22/07/2024
የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት አረፉ
የዝነኛው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት ሲሞን ፔትሮ ሳሊኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
በአገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔራዊ እና ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ዝናን ያተረፈው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
እኚህ ግለሰብ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የፎርብስ መጽሔት መረጃ ያሳያል ሲል አርትስ ቲቪ ዘግቧል።
በተያያዘ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ለሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ቤተሰብና ለመላው ዊቢውልድ ግሩፕ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ሳሊኒ ለኢትዮጵያ የነበራቸው ፍቅር በተግባር የተገለጠ እንደሆነ ጠቅሰው በሀገር ግንባታ ሂደት የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ማከናወናቸውንም አንስተዋል።