Yeshmebet wolellaw admi

Yeshmebet wolellaw admi Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yeshmebet wolellaw admi, Grocers, Bahar Dar Ghiorghis.

06/04/2026
❖ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው⁉❖••✥ገብርኤል ማለት " እግዚእ ወገብር”፦ የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ...
27/12/2025

❖ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው⁉❖

••✥ገብርኤል ማለት " እግዚእ ወገብር”፦ የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፦ማን ፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “የፈጠረንን✥አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል።

✥ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ ይህ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ

✥ገብርኤል ነው✥
የአሸናፊና የኃይል መልአክ

✥ገብርኤል ነው✥
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ

✥ገብርኤል ነው✥
"የመልአኩ ጥበቃ እና ረድኤት አይለየን"
❖ይቆየን❖

ታህሳስ 10 ;11 ;12 ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ ኑ ፅዮንን እንስራት
19/12/2025

ታህሳስ 10 ;11 ;12 ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ ኑ ፅዮንን እንስራት

“ ስንዴውን እየሸከፈ ነው”ባለፈው ጷግሜን ወር እንዲያው ሱባኤ  ባይባልም እንደነገሩ ገዳም ተቀምጬ ሳለ አምስቷ ቀን ስትፈጸም ድንገት አንድ ታላቅ መምህር እንዳረፉ ሰማሁ፣ የኔታ መጋቤ ምሥጢ...
01/12/2025

“ ስንዴውን እየሸከፈ ነው”

ባለፈው ጷግሜን ወር እንዲያው ሱባኤ ባይባልም እንደነገሩ ገዳም ተቀምጬ ሳለ አምስቷ ቀን ስትፈጸም ድንገት አንድ ታላቅ መምህር እንዳረፉ ሰማሁ፣ የኔታ መጋቤ ምሥጢር ተሾመ በጎንደር ሐመረ ኆኅ ሠለስቱ ምእት ቤተ ክርስቲያን የመጻሕፍተ መነኮሳት ምስክር መምህር ናቸው። ያን ጊዜ ራሳቸው የኔታ ከአምስት ዓመት በፊት ሌላ ትልቅ ሰው ሲያርፍ የተናገሩትን ቃል አስታውሼ ቀጣዩን አንቀጽ ጻፍኩ። ቢሆንም ከለቅሷቸው ባልገኝም አልቅሼ ጽፌ ተውኩት እንጂ አደባባይ አላወጣሁትም ነበር። ዛሬ ግን ሌላው ዓይናማ ሊቅ ሲጨመሩ ዐቅም ቢያንሰኝ አወጣሁት።


“ስንዴውን እየሸከፈ ነው”

ጌታ ራሱን ከመሰለበት ምሳሌዎች ንጹሕ ዘር በሚዘራ ገበሬ ነው።እርሻውም ይህ ዓለም፣ ዘሩንም ወንጌል ነው።እንክርዳድም ክፉት ዘሪውም ዲያብሎስ ነው።እንክርዳዱም የሚዘራው ሰዎቹ ሲተኙ ነው። ሰዎቹ ያላቸው ታላላቁ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። ማንቀላፋታቸው ዕረፍታቸው ሲሆን ሰዎቹ ሲተኙ እንክርዳድ መዘራቱ ታላላቆቹ ሲያርፉ በዲያብሎስና ግብር አበሮቹ አዲስ እንክርዳድ ሥርዓት ይዘራልና።አብረውም እስከ መከር ይቆያሉ።መከሩ የዚህ ዓለም ማለቅ ሆኖ አጫጆቹም መልእክት ናቸው።ያን ጊዜ ንጉሥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ የሚያበጥርበት የማያሳስት ሥልጣን የተባለ ነፋስ አለው።እንክርዳዱን በእሳት አቃጥሎ ስንዴውን በመንግሥተ ሰማያት ጎተራ ይሰበስባል ነበር የተማርነው።ማቴ፲፫፥፴፱-፵፪

የሥጋ ዓይን ሳይኖራቸው በነፍሳቸው የሚያዩት የኔታ መጋቤ ምሥጢር ተሾመ ደግሞ አሁንም “ስንዴውን እየሸከፈ ነው አሉ”።በ፳፲፫ ዓም መጽሐፈ መነኮሳትን ከእርሳቸው እያሄድኩ ሳለ ወንበር እንዳበቃ አንድ ትልቅ ሰው እንዳረፉ ሰማን።የኔታም ካዘኑ በኋላ “ አይ እግዚአብሔር እኮ እንክርዳዱን ለማቃጠል ስንዴውን አስቀድሞ እየሸከፈ ነው” አሉ። ምን ማለት ነው የኔታ ስላቸው፦ “ ሰዉ ከፍቷል፤አልመለስ ብሏል፤ ስለዚህ ወዳጆቹን አስቀድሞ ሸካክፎ በመከራ እሳት ሊገርፈን ይመስለኛል አሉ” ያን ጊዜም ጦርነት ውስጥ ነበርን። አሁንም እንደዚያው የመከራው እሳት እየገረፈን አለን።በጊዜው ተጨንቄ አሁንም የሚሆነውን ሁሉ እያየሁ እያሰብኳቸው ሳለ እንዳረፉ ሰማሁ።

የኔታ አሁን ደግሞ አንዱን ምርጥ ስንዴውን እርስዎን ወሰደ።እርስዎ ከሌሉ የታሪክ እንክርዳድ ሲዘራ ማን ያቀናል?በመጣን ቁጥር የማይዘጋ ቤት የማን አለ!ለትንሽ ለትልቁ የማይሰለች አንደበት ወዴት አለ? ታሞ የሚስቅልን አባት ወዴት እናገኛለን?ሰውነቱ ከአልጋ ተጣብቆ በደዌ ተይዞ የሚያስተምር ትዕግሥተኛ መምህርስ ?

የኔታ ሩቅ ሆኜ የት ጠፋህ የሚሉኝ ፣የኔታ በቀለም የወለዱኝ አባቴ፣የኔታ ጎንደር አራት ዓመት ስቀመጥ በደነዘዘኝ ቁጥር መጥቼ ልጅነቴን የማጫውትዎት ወዳጄ!.

የኔታ ስንዴዎቹን እናንተን ሲሸክፍ እኛን በእሳት እንዳያቃጥለን በጸሎትዎ ያስቡን። የመጽሐፈ መነኮሳት መምህር ነዎትና እኒያ በስስት ሲተረጉሙላቸው የነበሩ ከዋክብት እንጦንስና መቃርስን...ሲያገኟቸው እንደ ደከምን ይንገሩልን። ብየ አልቅሼ ነበር።

ዛሬ ደግሞ የክብረ ደናግል ናዳ ቅድስት ማርያም አበ ምኔት፤ የቅኔው፣ የመጻሕፍተ ብሉያትና ሐዲሳት፣የአቡሻኽር፣የፍትሐ ነገሥቱ ሊቅ የኔታ ይባቤ በላይ እንዳረፉ ከወንበር በኋላ ሰማሁ።የኔታ ይባቤ ቀርቤ ባላውቃቸውም በአንዲት እናታችን በቤተ ክርስቲያን ግን አውቃቸዋለሁ።እውነትን ትክ ብሎ የሚያይ የነፍስ ዓይን ያላቸው፣የአድር ባይነትን ካባ የናቁ፣ሳይማር መድረክ የያዘውን ፈር የሚስይዙ፣በአታቸውን አጽንተው በገዳማቸው የሚኖሩ መምህር እንደሆኑ ሰምቻለሁ።በሳይንስ ከተራቀቁ ምሁራን እስከ እስካልተማረው በጸሎታቸ

በረከታቸዉ ይድረሰን አባታችን #የኀዘን መግለጫ‎ #"ዘጻመወ በዓለም የሐዩ ለዝሉፉ፤ በዓለም የደከመ ለዘለዓለም ይድናል" መዝ 48(49)፥9‎ኅዳር 22/2018 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር‎ይህ ዘመን ቤ...
01/12/2025

በረከታቸዉ ይድረሰን አባታችን
#የኀዘን መግለጫ
‎ #"ዘጻመወ በዓለም የሐዩ ለዝሉፉ፤ በዓለም የደከመ ለዘለዓለም ይድናል" መዝ 48(49)፥9
‎ኅዳር 22/2018 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር
‎ይህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ምልክት የሚሆኑ ታላላቅ ሊቃውንት ልጆቿን እያጣች ያለችበት ጊዜ ነው። በዛሬው ዕለትም ቤተ ክርስቲያናችን በስስት ከምትመለከታቸው ሊቃውንት ልጆቿ አንዱ የሆኑት አራት ዐይና የኔታ ይባቤ በላይ (አርአያ ሥላሴ)በሞት ተለይተውናል። በሊቁ ዕረፍት የተሰማኝን ጥልቅ ኀዘን በባሕር ዳርና በሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ስም እየገለጽኩኝ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችን መጽናናትን እንዲሰጥ እመኛለሁ።
‎"የአርአያ ሥላሴን ነፍስ እግዚአብር በዐጸደ ገነት ያሳርፍልን።"
‎✍️አባ አብርሃም የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
‎@የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

30/11/2025

ማርያም ማርያም ማርያም

"ማርያም" ማለት ምን ማለት ነው ?* ማርያም ማለት፦መርሃ ለመንግስተ ሰማያትማለት ነው።* ማርያም ማለት ሰረገላ ፀሐይ ማለት ነው።* ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሔርማለት ነው።*ማርያም ማለ...
30/11/2025

"ማርያም" ማለት ምን ማለት ነው ?

* ማርያም ማለት፦መርሃ ለመንግስተ ሰማያትማለት ነው።
* ማርያም ማለት ሰረገላ ፀሐይ ማለት ነው።
* ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሔርማለት ነው።
*ማርያም ማለት ውኅብት (ስጥውት) ማለት ነው።
በተናጥል ሲተረጎም፦
ማ ፦ማለት=> ማይደረ መለኮት ማለት ነው።
ር ፦ማለት=> ርግብየ ይቤላ ማለት ነው።
ያ፦ማለት=> ያንቀዓዱ አቤኪ ኩሉ ፍጥረት ማለት ነው።
ም፦ ማለት=> ምስሐል ወምስጋድ

#የድንግል ማርያም ጰሎት ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ
ይጠብቀን። source orthodo info

🕊  ብርሃኔ ነሽ አይኔ ድንግል ማርያም እናቴ    የስደት ስንቄ ነሽ~~የአንደበቴ ጣዕም     ክብርና ሞገሴ~~የእኔነቴ ሰላምዛሬም እንደ ትላንት~~እልሻለው ማርያም       አማላጅነትሽ~~ሞ...
30/11/2025

🕊 ብርሃኔ ነሽ አይኔ ድንግል ማርያም እናቴ
የስደት ስንቄ ነሽ~~የአንደበቴ ጣዕም
ክብርና ሞገሴ~~የእኔነቴ ሰላም
ዛሬም እንደ ትላንት~~እልሻለው ማርያም
አማላጅነትሽ~~ሞትን ያሻግራል
ፀሎት ርህራሄሽ~~ሰላምን ያለብሳል
አንችን የተሰጠ~~ፍቅርሽ የገባው ሰው
የሚያመሰግንሽ~~የታደለ ሰው ነው!!!
እናቴ ማርያም ክብር ሁሉ ላንች ይሁን
ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፋ ነገር ሁሉ ትጠብቃችው!!!
አሜን አሜን አሜን

"የዛሬን ብቻ አውጭን ብለናት ከስንቱ መዓት አወጣችን እመ ብርሃን አሁንም ትጠብቀን አማላጅነቷ አይለየን✝🙏
26/10/2025

"የዛሬን ብቻ አውጭን ብለናት ከስንቱ መዓት አወጣችን እመ ብርሃን አሁንም ትጠብቀን አማላጅነቷ አይለየን✝🙏

Address

Bahar Dar Ghiorghis

Telephone

+251918619895

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeshmebet wolellaw admi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yeshmebet wolellaw admi:

Share

Category