ሰብስቤ አርቅሶ ADU

ሰብስቤ አርቅሶ ADU Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሰብስቤ አርቅሶ ADU, Grocers, pritoria, Durame.

ሀምባሪቾን ወደ ክብሩ መልሱት‼️ተራራ የሆነ ስም ተሸክሞ ትልቅ ህዝብ ወክሎ ከፕሪሚየር ሊጉ መቀላቀል ቻለ፡፡ስሙን የሚያክል ድጋፍ፣ለክብሩ የሚጨነቅ ደጋፊ ባለቤት መሆኑን ለማስመስከር ሁለት የ...
13/12/2023

ሀምባሪቾን ወደ ክብሩ መልሱት‼️

ተራራ የሆነ ስም ተሸክሞ ትልቅ ህዝብ ወክሎ ከፕሪሚየር ሊጉ መቀላቀል ቻለ፡፡ስሙን የሚያክል ድጋፍ፣ለክብሩ የሚጨነቅ ደጋፊ ባለቤት መሆኑን ለማስመስከር ሁለት የመጀመሪያዎቹ ፍልሚያዎች በቂ ነበሩ፡፡

ግን ከዚያ በኃላ ለምን ቡዳ በላው‼️

ሀምባሪቾ አሁን ከፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ግርጌ ሻሸመኔ ከተማ ብቻ በልጦ በሁለት ነጥብ የአዳማ ቆይታውን ለማጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡የክለቡ ተከታታይ ሽንፈትና ውጤት ማጣት ደጋፊውን ክፉኛ አሳዝኗል፡፡ከዚህ በመነሳት በክለቡ ላይ መሠረታዊ ለውጥ መደረግ እንደለበት ጥያቄዎች ሲቀርቡ ሰንብተዋል፡፡

ለዚህ ጥያቄና መልስ የሚሰጥ፣ለክለቡ ውጤት ማጣት ኃላፊነት የሚወስድ ቆራጥ፣ህዝብን የሚወግናና ለእውነት የቆመ አካል ግን እስካሁን አልተገኘም፡፡አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ለተወሰኑ ተጨዋችች ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው፣ለአሰልጣኙ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠውና በአጋማሽ ላይ ተከላካይና አጥቂ ለመግዛት ከውሳኔ ተደርሷል፡፡

ውሳኔው እንዲሁ በግርድፉ መልካም ነው እንበል፡፡ነገር ግን ክለቡ ያለበትን ችግር የሚፈታ፣የሚመሩ አካላትም ችግሩን በውል የተገነዘቡ አይመስለኝም፡፡የክለቡን ህሊውና ከማስጠበቅና የደጋፊውን ሞራል ከመጠበቅ ብሎም የህቡን ፍላጎት ከማክበር ይልቅ ለግለሰቦች የተጨነቁ፣እንዳይነኩባቸው የሳሱ ይመስላል፡፡

በየትኛውም ዓለም በተከታታይ ውጤት ያጣ፣የተሸነፈ፣መሻሻል ማሳየት ያልቻለ አሰልጣኝ ወይ በራሱ ፈቃድ ይለቃል ካልሆነም በቀጠረው አካል ይሰናበታል፡፡ሀምባሪቾ ከዚህ እውነት በተፀራሪ ለመቆም የሚያበቃው ምክንያት ምን ይሆን!!ዛሬ ላይ ፈጣን እርምጃ ወስዶ የክለቡን ቀጣይ ቆይታ ከማደላደል ይልቅ የይምሰል ውሳኔ መወሰን ለምን አስፈለገ!! ቦርዱና የዞኑ አስተዳደር ውግንናው ለማነው!!

እኔ ግን እን አንድ ደጋፊ እላለሁ ክለቡ መቀጠል ካለበት አሰልጣኙ ኃላፊነት ወስዶ ከዚህ ቀደም ለሠራው ሥራ ተመስግኖ በራሱ ፈቃድ መልቀቅ አለበት፡፡ይህንን ተሞክሮ ለመቅሰም ሌላ ቦታ መሄድ ሳያስፈል ተመሳሳይ ታሪክ የሚጋራውን የሻሸመኔ ከተማን መመልከት በቂ ነው፡፡ሀዲያ ሆሳዕና፣ሲዳማ ቡና እና ሌሎች ክለቦች የወሰኑትን ውሳኔ መፈተሸ ተገቢ ነው፡፡የዞኑ አስተዳደርና ቦርዱ ግን ቆም ብለዉ ራሳቸውን ይፈትሹ፡፡ኃላፊነት መውሰድ ባለባቸው ጉዳይ ሳያወላዱ ኃላፊነት ይውሰዱ፡፡ክለቡ የቴክኒክ ኮሚቴ እንዳይኖረው ለምን እንደተደረገ ይግለፅ፡፡የክለቡ አደረጃጀት እንዲስተካከል፣ጠንካራ የደጋፊ ማህበር እንዳይኖርና እንዳይመሰረት ለምን ተፈለገ??

እጃችሁን ከክለቡ ላይ አንሱ!!
ደስታችንን አትንጠቁ‼️
ሀምባሪቾን ወደ ክብሩ መልሱ‼️

አዲስ አሰልጣኝ ያስፈልገናል‼️

09/12/2023

🙇🙇🙏

25/11/2023

ኑሮ ከጌታ ከእየሱስ ጋር❤🙏

16/11/2023

እየሱስ❤

"ፍቅሬን አንጠፍጥ         ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ     Yidnekachew Teka Mehamed 🙏💖🙌ፍቅሬን አንጠፍጥፌ አንተ ላይ እጨርሰዋለሁ ራስህ ላይፍቅሬን አንጠፍጥፌ አንተ ላይ እጨ...
06/11/2023

"ፍቅሬን አንጠፍጥ
ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ
Yidnekachew Teka Mehamed 🙏💖🙌

ፍቅሬን አንጠፍጥፌ አንተ ላይ
እጨርሰዋለሁ ራስህ ላይ
ፍቅሬን አንጠፍጥፌ አንተ ላይ
እጨርሰዋለሁ እግሮችህ ላይ
ዙፋንህ ላይ
አንተ ላይ
ምህረትህ ላይ
እራስህ ላይ

የፍቅሬ ጥግ ነህ የእኔ መዳረሻ
የት ሄጄ ልተንፍስ ፍቅሬን ለማን ላውራ
የፍቅሬ ቦታዬ ፍቅሬን የማውልበት
ኢየሱስ አለህልኝ ሁሌ እንድነግርህ

ሌላ ቦታ የማፈስሰው እንባ የለኝም
ሌላ ቦታ የሚባክን ፍቅር የለኝም
ባዕድ ሰፈር የሚባክን ፍቅር የለኝም
ላልሞተልኝ የሚባክን ፍቅር የለኝም

የለኝም (4)
ኢየሱሴ ላይ አለቀብኝ
የእኔ ኢየሱስ ላይ ፍቅሬን ጨረስኩኝ

ማንም ዋጋ ከፍሎ አልሞተም ለምኔም ስለእኔ
አንተ አይደለህም ወይ ኢየሱስ የህይወቴ ዋሴ
ሌላ የምወድድበት ትርፍ አካል ከየት ላምጣ ታዲያ
መውደጃዬን ሁሉ ወሰድከው ሆኜ የፍቅርህ ባሪያ

ህይወቴን ተማምለዋል ሊያደርጉኝ የራሳቸው
ሊወስዱኝ ተፎካክረዋል እጣ እየተጣጣሉ
ከእነሱ ከቶ አንዳቸውም እጣ ውስጥ በሞት አልገባሁ
አንተ ነህ ራስህን ያስያዝከው በሞትህ ያሸነፍካቸው

ታሪኬን ያሳመርከው ላይ ፍቅሬ ይለቅ አንተ ላይ
ነገሬን ያሳመርከው ላይ ፍቅሬ ይለቅ አንተ ላይ
ምህረት ያገነንከው ላይ ፍቅሬ ይለቅ አንተ ላይ
በሞትህ የታደግከኝ ላይ ፍቅሬ ይለቅ አንተ ላይ

ኢየሱስ (8)

የፍቅሬ ጥግ ነህ የእኔ መዳረሻ
የት ሄጄ ልተንፍስ ፍቅሬን ለማን ላውራ
የፍቅሬ ቦታዬ ፍቅሬን የማውልብህ
ኢየሱስ አለህልኝ ሁሌ እንድነግርህ

ሌላ ቦታ የማፈስሰው እንባ የለኝም
ሌላ ቦታ የሚባክን ፍቅር የለኝም
ባዕድ ሰፈር የሚባክን ፍቅር የለኝም
ላልሞተልኝ የሚባክን ፍቅር የለኝም

የለኝም (4)
ኢየሱሴ ላይ አለቀብኝ
የእኔ ኢየሱስ ላይ ፍቅሬን ጨረስኩኝ
#መልካም ቀን #ይሁንላችሁ🙏💖

እጄን አትይዘኝም?ባህሪህን አውቀዋለሁ።ወዳንተ መጥቶ ለሚፈልግህ ብቻ ሳይሆን ያልመጣውንም ፈልገህ እንደምታመጣው አውቃለሁ።ስለዚህ እጆቼን ወዳንተ ዘርግቼ እጆቼን ይዘህ ካለሁበት አዘቅት እንድታ...
31/10/2023

እጄን አትይዘኝም?

ባህሪህን አውቀዋለሁ።ወዳንተ መጥቶ ለሚፈልግህ ብቻ ሳይሆን ያልመጣውንም ፈልገህ እንደምታመጣው አውቃለሁ።ስለዚህ እጆቼን ወዳንተ ዘርግቼ እጆቼን ይዘህ ካለሁበት አዘቅት እንድታወጣኝ እለምንሃለሁ።እጆቼን ይዘህ ስታነሳኝ ከቁሸቴም ስታነጻኝ ዳግመኛ በፊትህ እንደምቆም አውቃለሁ።

ተመስገን

ድል ድል ይሸተኛል ድል ለተረረውቹ ድል ለሀምባርቾ ዱረሜ💪💪
27/10/2023

ድል ድል ይሸተኛል
ድል ለተረረውቹ
ድል ለሀምባርቾ ዱረሜ💪💪

Address

Pritoria
Durame

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰብስቤ አርቅሶ ADU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category