Gedeo Midia Network

Gedeo Midia Network Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gedeo Midia Network, Grocers, London.

 #እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ Mituma Doge Haile and Burkit
19/07/2026

#እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ Mituma Doge Haile and Burkit

11/07/2026

የፖለተካ እንቅስቃሴ ለማቋረጥ ነበር ነገር ግን የምንሰማቸው ጉዶች እያስቻሉን አይደለም፣
ዲላ ከተመደቡት ክላስተሮች ውስጥ በአንዱ የግብርና ቢሮ እየተሠራ ያለውን ደባ ስለማሳወቅ።

በክልል ደረጃ ራስን ማስተዳደር፣ መደራጀት ወይም በክልሎች መካከል የሚደረግ ትብብር (Regional Integration/Resilience) ለህዝቦች እጅግ በጣም ብዙና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ይፈጥራል፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መረጋጋትን በመፍጠር የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ከፍ ያደርጋል በምል የፌዴራል ሥርዓት አገርቷን በተለያዩ ክልሎች እንደሸነሸነ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት የሀገርቱን 1/3ኛ ብሔርና ቋንቋ አጭቆ የያዘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንዱ ነው። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብዙ ቋንቋዎች፣ የብዙ ባህሎች፣የብዙ ከርሰ ምድር ሀብት ባለቤት በመሆኑ በውስጡ የታቀፈው ወደ 30 የሚደርስ ብሔር/ብሔረሰብ ተያይዞና ተደጋግፎ ከሰራ በአጭር ጊዜ ለውጥ ማስመዝገብ እንደሚችል በብዙ የታወቀ ጉዳይ ነው።

ሆኖም በደቡብ ክልል መንግሥት ውስጥ በታቀፉት 30 ብሔር/ብሔረሰብ ሀብትና የመንግሥት ሥልጣንን እኩል የመጋራት ችግር እንዳለ፣ በአመራር ደረጃ ያለው የእርስ በርስ ሹክቻ ከልማት ወደኋላ እያስቀረ እንደሆነ በሰፊው እየተነገረ ቆይቷል።

የጉዳዩ አሳሳቢነት ከክልሉ አልፎ የፌዴራል የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት ደርሶ የሰነበተ መሆኑን ከሰሞኑ በደቡብ ክልል በአርባ ምንጭ የተገነባውን ሪዞርትና የገጠር ኮርደር ልመርቅ ወደክልሉ ያመሩት ጠ/ሚንስቴር አቢይ አህመድ በንግግራቸው ውስጥ ያስተላለፉት ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ጥሩ ማሳያ ነው።

በዕለቱ በጠ/ሚኒስቴሩ የተላለፉት መልእክቶች በክልሉ ሹማምንት መካከል ምን ያህል ሹክቻና መጓተት እንዳለ በጥልቀት እንደሚያውቁ የገለጹበት አንዳንድ አገላለጾች አግራሞትን ይፈጥራሉ። ለአብነት ያህል፣

* " 30ውም ብሔረሰብ የተከበረ፣ የተወደደ፣ አንዱ ከአንዱ ልቆ፣ አንዱ ከአንዱ በልጦ ፣ እኔ አንደኛ ካልሆንኩ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ማደግ አይቻልም።"

* "ወላይታና ጋሞ፤ ጋሞና ጎፋ መተባበር ካልቻሉ፣ አብሮ መቆም ካልቻሉ ኢትዮጵያ እንዴት አብራ ትቆማለች?"

* " ለተከበረው የደቡብ ህዝብና አመራር ማስተላለፍ የምፈልገው ኮንሶ ከጋሞ አያንስሞ። ዳሰነች ከወላይታ አያንስም።ሁሉም ህዝብ እኩል ነው። እኔ እበልጣለሁ የምል ስሜት፣ እኔ እሻላለሁ የምል ሰሜት፣ ካለእኔ አንደኛ የለም የምል ለዘመናት ድሀ አድርጎ አስቀርቶናል።"

* " አላአስፈላጊ ሹክቻ ከልማት ወደኋላ እንዳያሰቀር የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች አስመሳይንና አንደኛ ብሔሮች ነን ባዮችን አትፈልጓቸው። የሚሠሩ ሰዎች ብቻ ፈልጉ"የምሉና መሰል ማሳሰቢያዎችን መስጠታቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በአንዳንድ ክላስተር እየተተገበሩ የቆዩ ድርጊቶች ከጠ/ሚኒስቴሩ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ አልፈው በቀጣይ በሚመሠረተው ጠንካራ የመንግሰትና የመንግስት መ/ቤቶች ጉዳዩ በሚመለከተው የበላይ አካል ጥልቅ ትኩረት ተሰጥቶ ማስተካከያ የሚሻው ዲላ ከተመደቡት ክላስተሮች ውስጥ በአንዱ የግብርና ቢሮ እየተሠራ ያለውን ደባ ማሳወቅ ወደድን።

በም/ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊው መሪሁን ፍቅሩ የመንግስት ሠራተኞች ቅጥሪና ዝውውር በተከለከለበት እና የደቡብ ኢትዮጽያን ካቋቋሙ 12 ዞኖች የህዝብ ቁጥርና ክልሉን እኛ ነን ያቋቋምነው በማለት ከወረዳዎች ቀጥታ በማምጣት ተቋሙን ሙሉ በሙሉ በወላይታ ተወላጅ እየሞላ ስሆን ለሌሎች አናሳ ቁጥር ያላቸውን ብሔረሰብ እጅግ በመናቅ፣ የግብርናውን ተቋም አስተዳደርና ፋይናንስ ወላይታ ፣ ም/ቢሮ ኅላፊና እርሻ ዘር

ዲላ ዙሪያ ወረዳ በወቸማ ትምህርት ቤት ከሚንስትሩ ፈተና እንድታልፉ መልስ ልናሰራ ነው በሚል ከእያንዳንዱ ተማሪዎች ሶስት መቶ ብር እየተሰበሰበ ይገኛል፣ የብልጽግና መንግስት በዚህ ምን ምላሽ...
08/06/2026

ዲላ ዙሪያ ወረዳ በወቸማ ትምህርት ቤት ከሚንስትሩ ፈተና እንድታልፉ መልስ ልናሰራ ነው በሚል ከእያንዳንዱ ተማሪዎች ሶስት መቶ ብር እየተሰበሰበ ይገኛል፣ የብልጽግና መንግስት በዚህ ምን ምላሽ አለዎት፣ የመረጥነው ልበዘብዙን ነው እንደ እያሉ ማህበረሰብ ማጉረመረሙን ቀጥለዋል።
ግልባጭ
ለሚመለከተው ሁሉ።

በአስቸኳይ ለዚህ ለግል ተበደይና ባልዋለበት ወንጀል ለደረሰበት የሳላሳ ሺ ብር ገንዘብ መቀጮ በውስጥ መስመር አካዎንት ተከፍተው በውጭ አገር ያላችሁት ጭምር እንረባረብለት ፍጠኑ ገሕድዶች ያላ...
02/06/2026

በአስቸኳይ ለዚህ ለግል ተበደይና ባልዋለበት ወንጀል ለደረሰበት የሳላሳ ሺ ብር ገንዘብ መቀጮ በውስጥ መስመር አካዎንት ተከፍተው በውጭ አገር ያላችሁት ጭምር እንረባረብለት ፍጠኑ ገሕድዶች ያላችሁትን መቶ ብርም ብትሆ ቶሎበሉ፣
ልጁ በአስቸኳይ ይግባኝ ይጠይቅ፣
ለሕዝብ ብሎ መታሰር ክብር ነው በርታ አለንለት።
ትላልቅ ሰዎች መደገፍ የምትፈልጉ ሰዎች የተማሪዎችን አካውንት ተጠቀሙ፣
ቆሻሾቹ መርዝ ስለሆኑ።

ስለጌዴኦ ዞን ምርጫ ጉዳይ ፈጣሪ ያሳያችሁ።ሰበር ዜናደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ኮቸሬና ፍሳገነት ምርጫ ክልል በቢሎያና ሀማ ምርጫ ታጣቢ አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ ባሰማራቸው ሀይሎች ኮሮ...
01/06/2026

ስለጌዴኦ ዞን ምርጫ ጉዳይ ፈጣሪ ያሳያችሁ።
ሰበር ዜና

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ኮቸሬና ፍሳገነት ምርጫ ክልል በቢሎያና ሀማ ምርጫ ታጣቢ አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ ባሰማራቸው ሀይሎች ኮሮጆ ውስጥ የምርጫ ድምፅ ሲጠቀጥቁ ተያዘ

አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ የቀበሌው ሊቀመንበር ጋር በመሆን ባሰማራቸው ሀይልች ከ600 በላይ ድምፅ በድብቅ የምርጫ ጣቢያ ኃላፊዎችን በገንዘብ ደልለው ምርጫው ሲያጭበረብሩ ተይዘዋል ሆኖም በአከባቢው ያሉ ፀጥታ አካላት ምንም ምላሽ መስጠት አልቻሉም ይህ የሆነው ከ7:00 ሰአት ጀምሮ የየተፎካካሪ ፓርቲ ታዛቢዎች በከፍተኛ ጫና ምክኒያት የተወሰነ ገንዘብ ተቀብለው ከምሳ መልስ ባለመግባታቸው የተፈጠረ ነው።

የሚገርመው ነገር ነገሩን ጫካ ገብተው ነው ሲጠቀጥቁ የነበረው በአስቾካይ በእነዚህ አከባቢ ያሉ ምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ ቦርዱ ማጣራት እንዲያደርግ እንጠይቃለን በዚሁ ምርጫ ጣቢያ 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ በዝረራ የተሸነፈው አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ ለሁለተኛ ጊዜ ላለመሸነፍ የማይባጥጠው ነገር እንደሌለ እየተነገረ ይገኛል።

30/05/2026

ብልፅግና እውነት ለመናገር በኮልደር ለፈረሱ ቤቶች የረከሰውን ገንዘብ ብከፍል? ገንዘብ ቸግሮት ነው? የሕዝብ እድገት ጠልተውት እንጅ።

የጌደብ ከተማ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብሎ የሸወደን የኮልደር ዲዛይን😂😂😂የተሰራው 50ሜትር ብቻ።
30/05/2026

የጌደብ ከተማ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብሎ የሸወደን የኮልደር ዲዛይን😂😂😂
የተሰራው 50ሜትር ብቻ።

የጌደብ ከተማ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብሎ የሸወደን የኮልደር ዲዛይን😂😂😂የተሰራው 50ሜትር ብቻ።የጌደብ ልጆች ሕዝቡን በሙዝቃ ጋጋታ ለመሸወድ የሄደበት መንገድ ተነቃ ፣ልማት ዜሮብልፅግና ዜሮአብይ...
30/05/2026

የጌደብ ከተማ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብሎ የሸወደን የኮልደር ዲዛይን😂😂😂
የተሰራው 50ሜትር ብቻ።
የጌደብ ልጆች ሕዝቡን በሙዝቃ ጋጋታ ለመሸወድ የሄደበት መንገድ ተነቃ ፣
ልማት ዜሮ
ብልፅግና ዜሮ
አብይ ዜሮ
ውሸት ብቻ።

Address

London

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gedeo Midia Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category