02/06/2023
በአፄ ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ ከደብረኤባ ቀበሌ ነዋሪ ሴቶች ጋር "ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን!" በሚል ርዕስ ሲካሄድ የዋለዉ ኮንፈረንስ ተጠናቋል።
የኮንፈረንሱ ተሳታፊውች እንደገለጹት አሁን እንደ ክልላችን እየገጠመን ያለውን ፈተና የምንወጣበትን ስልት የመከርንበት ነው ብለዋል።
በአፄ ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ የደብረ ኤባ ቀበሌ ዋና አስተዳደር አቶ ጋሻዉ ከበደ እንደተናገሩት ያሉብንን የአስተሳሰብ መዛባቶች አርመን ክልላችንን ወደ ፍጹም ሰላም ለማምጣት ሁላችሁም የየራሳችሁን አስተዋፀኦ ልታደርጉ ይገባል ብለዋል።
የአፄ ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ ሴቶች አማካሪ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ብርሃኔ ስዩም በበኩላችው አማራ በኢትዮጵያ የመንግስታት ታሪክ ውስጥ ሰፊ እና አይረሴ ታሪክ ሰርተው አልፈዋል እኛም የአባቶቻችንን እና የእናቶቻችን ፈለግ በመከተል የጽንፈኞችን አማራን የመበታተን አላማ አክሽፈን ትልቅነታችን ማስመስከር አለብን በተጨማሪም የአማራ ክልል የዘመናት ጥያቄ ለመፍታት የትግል ስልታችን በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ዉስጥ ሆኖ ጠንካራ እና ፅናትን የተላበሰ አማራጭ በመከተል ሊሆን እንደሚገባ በአፅኖት ተናግረዋል።