10/06/2026
የጓደኛውን ሞተር ቁልፍ በመስቀረጽ ሞተሩን ሰርቆ ወደ ኦሮሚያ ክልል የሸሸገው ተጠርጣሪ ከና ግብረአበሮቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ ።
በቀን 03/2018 ዓ.ም በሀለባ ቁሊቶ ከተማ ሜጦማ ቀበሌ ልዩ ስሙ መቀላ ተራ አከባቢ አቶ ነብዩ ጀማል የተባለው ግለሰብ የጓደኛውን የነጃ እማም ሀሱኔ አፓቺ ሞተር ሰይክል ቁሊፉን በማስቀረጽ ሞተሩን ወስዶ አቶ ህርጰ አማን ኦሮሚያ ክልል በሳ ቀበሌ ነዋሪ 2ተኛ ቦንሲ ወንባሪ በተመሳሳይ የባሳ ነዋሪ 3ተኛ ቦሪ ቦንሲ ስራሮ ወረዳ 4ተኛ ኑራ መሸሻ የባሳ ነዋሪ ሲሆኑ ሞተሩን ወደ ኦሮሚያ ክልል በሳ ቀበሌ ወስደው ከሸሸጉበት የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ፖሊስ ጥብቅ ክትትልና ጠንካራ ኦፕሬሽን ስራ በመስራት ተጠርጣሪውን ከና ግብረአበሮቹጋ በቁጥጥር ስር መዋል ችሏል።
ወንጀልን በጋራ እንከላከል !!
የሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ።
ዘጋባው የሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት ህዝብ ግንኘነት ነው!!!