12/06/2026
ፖለቲካ የማኅበረሰብ ችግሮችን በመፍታት፣ የጋራ ከፍታን ለማረጋገጥ የሚከወን ነው:: ከጊዜያዊ ግብና ከሥልጣን ቆይታ በላይ ነው። ዘላቂ ግብና ዓላማን ያነገበ፣ አቧራን በማስነሣት ከሚገኝ ጊዜያዊ ድጋፍ የሚልቅ ነው። ዐሻራን በማኖር የሚፈጠር ዘላቂ ለውጥን የሚተልም ነው፡፡ ፖለቲከኞችም ከራሳቸው ተሻግረው የብዙኃኑን ፍላጎት ለማርካት የሚሠሩ መሆን አለባቸው።
የመደመር መንግሥት ገፅ 281