11/08/2025
ከክለባችን ሃዲያ ሆሳዕና ስለነበረህ ጊዜ ከልብ እናመሰግናለን🙏
💥አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ በትልቁ የሚታወቅ ስም ነው። በተለይም ከሆሳዕና ከነማ ጋር ባሳለፈው ጊዜ በስፋት ይታወቃል።
ስኬቶች እና አበርክቶዎች:
💥አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሆሳዕና ከነማ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ቡድኑን #ሁለቴ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማሳደግ በክለቡ ታሪክ የማይረሳ ስራ ሰርተዋል።
* በ2007 ዓ.ም ሆሳዕና ከነማን ከሀላባ ከነማ ጋር ባደረጉት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በማሸነፍ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉን ሲያረጋግጡ የቡድኑ መሪ ነበሩ።
በተጨማሪ 2011 ሃዲያ ሆሳዕና ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አሳድገዋል። በፕሪሚየር ሊጉም 2008,2012,2016,2017 ዓ/ምህረቶች ከክለባችን ሃዲያ ሆሳዕና ጋር ቆይተዋል። የብሔራዊ ሊግ ዋንጫ ሁለቴ የአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ አንዴ በማንሳት የመጀመሪያው ነው።
💥አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ(መንቾ) ለሆሳዕና ከተማ ከመጫወት አንስቶ ሃዲያ ሆሳዕና እስከማሰልጠን ክለቡ በሚፈልቸው ወቅት ሁሉ ክለቡን በመቀላቀል ሙያዊ አገልግሎት የሰጡም ናቸው
💥 እርሳቸው እንደሚሉት፣ የቡድናቸው የስኬት ምስጢር በኳስ ቁጥጥር ላይ የተመሰረተ አጨዋወት መከተላቸው እና የተጫዋቾች ተነሳሽነት ነው።
💥 በክለባችን ላገለገሉበት ጊዜ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን። በክለቡ በቆዩበት ጊዜ ቡድናችንን
በ የእርስዎ ትጋት፣ ሙያዊነት እና ለቡድናችን ያለዎት ፍቅር ሁሌም ይታወሳል ከእርስዎ ጋር ክለባችን ያሳለፍቸው ጊዜያት እና ያገኘናቸው ድሎች ሁልጊዜም በልባችን ይኖራሉ።
በቀጣይ ላይ ታላቅ ስኬትን እና ደስታን እንመኝልዎታለን። መልካም እድል!"
✍️ናኒ የከቤራው