29/10/2025
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሲሰጡ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል:-
2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ ታላላቅ እና አይቻሉም የተባሉ ጉዳዮችን እውን ያደረግንበት የስኬት ዓመት ነበር።
የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የሀገሪቱን ግብርና መር የኢኮኖሚ አካሄድ፣ ከአንድ ዘርፍ ወደ ብዝኃ ዘርፍ በመቀየር ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል።
በዚህም 5 ዋና ዋና ዘርፎች ተለይተው ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ላይ እየተሰራ ነው።
መንግሥት የኢትዮጵያን ልማት ለማፋጠንም ከግሉ ዘርፍ ጋር በጥምረት፤ መንግሥት ከሕዝብ እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ የተፋጠነ ዕድገት እውን ለማድረግ እየተጋ ነው።
በአረንጓዴ ዐሻራ 48 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል፤ ይህም በዓለም ትልቁ የደን ማልማት ሥራ ነው።
በዚህም ኢትዮጵያ ለአንድ ችግኝ 1 ዶላር ብታወጣ ለዓለም አየር ንብረት 48 ቢሊዮን ዶላር አውጥታለች ማለት ነው።