አስተናባሪ ተቆጣጣሪ/አላህ ነው ብሎ ማመን አንዱ የኢማን መሰረት ነው።
ከማንኛውም አይነት እንከን እና ጉድለት የጠራ/በሰው ልጅ ላይ የሚታዩ የድክመት ምልክቶች ፍጹም የማይታዩበት
፡የማይበላ እና የማይጠጣ የማይወልድ የማይወለድ ፍጹም የ እሱም ቢጤም ሆነ አምሳያ ስለሌለው ይህን ይመስላል ብለን
ልንመስለው የማንችል ሃያሉ አምላክ አላህ ነው ብሎ ማመን ።
- * እሱ ለምን ሰራህ ተብሎ ሊጠየቅ የማይችል እሱ ግን የፈለገውን የሚሰራ እና የሚጠይቅየሚምር
የሚቀጣ/የሚፈጥር የሚገድል/የሚያስታምም የሚያድን/ የፈለገውን ሰሪ ብቻውን ቀሪ የፍርዱ ቀን ባለቤት አላህ ነው ብሎ
ማመን አስፈላጊ እና የግድ ነው።
2ኛ በመላእክት(በመላኢኮች ማመን) ከብርሃን የተፈጠሩ የማይበሉ የማይጠጡ ከተፈጠሩ ጀምሮ የፈጣሪን ትእዛዝ ብቻ
በመተግበር ላይ የሚዘወትሩ፡ መላእክት አሉት ብሎ ማመን የግድ ሲሆን ከነዚህ መላእክት ዋናዋናዎች ጂብሪል ሜካኤል
ኤስራፊል...የመሳሰሉት ይገኙበታል።
እነዚህ መላእክት ከራሳቸው ምንም ማድረግ የማይችሉ የማይጠቅሙ እና የማይጎዱ በመሆናቸው አምልኮ ለነሱ ተገቢ
አይደለም። እነሱ ፈጣሪያቸውን ሌት ከቀን በቅንንነት ያመልካሉ ፡አመጸኞች አይደሉም። ተግባራቸው የተለያየ ነው።
በጣም ትልቅ ፍጥረት ናቸው። ጅብሪል የሚባለው መላእክት 700 ክንፎች ሲኖሩት አንዱ ክንፍ ብቻ ሲዘረጋ ከጀምበር
መግቢያ እስከ መውጫ ይደርሳል። ይህ የሚያሳየው የ እነዚህ ፈጣሪ ምን ያህል ታላቅ መሆኑን ነው አሏሁ አክበር!!!

04/11/2025

Watch, follow, and discover more trending content.

የተወሰደውን ሀብታችንን መጠየቅ ህጋዊና ተፈጥሯዊ መብታችን ነው።
01/11/2025

የተወሰደውን ሀብታችንን መጠየቅ ህጋዊና ተፈጥሯዊ መብታችን ነው።

Check out Afela’s video.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-👉 ኢትዮጵያ ትልቁ የምታወጣው ወጪ ለማ...
28/10/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 ኢትዮጵያ ትልቁ የምታወጣው ወጪ ለማዳበሪያ እና ነዳጅ ነው፤

👉 ዳንጎቴ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያለማው የማዳበሪያ ፋብሪካ 30 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ የሚያመርት ነው፣

👉 ቢሾፍቱ የሚሰራው አየር መንገድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያመጣል፤ አየር መንገዱ ከ100 ሚሊየን በላይ ተጓዦችን በዓመት የሚያስተናግድ በመሆኑ ከአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ይሆናል፣

👉 እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የቤት ባለቤት እንዲሆን ማድረግ የሚቻል አይደለም፤ ቢያንስ ሁሉም ሰው የኪራይ ቤት እንዳያጣ ማድረግ ያስፈልጋል፣

👉 የኮሪደር ልማት ዋና ዓላማው ያለንን ቦታ በአግባቡ እንድንጠቀም የሚያደርግ ነው፤ የኮሪደር ልማት የፈጠራ አቅም እና የኑሮ ዘዬን የቀየረ ነው፣

👉 አዲስ አበባ ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ ትንንሽ ስታዲየሞች ተገንብተዋል፤ የተገነቡት ትንንሽ ስታዲየሞች በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ተጫዋቾችን ያበረክታሉ።

28/10/2025

የቀይ ባሕር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልካዓ ምድራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን!! p.m Dr Abiy @

''ቀይ ባህር ያስፈልገናል'' በ2ሚሊዮን ህዝብ መታፈን የለብንም።  ''ፊልድ ማርሻል ብረሃኑ ጁላ''ፈልድ ማርሻሉ በ118ተኛው የሰራዊት ቀን ሲከበር ባስተላለፊት መልዕክት ''ቀይ ባህር ያስፈ...
26/10/2025

''ቀይ ባህር ያስፈልገናል'' በ2ሚሊዮን ህዝብ መታፈን የለብንም። ''ፊልድ ማርሻል ብረሃኑ ጁላ''

ፈልድ ማርሻሉ በ118ተኛው የሰራዊት ቀን ሲከበር ባስተላለፊት መልዕክት ''ቀይ ባህር ያስፈልገናል'' የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ10 አመት በሗላ 200 ሚሊዮን መሆኑ አይቀርም፤ እናም 200 ሚሊዮን ህዝብ በ2 ሚሊዮን ህዝብ መታፈን የለበትም በማለት ጠቆም አድርገው አልፈዋል።

አክለውም ኢትዮጵያ ሦስት ነገር ያስፈልጋታል፤ ሰላም፣ ልማትና የባሕር በር" በማለት በቦሌም በባሌም ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ትሆናለች ብለዋል።

የፊልድ ማርሻሉን ሃሳብ እንደት ያዩታል?

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ አስክሬን በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ...
26/10/2025

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ አስክሬን በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ
ይቀንስልህ አልነበር? ሲል ጠየቀው።

ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም አለው

ያን ጌዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ..... ስሜቱ በጣም ተነካ ዓይኖቺ በዕንባ ታጠቦ።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል የወንድማማችነት የአንድነት ተምሳሌት ሆነ

እናም ..... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ

ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም!
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም!
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው!
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም!
ወንድምህ ቢስት በየዋህነት መንፈስ አቅናው!
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት።

26/10/2025

ለሁሉም ሙስሊም ኡማ:- ሰሞኑን በየ ሶሻል ሚዲያው የሚሰራጩ የውስጥ ጉዳዬችን ወደ አደባባይ የማውጣት እና ኡማውን ለሁለት የመሰንጠቅ አዝማሚያ ያላቸው መልዕክቶች መሰራጨታቸው በፍጥነት ይታረሙ።

20/10/2025

በሙፍቲ ህልፈት ብናዝንም ከቀደምት ሰለፎች የትዕግስት ቀንዲል ትምህርት ልንወስድ ይገባል ። ነብያችን(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባረፉ ወቅት የነበረዉን ክስተት መለስ ብለን ማስታወሱ ብርታትን ይቸረናል ።

ነብያችን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲያልፉ ብዙዎቹ ድንጋጤ ዉስጥ ገብተው ነበር። ከፊሎቹ አልሞቱም ብለዉ እስከ መሞገት ደርሰዋል ። የተቀሩት ደግሞ እግራቸው ለመቆም ምላሳቸው ለመናገር አቅም ገደደው።

ህልፈተ ዜናው የደረሳቸዉ አቡበክር ሲዲቅ ከእናታችን አዒሻ ቤት ገብተዉ ያንን በሻሻ ፊት ደጋግመው ሳሙት ። ከዚያዉ ወደ መስጂድ አመሩ ። ሰይድ ዑመር ከመስጂድ ዉስጥ እየተናገሩ ሳለ አቡበክር መናገር ጀመሩ ። የመስጂዱ ታዳሚ ትኩረቱን ወደ አቡበክር ሲዲቅ አዞረ። አቡበክር ሲዲቅም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ ፤

"من كان يعبد محمدا فإن محمدا قد مات ومن كان يعبد الله فإن الله حي لا يموت."

"ሙሐመድን የሚያመልክ ሰው ካለ መሐመድ በርግጥ ሞተዋል ። አላህን የሚያመልክ ሰው ግን አላህ ህያው ነው አይሞትም።

አስከትለዉም እንዲህ የሚለዉን የቁርዐን አያት አነበቡ ፡

وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ۚ أَفَإِن مَّاتَ أَوْ قُتِلَ انقَلَبْتُمْ عَلَىٰ أَعْقَابِكُمْ ۚ وَمَن يَنقَلِبْ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ فَلَن يَضُرَّ اللَّهَ شَيْئًا ۗ وَسَيَجْزِي اللَّهُ الشَّاكِرِينَ

“ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን ወደኋላው የሚገለበጥም ሰው አላህን ምንም አይጎዳም፡፡ አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል፡፡”

ይህንን የአቡበክር ሲዲቅ ንግግርን የሰሙ በሙሉ በነብያችን(ሶለለሁ ዐለይሂ ወሰለም) ህልፈት እርግጠኛ ሆኑ ። ይህንን የቁርዐን አያት ከአሁን በፊት ያልሰሙት እስከሚመስላቸዉ ድረስ በአዲስ ተቀባበሉት ።

እኛም በአቋማችን የፀናን ሆነን ሞትን ልንጠብቀው ይገባል። የሙፍቲያችን ከዱንያ መሻገር ለእርስዎ እረፍት ቢሆንም ትልቅ ክፍተት እንደሚፈጥር እሙን ነው። ቢሆንም ግን “እኔ አንድ ዑመር ብሔድ አሏህ ብዙ ዑመሮች አሉት” የሚለዉን ዘመን ተሻጋሪ ንንግራቸዉን መዘንጋት የለብንም ። አዎን አሏህ ብዙ ዑመሮች አሉት ። በሸይኻችን ማለፍ ክፍተት ይኖራል ብላቹ ላሰባችሁ በሙሉ የተጀመሩ የፅናት ጉዞዎች እንደማይደናቀፉ በአሏህ ስም ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

አባታችንን ሐጂ ዑመር ላይመለሱ ተሸኝተዋል ። አስተምህሮታቸዉን ማስቀጠል የጋራ ሓላፊነታችን ሆኗል። ሙፍቲ በዘመናቸዉ ከጣፋጭ የሐሪማ ኑረት እስከ አሳማሚ ግፍ ያካተተን የህይወት ዉጣ ዉረድን አስተናግደዋል ። ያለፉት ጥቂት አመታት ደስታን አልሰጧቸዉም ነበር ። “ዉስጣችን ነዷል እስኪ ሁላችንንም አሏህ ያሽረን” በሚለው ቃል አሏህን እስከመማፀን ደርሰዋል።

በጣም የሚያሳዝነው በህይወት ሳሉ ክብራቸውን የተጋፉ በእለት ሕልፈታቸው እንኳን አላረፉም። ሐገር የሀዘን ማቅ ተከናንቦ ባለበት ሁኔታ አብረዉ ማዘን ባይችሉ እንኳን ከክፋት አለመታቀባቸው መጪዉን ጊዜ በመልካም ለመገመት ያዳግታል ። በርግጥ ለዚህ ያበቃቸው ብልሹ አስተምህሮት በሌሎች ሐገራት ምን እያደረገ እንደሆነ ሁሉም ያዉቃል። እንዲህ ያሉ ከእምነትም ሆነ ከባህል ያፈነገጡ ብልሹ ምግባሮችን በጊዜ መከርከምና ማረቅ የሁሉም ኢትዮጲያዊ የጋራ ሐላፊነት ነው።


በስተመጨረሻም ለመላዉ የሙፍቲ ወዳጆች ሶብሩን ለሙፍቲ ደግሞ ጀነትን

Address

Kara Korie
Addis Ababa
ADDISABEBA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afela አፍላ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Afela አፍላ:

Share

Category