Weynshet Abebe

Weynshet Abebe Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Weynshet Abebe, Grocers, Addis Ababa.

22/04/2026
22/04/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝግባ ሊጠናቀቅ አንድ ቀናት ብቻ ቀሩት!

እንግዲያውስ ባሉበት ሆነው በ"ምርጫዬ” የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ በኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።

22/04/2026

እስካሁን አልተመዘገቡም ?

የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል!
ባሉበት ሆነው በ"ምርጫዬ” የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ በኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።
ፈጥነው በመመዝገብ ዉሳኔ ሰጪዎችን ይቀላቀሉ !

17/04/2026

የመራጮች ምዝገባ 5 ቀን ብቻ ቀረው!!
እኔ በጊዜ የምርጫ ካርዴን ወስጃለሁ፤ እናንተስ?

እንደ ሰለጠኑት ሀገራት በእኛም ሀገር የመንግሥት ሥልጣን ከሕዝብ የሚመነጭና በሕዝብ የምርጫ ካርድ የሚወሰን መሆን አለበት፤ ይኖርበታልም።

ምርጫ በሁሉም አካባቢ ሰላማዊና የተረጋጋ ሁኔታ እንዲሰፍን፣ የዴሞክራሲ እና የሰለጠነ የፓለቲካ ሥርዓትን ለመገንባት፣ የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል፣ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው።
ከምርጫ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ በአገር ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያመጣል።
ስለሆነም፤ ሁላችሁም የምርጫ ካርዳችሁን ወስዳችሁ የመምረጥ መብታችሁን ተጠቀሙ። መብታችሁን ተጠቅማችሁ ባትመርጡ፣ ሌሎች ተመዝግበው በመረጡት መንግሥት መተዳደራችሁ የማይቀር መሆኑን በመገንዘብ መብታችሁን ተጠቀሙ።

የምርጫ ካርድ ወስዶ መምረጥ ለሀብታሙም፣ ለደሃውም፣ ለተማረውም፣ ላልተማረውም፣ ዕድሜው ለመምረጥ ለደረሰ ወጣት፣ ለጎልማሳው፣ ለአዛውንቱ፣ ለሴቱም ሆነ ለወንዱ፣ ለባለስልጣንም፣ ለሌላውም ዜጋ እኩል የተሰጠ መብት ስለሆነ መብታችሁን ተጠቀሙበት!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Weynshet Abebe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category