17/10/2025
የከሸፈው ፕሮፖጋንዳ!
ወያኔ ሰሜን እዝን አጥቅቶ ኢትዮጵያን ሲወርር ከጦርነቱ ባልተናነሰ መጠነ ሠፊ ፕሮፖጋንዳ ከፍቶም ነበር። ግን ከመቀጥቀጥ እና ከመሸነፍ ሊታደገው አልቻለም። የኢትዮጵያ ጀግኖች ቀጥቅጠው እርቃኑን አስቀርተው የሽንፈት ውርደትን አልብሰው አሸነፉት።
ዛሬም የከሸፈ ፕሮፖጋንዳውን አንግቦ እዚህም እዚያም የሚተነኩሰው ጽንፈኛው ኀይል ከባድ ምት እየደረሰበት ለቅሶ ላይ ይገኛል።
ነጭ ውሸት በፀራራ ፀሀይ!
ታዲያ ለደጋፊዎቹ እጅ መንሻ ይዞ የቀረበው አንዲት ታጣቂ አባሉን በጥምር ጦሩ ምት ሲያጣት ልዩ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ማዋልን መርጧል። በአስከሬን መነገድ የቆየ ልማዱ ቢሆንም ዛሬም ብዙ ውሸት እና ሰፊ የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻን እንደ ግብ ቆጥሮ እያስተጋባ ተስተውሏል። ግን ውሸት ውሸት እንጅ እውነት ሆኖ አያውቅም!
የምስጉን ስነምግባር እና ጀግንነት ተምሳሌቱን የመንግስት ጦር በዚህ አይነት ፕሮፖጋንዳ ስሙን ማጠልሸት ተቀባይነት የሌለው የተሸናፊው ጽንፈኛ ቡድን ባህሪ መሆኑን ሁሉም ተረድቶታል።
ጀግኖቻችን የከሸፈውን ፕሮፖጋንዳ ወደኋላ እየተው ወደፊት በደማቅ ድል ታጅበው ጉዟቸውን ቀጥለዋል!