20/10/2024
መደመር የችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍና መንገዳችን ነው!
የመደመር እሳቤ በብዙ ጉዳዮቻችን ላይ ያለንን አቅም አሟጠንና ብክነትን ቀንሰን በመጠቀም የጋራ ግቦቻችንን እውን የምናደርግበትና የሀገራችንን ህልውና የምናረጋግጥበት የንቃት መንገድ ነው።
የንቃት መንገድ ነው ስንል የኑሮ ጣጣን ሁሉ ለርእዮተ ዓለም ሰጥቶ ያንን እየመነዘሩ ከመኖር ይልቅ መርህንና ነባራዊ ሁኔታን እያስታረቁ ለመሄድ የሚያስችል የሁልጊዜ ዝግጁነትን የሚፈልግ በመሆኑ ነው። ይህን መንገድ ስንከተል የሕዝብን ፍላጎት ከሀገሪቱ አጣዳፊ ህልውና ጋር አዳብለን ለመመለስና በመጨረሻም ለሀገራችን ህልውና አስተማማኝ የሚሆነውን የሥልጣኔና የብልጽግና ጎዳና ለመቀላቀል ያስችለናል።