14/10/2025
#መምህር
*******
አንተ የቀለም ሰው ጥበብ አስተማሪ
የአለምን ሚስጥር በሙያህ መርማሪ
የሰው ግርድና ምርት ሁልጊዜ አበጣሪ
ስራህ የሚያኮራህ ትውልድ አሳማሪ
ተጨንቀህ ተጠበህ አዲስ ሰው ፈጣሪ
አንተ ነህ መምህር ስልጣኔ አብሳሪ።
ጨቅላ ህፃናትን ኮትኩቶ አሳዳጊ
መሃይምነትን ዘወትር ተዋጊ
በየትኛውም ቦታ ሙያህ ተፈላጊ።
እውቀትን ለመዝራት አቋርጠህ ተራራ
በሀሳብ ማዕበል ስትበር እንደ አሞራ
ብጤህን ለማፍራት ፍቀህ ነጭ አቧራ
መምህር አይታክትህ ሙያህን ስትዘራ
የስልጣኔ ምንጭ ያንተ ቅዱስ ስራ
ለአዳዲስ ግኝቶች የእድገት አሻራ
አስተካክለህ ስለህ የሰውን አእምሮ
ፍጡር ሰው እንዲሆን አውቆ ተመራምሮ
ጥበብ ፍልስፍናን ህሊናን ቀምሮ
ሁሉን ያዳርሳል በጊዜ ቀጠሮ።
ክብርና ምስጋና ለመምህራኖች🙏